Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.
August 21, 2025እስካሁን የት እንዳሉ ያልታወቀው የጋዜጠኞች ጉዳይባለፈው ሳምንት ጭንብል በለበሱ ሰዎች የታፈነው እና ሌሎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ያላቸው ጋዜጠኞች ጉዳይ እጅግ እንዳሳሰበው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ገለፀ። የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ እንዳሉት ኢትዮጵያ «ለጋዜጠኞች ምቹ ያልሆነ ኹኔታ ያለባት ሀገር እየሆነች መጥታለች።»...more4minPlay
August 20, 2025የሲቪል ማኅበራት አስተዳደር የሚያረቀዉ ሕግ ላይ የቀረበው ስጋትአምነስቲ ኢንተርናሽናል በሲቪል ማኅበራት አስተዳደር በሚረቀቀዉ ሕግ በተለይ የሲቪል ማኅበራትን የሚመራዉ ቦርድ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ይወድቃል የሚል ስጋቱን አስታዉቋል። አዲስ «እየተረቀቀ» ነዉ በተባለዉ ደንብ መሰረትም ቦርዱ 7 አባላት ይኖሩታል ተብሏል።ከመካከላቸው 5ቱ በመንግሥት ሲሾሙ የቀረው 2 ስፍራ ብቻ ለሲቪል ማኅበራቱ የሚተው ነዉ።...more0minPlay
August 20, 2025የኢትዮጵያ መንግሥት የደመወዝ ጭማሪን “ገንዘብ ነው የሚያስብለው ገበያ ሲረጋጋ ብቻ ነው” የመንግሥት ሠራተኛየመንግሥት ሠራተኞች ከመስከረም 2018 ጀምሮ ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ጭማሪ እጃቸው ከመግባቱ በፊት የሸቀጦች ዋጋ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ በመሳሰሉት ላይ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል ሥጋታቸውን ተናግረዋል። “ያልተገባ” የዋጋ ጭማሪ ሊኖር እንደሚችል ያመኑት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።...more10minPlay
August 20, 2025ስለደመወዝ ጭማሪው የሕዝብ አስተያየትየደመወዝ ጭማሪ ለሠራተኛው መልካም ከመሆኑም በላይ አንገብጋቢ ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ሆኖም ጭማሪው ብቻውን በቂ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ የደመወዝ ጭማሪው ለዋጋ ንረት ምክንያት ሆኖ ማህበረሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና አንዳይከሰት በአቅርቦትና መሰል ስራዎች ላይ ተገቢ ቁጥጥር ላይ ይበልጥ መሰራት እንዳለበት የነዋሪው አብይ ጥያቄ ነው፡፡...more4minPlay
August 20, 2025የትግራይ ክልል ኃይሎችን ለመሸምገል የተደረገው ጥረትበትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት 'ተስፋ ሰጪ' ሽምግልና መደረጉን የትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማቲክ የተባለ የተቋማት ስብስብ አስታወቀ። በሌላ በኩል ተቃዋሚው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ 'የትግራይ ፖለቲካ ከትግራይ ወጥቶ፥ በውጭ ኃይሎች እየተገፋ ነው' ብሏል። በትግራይ ላለው የፖለቲካዊ ቀውስም የህወሓት ቡድኖችን ተጠያቂ አድርጓል።...more4minPlay
August 20, 2025ራስ፤በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች AIን መጠቀም የሚያስችለው መተግበሪያእንደ ቻት ጂፒቲ ( ChatGPT)ያሉ በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ ዲጅታል መድረኮች በአብዛኛው በእንግሊዝኛ የሚሰሩ በመሆናቸው ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች ምቹ አይደሉም። በሶስት ወጣቶች በቅርቡ ይፋ የሆነው ራስ መተግበሪያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን (AI ) በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ለመጠቀም ዕድል የሚሰጥ ነው።...more3minPlay
August 20, 2025የ11 ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጥምረት ምስረታ ጉባኤአገው ለፍትሕና ዴሞክራሲ፣አገው ብሔራዊ ሸንጎ፣ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣የዶንጋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣አፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ፣ ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ እና የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ተጣምረናል ብለዋል...more4minPlay
August 19, 2025ደቡብ ትግራይ ሞኾኒ ከተማ በተቀሰቀ ግጭት 6 ሰዎች ቆሰሉሁነቱ የተከሰተው ከትግራይ ሐይሎች ጋር ልዩነት ውስጥ የገባው፥ በቅፅል ስሙ ቴንሽን ተብሎ የሚታወቅ ኮነሬል ሓለፎም መሓሪ የተባለ የሚሊሻ ሐላፊ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል መሞከራቸው ተከትሎ ነው የተባለ ሲሆን፥ በዚህ መካከል በማህል ከተማ ቶክስ ተከፍቶ ብያንስ ስድስት ሰዎች በጥይት መጎዳታቸው አሰምተናል።...more0minPlay
August 19, 2025የመራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ የ100 ቀናት የስልጣን ጊዜትራምፕና የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲንን በአላስካ ዩናይትድ ስቴትስ ባካሄዱት ጉባኤ ላይ ዜሌንስኪም ሆነ አንድም የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገር ባይጋበዝም ሜርስ አውሮፖች፣ ዩክሬንና ኔቶ የተካፈሉበት ጉባኤ እንዲካሄድ አድርገዋል። ትራምፕም በጉባኤው ላይ በስልክ ተሳትፈዋል። በዚህም «አውሮጳንና ጀርመንን አትርሱ» የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።...more0minPlay
August 19, 2025የዩናይትድ ስቴትስ፣ የዩክሬንና የአዉሮጳ መሪዎች የሠላም ውይይትየውይይቱ ዋና ግብም ዘለንስኪና ፑቲን በቀጥታ የሚገናኙበት የሁለትዮሽ ውይይት መድረክ ማመቻቸት፣ ያም በተሳካ ሁኔታ ከተካሄደ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የታከሉበት የሶስትዮሽ ውይይት የማድረግ ራዕይን የሰነቀ ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጀመርያው ውይይት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.