Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.
August 04, 2025ሰላም ስምምነት ይዘቶች እስኪፈፅሙ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ቁመናውን ጠብቆ ይቆያል መባሉየሰላም ስምምነት ይዘቶች እስኪፈፅሙ እንዲሁም የሚጠበቀው የሰራዊት ስንብት ሂደት እስኪተገበር ድረስ 'የትግራይ ሰራዊት' ወታደራዊ ቁመናው ጠብቆ እንደሚቆይ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ። ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የፌደራሉ መንግስት ሐላፊነቱ እንዲወጣም ጀነራል ታደሰ ጥሪ አቅርበዋል።...more3minPlay
August 04, 2025‘ማህበረሰብን ማብቃት’ ሁሉን አቀፍ መርሃ ግብር በዋሽንግተን ዲሲበዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ለምስራቅ አፍሪካ ማሀበረሰብ አካላት ተደራሽ የሆነ ሁሉን አቀፍ መርሃ ግብር ተካሄደ። ባሳለፍነው ቅዳሜ የተካሄደው ይሄው ዝግጅት፣ የተለየዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የዳሰሱ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች የተደረጉበት፣ የመጽሃፍት አውደ ርዕይ፣ የንግድ ትረኢት፣ የጤና አቅርቦትና የመዝናኛ ዝግጅትን ያካተተ ነበር።...more5minPlay
August 04, 2025የኦሮሞ ልሂቃን ጥሪ እና የኦነግ መግለጫየኦሮሞ ምሁራንና የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በሚል እራሱን የሰየመ የልሂቃን ቡድን ባሳለፍነው ሰሞን በዩናይትድ ስቴትስ ተሰብስቦ በኦሮሚያ ክልል፣ በኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የፖለቲካ ግቡን አስቀምጠዋል፡፡ሆኖም ኦነግ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ በስብስቡ ውስጥ የወከለው አካል አለመኖሩንና አለመሳተፉን አስታዉቋል።...more4minPlay
August 03, 2025የተቃዋሚዎች ወቅታዊ ውይይቶች ለኢትዮጵያ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ያመላክቱ ይሆን?ፍጹም የፖለቲካ እና የዓለማ ልዩነት ያነገቡ እነዚሁ ቡድኖች በውይይቶቻቸው ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ቀውስ ዘላቂ መፍትሄ የሚሏቸውን የተለያዩ ሃሳቦች እያቀረቡ ሲሆን በዋናነት ግን አሁን በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ካለፈ በኋላ ስለሚኖር የሽግግር ስረዓት መምከሩን ትኩረት ሰጥተዉበታል።...more0minPlay
August 03, 2025ሩሲያ በዶኔትስክ እና ኼርሶን ግዛቶች በፈጸመችው ድብደባ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታወቁከጥቁር ባሕር አጠገብ በምትገኘው የሩሲያ ሶቺ ከተማ አጠገብ ከሚገኝ የነዳጅ ማደያ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በዩክሬን የድሮኖች ጥቃት የተቀሰቀሰ እንደሆነ የሩሲያ ባለሥልጣናት ወንጅለዋል።...more0minPlay
August 02, 2025በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቀቀበፍራንክፈርት ከተማ ሲካሔድ የሰነበተው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቋል። በሁለት ዲቪዚዮኖች 40 ቡድኖች በተሳተፉበት የአዋቂዎች የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮ-ዴንማርክ እና ትዮ-ፍራንክፈርት አሸንፈዋል። በፌስቲቫሉ ሕብስት ጥሩነሕ፣ ብርሀኑ ተዘራ እና ልጅ ሚካኤል የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን ያቀረቡበት መርሐ-ግብርም ነበር።...more6minPlay
August 02, 2025ትኩረት በአፍሪቃ፤ የሱዳን መከፋፈልና የአፍሪቃ ረሐብየሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል በሱዳን የትይዩ መንግስት ማቋቋሙን ከዳርፉር ይፋ አድርጓል። በ2030 በዓለማችን ከሚኖር የረሐብ ችግር 60 በመቶ የምትሸፍነው አፍሪካ መሆኗን ሰነዱ ይፋ አድርጓል።...more14minPlay
August 02, 2025"የዳግም ግጭት ሥጋት" እንዳሳሰበው ኢሰመጉ ገለፀ"በተለያዩ አካላት የሚደረጉ ወታደራዊ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች፣ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች እና የሚዲያ ዘመቻዎች" እጅግ እንዳሳሰቡት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ገለፀ። "አለመግባባቶች በውይይትና በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን ሁኔታ በማመቻቸት ማኅበረሰቡ ከሥጋት ወጥቶ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር" ለግጭት ማቆም ስምምነት ፈራሚዎች ጥሪ አድርጓል።...more3minPlay
August 02, 2025“በኦሮሚያ የቀጠለው ግጭት የማህበረሰቡን ሰቆቃ አባብሷል” ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴበኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና አማጺ ኃይሎች መካከል በአገሪቱ ትልቁ ክልል ኦሮሚያ የሚደረገው ግጭት “አውዳሚ ውጤትን እያስከተለ ነው” ሲል ዓለማቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) አስታወቀ፡፡ ኮሚቴው በክልሉ የቀጠለው ግጭት ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው የጤና እና ሌሎችም መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ እንቅፋት እየሆነ ነው ብሏል፡፡...more4minPlay
August 02, 2025ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚሠሩ አራት የሐዋላ አስተላላፊዎችን በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወነጀለችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዩናይትድ ስቴትስ የሚንቀሳቀሱ አራት የሐዋላ አስተላላፊዎችን “በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር” ወነጀለ። በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች ድርጅቶቹን እንዳይጠቀሙ መክሯል። ሐዋላ አስተላላፊዎቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች “የሚመለከታቸው አካላት ምርመራ በማካሔድ እንዲተባበሩ” ብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቅርቧል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.