Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.
August 27, 2025በደብረ ብርሀን የተጠለሉ ተፈናቃዮች አቤቱታበአማራ ክልል ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካክል በሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን ከተማ በሶስት መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙት ለመጠለያ ችግር መዳረጋቸውን ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፣ ተፈናቃዮቹ የእርዳታ እህልም ቢሆን ወቅቱን ጠብቆ እንደማይደርሳቸው ይገልፃሉ።...more4minPlay
August 27, 2025በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ልጆቻቸውን ለመታደግ ከነብር ጋር ትግል የገጠሙ አባትበምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከገባው ነብር ጋር ትግል የገጠሙ አባት ሕይወታቸው በተዓምር ተርፏል። ሙስጠፋ ረሺድ ምሽት 1፡30 ግድም ወደ መኖሪያ ቤታቸው ከገባው ነብር ታግለው ልጆቻቸውን እና ባለቤታቸውን ቢያተርፉም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።...more4minPlay
August 26, 2025በትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ሰበብ የክልሉ አስተዳደርና የፌደራል መንግሥቱ ዉዝግብበሳምምንቱ መጨረሻ በአሸንዳ በዓል ስነስርዓት የተናገሩት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ ከፌደራል መንግስት ይጠበቅ የነበረው የትግራይ ክልል ሕገመንግስታዊ ግዛት እንዲሁም ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው መመለስ ምላሽ አለማግኘቱ በማንሳት ወቅሰዋል...more3minPlay
August 26, 2025ዘንድሮ ከ287 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኤሌክትሪክ መሰረተልማቶች ተሰርቀዋል-መስሪያ ቤትየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ሃምሌ በተጠናቀቀው የ2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት 287.5 ሚሊየን ብር (አምስት ሚሊየን ዶላር) በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትና በኃይል ስርቆት የደረሰበትን ኪሳራውን በገለጸበት ሪፖርቱ በስርቆት ያጋጠመው ኪሳራው ከፍተኛ ስጋት መደቀኑንና የአገልግሎት ተደራሽነት ጥረቶችን ፈተና ውስጥ ስለማስገባቱ ተጠቁሟል፡፡...more4minPlay
August 26, 2025በደቡባዊ ትግራይ የተፈጠረዉ ዉጥረት እንደቀጠለ ነዉየትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በክልሉ የደቡባዊ ዞን አስተዳደር አካላት ማንሳቱን ተከትሎ ዳግም በአካባቢው የፀጥታ ስጋት ተከስቶ ይገኛል።ባለፈው ወር የዞኑ አስተዳደር አካላት መውረዳቸውን የተቃወሙ የዞኑ ነዋሪዎች፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ቅሬታቸው ሲያቀርቡ የነበሩ ሲሆን ይሁንና ይህ ተቃውሞ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል...more3minPlay
August 26, 2025የስኳር ህመምተኛ ታዳጊዎች ቁጥር መጨመርበስኳር ህመም የሚጠቁ ታዳጊዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ብቻ 365 የስኳር ታማሚ ታዳጊዎች ክትትል እየተደረገላቸው ነው ፡፡ታዳጊዎቹ በየወሩ በሆስፒታሉ በህመሙ ዙሪያ ትምህርታዊ ገለጻ ይደረግላቸዋል ፡፡ ከህመሙ ባህሪያት ጋር በተያያዘ ምን ማድረግ እንዳለባቸውም ጥያቄዎችን ያነሳሉ፣ከሀኪሞች ምላሽና ማብራሪያም ይሰጣቸዋል ፡፡...more9minPlay
August 26, 2025ሰሞኑን ጥምረት የመሠረቱ ክልላዊ ፓርቲዎች ግንባር እስከመመሥረት እንደሚጓዙ ገለፁጥምረቱ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልላዊ ፓርቲዎች ላይ ተከትሏል ያለው "አግላይ አካሄድ" ለመመስረቱ መነሻ እንደሆነው ከዚህ በፊት አስታውቋል።ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ግን ይህን አቋም "ተገቢነት የሌለው" በማለት---- ወቀሳዉን ውድቅ አድርጓል።...more4minPlay
August 25, 2025ማሕደረ ዜና፣የኢትዮጵያ ጉዞ አቅጣጫዉ ይታወቅ ይሆን?ኢትዮጵያ ከአፍሪቃ አንደኛ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ገንባታ-በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ከሌላት፣ ደሞዝ ተጨምሮ የሠራተኛዉ ኑሮ ካልተሻሻለ፣ ብልፅግናዋ እየተወራ-ሥራ አጥነት፣ ሥደትና ድሕነት ካናጠረባት አንድም የሚባለዉ ጥሩ ሁሉ ሐሰት ነዉ።ሁለትም መልስ ያልተሰጠዉ መሠረታዊ ችግር አለ ማለት ነዉ...more14minPlay
August 25, 2025“ የኢትዮጵያን ይግዙ “ ፕሮጀክት ተስፋ እና ተግዳሮትመንግሥት “የኢትዮጵያን ይግዙ“ በሚል የአገር ውስጥ ምርትን ወደ ገበያ ለማስገባት የሚያስችለውን ፕሮጅክት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል። የፕሮጀክቱ አካል የሆነው የግብይት መድረክ በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ነዉ። ፕሮጀክቱ ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅ ረገድ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡...more4minPlay
August 25, 2025በህዳሴ ግድብ ምርቃት ሰሞን የሚደረገው የኢትዮጵያ እና ግብጽ የእግር ኳስ ግጥሚያ እና ሌሎችየኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ቀሪ የማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት እያደረገ ነው። ካይሮ ላይ ከግብጽ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርገው ተጠባቂ ጨዋታ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ያለበትን አቋም እንጠይቃለን። የጀርመን ቡንደስ ሊጋ አዲሱ የውድድር ዓመት በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በይፋ ተጀመሯል።...more11minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.