Drum of Changes

Drum of Changes

Download on the App Store

Drum of Changes episodes

  • የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ነጻ ማውጣት፦ በ ንጉግ ዋ ቲዮንጎ እይታ

    "እኛ ደግሞ አፍሪካውያኖች የራሳችን ታሪክ የምንነግርበት፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የምናስተላልፍበት ጥበብ፣ የራሳችን መንገድ አለን። ስለዚህ ይሄ የአውሮፓ ተኮር የሆነውን አመለካከት ከአፍሪካ ስነ ጽሁፍ ውስጥ አውጥተን በአፍሪካ ተኮር ወይም ደግሞ አፍሮ ሴንትሪክ በሆነው ስንተካ አንደኛ ዲኮሎናይዝ እያደረግን ነው ማለት ነው።" ሲሉ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነጽሁፍ መምህርና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ስነጽሁፍ አስተማሪ እና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰን (ዶ/ር) አነጋግሮ የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ለማላቀቅ መደረግ ያሉባቸውን ጉዳዮች በቀዳሚው ክፍል እናስደምጣችኋለን። እንዲሁም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረክ መለያ የሆኗትን አትሌቲክስ (አትሌቶቿን) እና ቡናን በዲፕሎማሲ ረገድ ''ሶፍት ዲፕሎማሲ'' አማራጭነት መጠቀም በምትችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሁለተኛው ጉዳያችን አድርገነዋል። ለዚህም የታሪክ አጥኝ እና የመገናኛ ብዙሀን ጥናት ባለሞያ የሆኑትን ተረፈ ወርቁን አነጋግረናል።

    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:


    1 hr
  • ካሳ ወይስ የቀድሞውን መመለስ ፡ የአፍሪካ ጥሪ ለእውነተኛ ፍትህ

     "ይህ የአፍሪካ ዕዳ ተብሎ የሚጠራው ነገር በቀላሉ መወገድ አለበት። ሌባ ከቤትህ ሰርቆ ሲያበቃ እንዴት እንካ ቤትህን ስራበት ብሎ ገንዘብ ሊያበድርህ ይችላል? እንዴትስ ከራስህ ሰርቆ ያበደረህ ገንዘብ ላይ ወለድ ሊጥል ይችላል? ይህ ግራአጋቢ ነገር ነው።" ሲሉ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ተወካይ ከሆኑት አምብሮስ ኪንግ (ራስ ወልደ ስላሴ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

    "ፍትህ ለአፍሪካውያን እና አፍሪካዊ ዝርያ ላላቸው ሁሉ በካሳ መልክ" የሚለው ሐሳብ የአፍሪካ ኅብረት እ.ኤ.አ 2025 መሰባሰብያ ጭብጥ ነው። የአፍሪካ ፍትህና ካሳ በምን መልኩ ሊለካ ይችላል ፣ መልሱ ከባድ አከራካሪም ነውና ለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ተወካይ ከሆኑት አምብሮስ ኪንግ (ራስ ወልደ ስላሴ) ጋር ቆይታ አርጓል። የኢትዮጵያ የባህር ባለቤትነት ጥያቄን በተመለከተ በሰላሌ ዩኒቨርስቲ የታሪክና የቅርስ ጥበቃ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪውን ደረጀ ኃይሌ አነጋግረናቸዋል፡፡

    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:


    1 hr
  • የአፍሪካ ቀጣናዊ ጥምረቶች ፣ የአህጉር አቀፍ ትስስር ካስማዎች ወይስ ወጥመዶች?

    "አፍሪካ የገንዘብ ሀብት እጥረት እንደሌለባት ልብ ማለት ያስፈልጋል - አፍሪካውያን የጎደለን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚሆን ፍላጎት ነው። በእውነት የሚያስፈልገን ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት የሚያስችል ቁርጠኝነት ነው። የዚህ ዓይነቱ ቁርጠኝነት ስለጎደለንም ልብ በሚሰብር መልኩ ከውጭ በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ሆነን ቀርተናል" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

    ድራም ኦፍ ቼንጅስ በዛሬው ዝግጅቱ ሁለት የተለያዩ ግን ወሳኝ ጉዳዮችን በስፋት ይዳስሳል ፡፡ አህጉሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ቀጣናዊ ጥምረቶች ለአህጉር አቀፍ ትስስር ካስማዎች ናቸው ወይስ በውስን የፋይናንስ አቅማቸው ምክንያት አፍሪካን የማጥመጃ መረብ ሆነዋል ? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በደቡብ አፍሪካ በሚገኘው በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ 'በአረቡ ዓለም ፖለቲካ በተሳሳተ መንገድ እንድትሳልና ብሔራዊ ጥቋንም ለማስከበር ' የአረብ ሊግ ሊሆን ቀጣይ የጥምረት መዳረሻዋ እንዴት ሊሆን እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ምክለታቸውን አጋርተውናል፡፡

    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

    1 hr
  • ከምዕራቡ ዓለም ባሻገር :- ኢትዮጵያ ለቱሪዝሟ እድገት ወደ ደቡባዊው ዓለም ታማትራለች

    "ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ሁሉ አቅፋ ይዛለች ። ስለዚህ አንድ ሰው አፍሪካን በእውነት መጎብኘት ከፈለገ፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሁሉንም ማየት ይችላል።[…] ስለዚህ፣ በብሪክስ ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አገሮችን፣ ጥሩ የህዝብ ብዛትን እና ጥሩ ኢኮኖሚን በተመሳሳይ ጊዜ እናገኛለን፤ ይህም እነርሱን የቱሪስት እንግዶቻችን ልናደርጋቸው ያስችለናል።[...] ስፑትኒክ አፍሪካ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ብዙዎች ጋር ለማድረስ ይረዳናል። ሚዲያው ቢሮውን በኢትዮጵያ መክፈቱም ከራዕያችን ጋር በእጅጉ የተጣጣመ ነው" - ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማን አነጋግሮ የኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች ሀገራት ጭምር በማዞር አዲስ የቱሪዝም የገበያ እያማተረች ስለመሆኗ ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን ይዳስሳል። እንዲሁም ቻይና በቅርቡ ለአፍሪካ ሀገራት '' እተገብረዋለሁ'' ያለችውን የዜሮ ታሪፍ ጉዳይ ያነሳል። ለዚህም የፓን አፍሪካ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ክቡር ገናን አነጋግሯል።

    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:


    1 hr

About Drum of Changes

From the publisher's feed

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa…