Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.
August 25, 2025ኦሮሚያ ክልል:- አርሶ አደሮችን የሚያግተው ማነው?በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ሸዋ ዞን ግንደበረት ወረዳ ካለፈው መጋቢት ወር ወዲህ አንጻራዊ የፀጥታ ይዞታ ከሰፈነባቸው አከባቢዎች አንዱ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ። ይሁንና ባለፉት ስድስት ዓመታትን ጨምሮ እስካሁን ድረስ አርሶ አደሮችን በማገት የሚፈጸመው ወከባ በባሰ ሁኔታ መቀጠሉን ነዋሪዎች እና የተለያዩ የአከባቢው ማህበረሰብ እየገለጹ ነው፡፡...more4minPlay
August 25, 2025አሳሳቢዎቹ እገታ እና አስገድዶ የመሰወር ድርጊቶችበተደጋጋሚ እየተፈፀመ የሚገኘው እገታ እና አስገድዶ መሰወር "የሥርዓት እልበኝነት" ማሳያ እንዳይሆን ጥንቃቄ እንዲደረግ ተጠየቀ። በጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ተሳትፎ ባላቸውና በሌሎች ላይ የሚፈፀመው ይህ ድርጊት "መንግሥታዊ እና ሕጋዊ ጥበቃ አለኝ" የሚለውን የማኅበረሰብ እምነት እየሸረሸረ የሚመጣ ነው" ሲሉ አንድ ፖለቲከኛ ገልፀዋል።...more4minPlay
August 25, 2025“የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል” መባሉና በአማራ ክልል የፈጠረው የዋጋ ጭማሪአዲስ የመንግሥት ሠራተኛ የደመውዝ ጭማሪ ይደረጋል በሚል የአንዳንድ ሸቀጦች ዋጋ መጨመሩን የአማራ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል፡፡ የደመውዝ ጭማሪ ሊደረግ ነው” በሚል አንዳንድ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ ነዉም ተብሏል። ፡...more4minPlay
August 24, 2025እንወያይ፤ ለኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ዋና ዋና ፈተናዎች እና መፍትሔዎችውይይቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ይረዳል በሚል በመስጠት ላይ ስለሚገኘው የክረምት ልዩ ስልጣና ምንነት እና ስለገጠሙት ፈተናዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አዲሱ የትምህርት ዘመን ሊጀምር የአንድ ወር እድሜ ያህል እንደመቅረቱ ከትምህርት ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሯል።...more45minPlay
August 24, 2025ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ጦርነት ሲያበቃ የውጪ ሀገራት ወታደሮች በዩክሬን መገኘት “ጠቃሚ” እንደሚሆን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ገለጹዛሬ ብሔራዊ የነጻነት ቀኗን ያከበረችው ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የገጠመችው ጦርነት ሲያበቃ ዋስትና የሚሆናት የደሕንነት ማረጋገጫ ከምዕራባውያን አጋሮቿ ጋር በመሆን ለማበጀት ጥረት እያደረገች ትገኛለች።...more0minPlay
August 23, 2025በደቡብ ሱዳን በበረታ ግጭት እና ፖለቲካዊ ቀውስ ሰላም እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠነቀቀየደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በአምስት ዓመታት ውስጥ ሰባተኛ የፋይናንስ ሚኒስትር ሾመዋል። ልጃቸው አዱት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ፕሬዝዳንታዊ አማካሪ ሆናለች። ኪር ተቀናቃኛቸው ሪየክ ማቻርን አስረው ሹም ሹር ሲያካሒዱ በግጭት እና ፖለቲካዊ ቀውስ የሀገሪቱ ሰላም እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠንቅቋል።...more0minPlay
August 23, 2025ክፍተቱ የሰፋው የውጭ ምንዛሪ ተመን እና የትይዩ ገበያውየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሰሞኑ 150 ሚሊየን ዶላር ግድም ለንግድ ባንኮች በውጪ ምንዛሪ ክምችት ብያከፋፍልም የንግድ ባንኮች እና ገለልተኛ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች የውጪ ምንዛሪ መጠን በ10 በመቶ ስለመስፋቱ እየተነገረ ነው፡፡ ባሁን ወቅት በኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላር በ140 ብር ገደማ እየተመነዘረ ነው።...more4minPlay
August 23, 2025በአፍሪካ ክትባቶች በብዛት ለማምረት የተወጠነው ዕቅድ ከምን ደረሰ?የኮቪድ-19 ዓለምን ካመሰ በኋላ የተሠሩ ክትባቶች በፍጥነት እና በፍትኃዊነት አለመዳረሳቸው የአፍሪካን ጥገኝነት አጋልጦታል። ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወዲህ አፍሪካ ክትባቶች እና መድሐኒቶች በማምረት ከጥገኝነት እንድትላቀቅ በርካታ ዕቅዶች አሉ። ዕቅዶቹ በረዥም ጊዜ ምን ያክል ዘላቂ ናቸው?...more9minPlay
August 23, 2025በአማራ ክልል የተፈናቃዮች የመጠለያና የምግብ ጥያቄበአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ጃራ የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በመኖሪያ መጠለያ መቸገራቸውን ሲገልፁ የደቡብ ወሎ ተፋናቃዮች ደግሞ “በምግብ እጥረት ተቸግረናል” ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የምግብ እርዳታ መቀነስ ቢኖረም እርዳታው ግን አልተቋረጠም ነው ያለው፡፡...more0minPlay
August 23, 2025ወደ ዩክሬን የሰላም አስከባሪ ጦር የመላክ ሀሳብበ ጀርመን ውዝግብ አስነሳበዩክሬ እና በሩስያ መካከል ሰላም ስለመውረዱ ምንም የተጨበጠ ነገር ባይኖርም ፤ ጀርመን ግን «ቡንደስቬር»እየተባለ የሚጠራውን የሀገሪቱን ጦር በሠላም አስከባሪ ሀይል ውስጥ የማሳሳተፉ ሀሳብ ከወዲሁ እያወዛገበ ነው።ሁለቱ ሀገራት ሰላም ካወረዱ የጀርመን ሚና ምን ሊሆን ይችላል? የሚለውም በጀርመን ፖለቲከኞች ዘንድ እያከራከረ ነው።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.