
Sign up to save your podcasts
Or


“የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት ላይ ብቻ አላተኮሩም [ምዕራባውያን]። በአዳጊ ሀገራት ውሰጥ የህዝብ ቁጥር መጨመርን በመግታት፣ የሀገራቱን ሀብት ለመበዝበዝ የሚያመች ስትራቴጂ እየከተሉ ነበር። ይህ ያፈጠጠ የብዝበዛ አካሄድ ነው። ምክንያቱም በእነዚህ ሀገራት አነስተኛ የህዝብ ቁጥር መኖር ማለት ለምዕራቡ ዓለም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ቁጥጥር ወይም ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ቀላል ይሆንላቸዋል” ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እ.ኤ.አ. በ1974 በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ምክርቤት የተዘጋጀውንና ‘የኪሲንጀር ሪፖርት’ በመባል የሚታወቀውን ሰነድ በማዳሰስ ላለፉት አስርት ዓመታት የምዕራቡ ዓለም በተለይም በተመረጡ 13 የደቡቡ ዓለም ሀገራት ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የህዝብ ቁትራቸው እንዳያድግ ሲከተለው የነበረውን ስትራቴጂ እንፈሻለን። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ጋር ቆይታ በማድረግ ይህንን ሰነድ ፈትሸነዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
“አፍሪካ የራሷን ታሪክ፣ የራሷን እውነታ ለዓለም የምትነግርበት ድምፅ ይኖራት ዘንድ ፍፁም አስፈላጊ ነው። ምክኛቱ ደግሞ እስከዛሬ ድረስ አፍሪካን ብሎም የአፍሪካን ታሪክ በራሳቸው መንገድ ሲተርኩ ስለአፍሪካ ሲናገሩ የቆዩት አውሮፓውያን ናቸውና። ከአፍሪካ ውጭ [በአሜሪካ] እንዳደገች አንዲት ጥቁር ሰው እውነቱን ለመናገር ስለአፍሪካ መልካም ነገር ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ፓናፍሪካኒስቷ ጃኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የባሪያ ንግድ፣ የቅኝ ግዛት እና መዋቅራዊ ብዝበዛ በጥቁር ሕዝቦች ላይ ጥሎ ስላለፈው አሻራ እንቃኛለን። ጨምረንም መላው የጥቁር ሕዝቦች ለፍትህ እና ካሳ የሚያደርጉትን የትግል ጉዞ እንመለከታለን። በዚህ ጉዞ ውስጥም ለጥቁር ሕዝቦች የቆሙ ተቋሟት ዛሬም ድረስ ከቀጠለው የቀድሞ ቅኝ ገዥዎች ግብዝነት ጋር የሚያደርጉትን ትግል እንፈትሻለን። ለዚህም ታዲያ ኑሯቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉት ጥቁር አሜሪካዊቷ ፓናፍሪካኒስት፣ ደራሲ እና ወደ አፍሪካ የመመለስ ንቅናቄ አንቂ ጃኔል ሆይሌትን ጋብዝን በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ሐሳባቸውን አጋርተዉናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
“የምዕራቡ ዓለም የአፍሪካን የሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ከሚፈልግባቸው ምክንያቶች መካከል ዘረኛ ፖሊሲው አንደኛው ነው [...] ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ብዙ ወጣት ትውልድ ያላት አፍሪካ የዓለምን ሀብት ለመቆጣጠር ለያዙት ግብ እንቅፋት ትሆናለች የሚል ነው [...] ብሪክስ አፍሪካ ስለአፍሪካ የምታስብበት ብሎም አፍሪካ የራሷን ጥቅም ማስጠበቅ የምትችልበት ጠንካራ ህብረት ነው” ሲሉ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ ደቡብ አፍሪካዊቷ የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ ሻኪራ ቹናራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ትንቅራችን በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አጣዳፊ ጉዳይ ስለመሆኑ ያስቃኘናል። በዚህ ጉዳይ ላይ ደቡብ አፍሪካዊቷ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያዋ ሻኪራ ቹናራን አነጋግረናል። ተከታዩ ጥንቅራችን ደግሞ፣ በአፍሪካ ሌላኛውን የሉዓላዊነት ገፅታ ያስቃኘናል። በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ምስጋናው እያሱ፣ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ፋይናንስ አማካሪ እንዲሁም ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ፣ በአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገናል ።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
“ኩባ [...] የህልውና ፈተና በገጠመን ወቅት መስዋዕትነት በመክፈል ከጎናችን ቆማለች፤ አፍሪካውያን ግን በተዋለልን ልክ ለኩባ ደርሰንላታል ወይ?” ሲሉ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ይጠይቃሉ።
ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 5/2018 ዓ.ም. “ህብረት ከግላኮማ ነፃ ለሆነች ዓለም” በሚል ጭብጥ የዓለም የግላኮማ ሳምንት ይከበራል።
“ግላኮማ ታማሚዎች ሳያውቁት የማይቀለበስ የዓይነ ስውርነት የሚያስከትል በሽታ ቢሆንም፣ የግንዛቤ እጥረት ሁኔታውን አክብዶታል” ሲሉ የግላኮማ ስፔሻሊስቷ ዶ/ር አበባ ተክለጊዮርጊስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በዛሬው የ ድሪም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ ስለ ግላኮማ በሽታ ከስፔሻሊስትና ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አበባ ተክለጊዮርጊስ ጋር እንመክራለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ ስለ ኩባ የታሪክ መስዋዕትነት ከኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ጋር እንቆያለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
“ለአፍሪካ ይህ በጣም መጥፎ ዜና ነው። የነዳጅ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ አብዛኞቹ አገራት እንዲህ ዓይነቱን ጫና ለቋቋም እጅጉን ይቸገራሉ። [...] ስለዚህ የአፍሪካ አገራት ስለ አማራጭ የኃይል ምንጮች የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው።እንደሚታወቀው አፍሪካ ብዙ አማራጮች አሏት”ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ዝግጅታችን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን የጦር ዘመቻ ተከትሎ በአፍሪካ ላይ የሚመጣውን ሁለንትናዊ ጫና እና መፍትሄዎቹን በተመለከተ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) አነጋግርናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ መጋቢት 17-18 በአዲስ አበባ የሚካሄደውን አራተኛውን “በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረምን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ጋር ያደረግነውን ቆይታ ታደምጣላችሁ።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
"ምዕራባውያን ሩሲያን ወደ አቅም አልባ ትንንሽ ግዘቶች የመከፋፈል እቅዳቸው የቆየ ነው […] ከሰሞኑ ለዩክሬን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ማሰባቸው ይህ እቅዳቸው በመክሸፉ ተስፋ የመቁረጣቸው ማሳያ ነው" ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ የፈረንሳይ እና ብሪታንያ ለዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መዘጋጀታቸው ምን ዓለም አቀፍ ትርጓሜ አለው ስንል በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር የሆኑት ዳዊት መዝገበን አነጋግረናል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
"ላለፉት አስርት ዓመታት ዓለም አቀፍ ዜናዎች ከአንድ አቅጣጫ የሚመጡ እና የአንድ ወገን ሐሳብን የሚያንቀባርቁ ነበሩ … በአንፃሩ ደግሞ አሁን ያለንበት ወቅት የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ንቃት ጎልቶ ይስተዋላል … የዓለም ታሪክ ርዕሰ አንቀጽ እንጂ የማንኛውም ታሪክ ዳራ መሆንን እምቢኝ ያሉበት ወቅት ነው" ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ት/ት ክፍል መምህርና እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አየለ አዲስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ስለሚያደርጓቸው ትብብሮች በቀዳሚነት እንቃኛለን። ለዚህም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ት/ት ክፍል መምህርና እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አየለ አዲስ (ዶ/ር) አብረዉን ቆይታ አድርገዋል። በሁለተኛው ጥቅራችን ደግሞ በአፍሪካ የዲጂታል ክፍያ ስረዓት እጣፈንታን በተመለከተ፣ በቴንድኤክስ አዲስ አበባ 2026 ጉባኤ ላይ ተገኝተን ኮምፑሊንክስ የተሰኘ ኩባንያ ቢዝነስ ዳይሬክተር የሆኑትን ቻውላ ጋናትራን አነጋግረናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ
“ ከቆዳችን በታች ሁላችንም አንድ አይነት መሆናችንን እናያለን … ፖለቲከኞች ለራሳቸው ዓለማ ከዚህ የተለየ ኃቅ ሊያሳዩን የመቻል አቅማቸዉን አሳንሼ ግን ማየት አልፈልግም … ነገር ግን አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ሩሲያ ወይት ሌላ ቦታ ብንኖር ሰዎች ሁሉ አንድ ዘር ነን” ሲሉ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ፣ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ ተመራማሪ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እጅግ የተሟላ እና ጥንታዊ የሆነችውንና ከ3.3 ሚሊየን በላይ እድሜ ያላት የሰላምን (አውስትረሎፒቲከስ አፋረንሲስን) እና በቅርቡ የተገኘውን የ 2.6 ሚሊየን እድሜ ባለቤት ፓራንትሮፐስ ጨምሮ የብዙ ግኝቶች እና ምርምሮች ባለቤት፣'ምድረ ቀደምት (ላንድ ኦቭ ኦሪጅን)' የሚለውን መጠሪያ ያስተዋወቁ እና በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ተመራማሪ መምህር፣ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድን በእንግድነት ጋብዟቸዋል።በቅርቡ ያገኙትን ቅሪተአካል (ፓራንትሮፐስ) መነሻ በማድረግ ስለሰው ዘር አመጣጥ ፣ኢትዮጵያ ስላላት ማዕከላዊ ስፍራም እናወጋለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ90-95 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ የባህል ቅርሶች ከአህጉሪቱ ውጭ ይገኛሉ። ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሙዚየሞች ብቻ ከ500,000 በላይ የአፍሪካ ቅርሶችን ይዘዋል።ከእነዚህም አብዝኃኛዎቹ በቅኝ ግዛት ዝርፊያ፣በአስገዳጅ ሁኔታዎች ወይም በሕገ-ወጥ ዝውውር የተገኙ ናቸው።
"ከአገራችን ተዘርፈው ተወሰዱ ቅርሶቻችን በክፍያ መልሰን እንድንወስድ መጠየቃችን አሳዛኝ ነገር ነው። እነዚህን ቅርሶች የያዙ ሙዚየሞች ወይም የግል ቅርስ ሰባሳቢዎች ወደኢትዮጵያ እንዲመልሷቸው እናበረታታለን"ሲሉ የሺ ካሳ፣ የራስ ደስታ ዳምጠው የልጅ ልጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አባተ ጎበና (ዶ/ር) በበኩላቸው "በመቅደላ ጦርነት ወቅት ወደኢትዮጵያ የመጡ እንግሊዛውያን፣ አስቀድመው ስለኢትዮጵያ ውድ ቅርሶች ያውቁ ነበር። ቅርሶቹን ለመዝረፍ በጀት ተመድቦላቸው የመጡ ባለሞያዎችም የሀገሪቱ ቅርሶች ዘርፈዋል።[...] ምዕራባዉያን [በማንኛውም መልኩቢመጡ] ባዶ እጃቸውን ግን አይመለሱም ነበር።" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በምእራቡ ዓለም እስረኛ የሆኑ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ቅርሶችን ጉዳይ እንመረምራለን።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
''ብሪክስ እንደ አላማ አድርጎ ከተነሳው መካከል የፋይናንስ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ንፁህ የአየር ከባቢ መፍጠርና የዲጂታል ሥራዎች ማስፋፋት ይገኙበታል። እኛ አፍሪካዊያን ነገሮችን በብስለት መምራትና መጠቀም ከቻልን ከብሪክስ የልማት ባንክ ብዙ መጠቀም እንችላለን። የልማት ባንኩ ከቀደመው የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ጫናም እንድወጣም የሚያስችል ነው '' ሲሉ አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶ/ር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል።
ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ በንግድ እና ኢኮኖሚ ላይ ያለው በጎ ተፅዕኖ በተመለከተ ከአሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶክተር ጋር ተወያይተናል።
በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ጉዳይን በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድቤት ፊት ስለማቅረብ ከያዛቸው ውድነህ የኢንቫይሮመንታል ጂዮግራፈር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና አዳፕቲሽን ባለሙያ፣ መምህርና ተመራማሪ ጋር ቃኝተነዋል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ
From the publisher's feed