Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.
August 29, 2025በኖርዌይ የትውልደ ኢትዮጵያዊት ማህበራዊ ሰራተኛ ግድያባለፈው ዕሁድ ሌሊት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ታሚማ ኒብራስ ጁሃር በአንድ በኖርዌይ ኦስሎ በሚገኝ የታዳጊዎችና ወጣቶች ማዕክል (rihablitation center) በስራ ላይ እንዳለች በቤቱ ከሚኖሩትና ከሚገለገሉት በአንዱ በግፍ መገደሏ ድፍን ኖርዌይን ያስደነገጠና በርካታ ጥያቄዎችን ያስነሳ ኾኗል፡...more4minPlay
August 29, 2025የነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝትመንግስት የደመወዝ ጭማሪ አደርጋለሁ ማለቱን ተከትሎ የታየው የዋጋ ጭማሪ፤ ወጣቱ ስደትን እንደአማራጭ የማየት፣ እንዲሁም በትግራይ ደቡባዊ ዞን የተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋትን የተመለከቱ አስተያየቶች ይቀርባሉ።...more0minPlay
August 29, 2025ሉሲ እና ሰላም ፕራግ ውስጥ ለእይታ የመቅረባቸው አንድምታድንቅነሽ ወይም ሉሲ እና ሰላም ቅሪተ አካላት ቼክ ሪፐብሊክ ፕራግ ውስጥ ለእይታ በቅተዋል። ኤግዚቢሽኑን በተመለከተ የባህል ሚንስትሯ ሰላማዊት ካሳ በይፋዊ የማህበራዊ መገናኛ ገጻቸው የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት ለመንገር፤ አዲሲቷን ኢትዮጵያንም ለአለም ለማብሰር ድንቅነሽ/ሉሲ እና ሰላም በማዕከላዊ አውሮፓ ተገኝተዋል» በማለት ጽፈዋል።...more5minPlay
August 29, 2025በጌዴኦ ዞን በመሬት ናዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው በዞኑ ራጴ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት የገጠር ቀበሌያት ውስጥ ነው ፡፡ የመሬት ናዳው ትናንት ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ገደማ የደረሰው በወረዳ ጫራቃ እና ሀሮ በተባሉ ቀበሌያት ውስጥ ነው ፡፡...more4minPlay
August 29, 2025በአማራ ክልል የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ለተላላፊ በሽታዎች መጋለጡከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎተሁለደሬ ወረዳ ጃሪ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙተፈናቃዮች መኖሪያ ቤታችን ፈርሶ ከዝናብ እና ብርዱ ጋር መኖር ብንለምድም ወባና እና የተቅማጥ በሽታ ጤና ነሳን ይላሉ፡፡ አሁን ላይ ተቋማት ሥራ በማቆማቸው ነብሳቸውን ለማትረፍ በልመና እየታከሙ መሆኑን ገልጸዋል።...more4minPlay
August 29, 2025በኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆምና የሽግግር ጊዜ እንዲመቻች የቀረበ ጥሪበኢትዮጵያ በዘር ላይ የተመሰረተ ያለው ፖለቲካና የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም፣በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ትብብር ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ። የንቅናቅው ሊቀመንበር ዶክተር ባደገ ቢሻው ለዶቼ ቬለ እንዳሉት፣በሀገሪቱ ሁኔታዎች እየተረጋጉ ሲሄዱም ፍትህና ዲሞክራሲ የሚሰፍንበት የሽግግር ሂደት መፈጠር አለበት።...more4minPlay
August 27, 2025የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሥራ ለመፍጠር ሲያነክስ “ስደት እንደ አማራጭ ሳይሆን እንደ ብቸኛ መፍትሔ እየተቆጠረ ነው”ኢትዮጵያውያን የተሻለ የሥራ እና የገቢ አማራጭ ፍለጋ ወደ አረብ ሀገራት፣ ደቡብ አፍሪካ እና በሰሐራ በኩል ወደ አውሮፓ ሲጓዙ ለሞት፣ ስቃይ እና እንግልት ይዳረጋሉ። ዜናውን የሰሙ አለፍ ሲልም ሰቆቃውን የሚያውቁ ከመሰደድ አልተቆጠቡም። ተማራማሪዎች በኢትዮጵያ “ስደት እንደ አማራጭ ሳይሆን እንደ ብቸኛ መፍትሔ እየተቆጠረ” መምጣቱን ይናገራሉ።...more0minPlay
August 27, 2025በኢትዮጵያ ስለቀደምት የሰው ልጅ ዝርያ መረጃ የሚሰጡ አዳዲስ ቅሬተ አካላት ተገኙየቅሪተ አካል ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ አፋር ክልል ዕድሚያቸው ከ2.6 ሚሊዮን ዓመት በላይ የሆኑ የጥርስ ቅሬተ አካላት ማግኘታቸውን በቅርቡ ይፋ አድርገዋል።የተገኙት ጥርሶች ከጠቅላላው የሰው ልጅ ቅሬተ አካል ጋር ሲነፃጸር ትንሽ እና በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም ፣ ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት አዲስ የዝግመተ ለውጥ የምርምር ምዕራፍ የሚከፍቱ ናቸው።...more0minPlay
August 27, 2025የሽግግር ፍትሕ አተገባበር ጉዳይ ምን ላይ ደረሰ?የፍትሕ ሚኒስቴር ባዋቀረውና 13 አባላት ባሉት የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች ቡድን ሲከናወን የነበረው ሥራ ውጤቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ ሂደቱ ምን ላይ ይገኛል? የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከሳምንታት በፊት ዓመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ "ከሕግ ረቂቅ ሰነዶች ውጪ ሌሎች ተግባራት በታቀደላቸው ጊዜ አለመከናወናቸው አሳሳቢ ነው" ብሏል።...more4minPlay
August 27, 2025የናይሮቢ የአየር ንብረት ፍትህ የበጋ ትምህርት በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነውየ5ኛው የናይሮቢ የአየር ንብረት ፍትህ የበጋ ትምህርት ወጣት መሪዎችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን፣ ፖሊሲ አውጪዎችን እና ምሁራንን ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአለም ሀገራት በማገናኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።...more3minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.