Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.
August 07, 2025የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት የነሐሴ 01 ቀን 2017 መሰናዶበየመን የባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ስደተኞች ቁጥር 92 ደርሷል። በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡ መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። አደጋው ያስደነገጣቸው ኢትዮጵያውያን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ስለ ስደት መንስኤዎች ሐሳባቸውን እያጋሩ ነው።...more9minPlay
August 07, 2025የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ሺዎችን አፈናቀለ፤ ቤትና ሰብልም አጠፋበደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሰበታ ሀዋስ ወረዳ አዋሽ በሎ ነዋሪ የሆኑት እመጫት እናት በአከባቢው ካሉ መኖሪያ ቤቶች አንዱም ሳይቀር በወጣው የአዋሽ ወንዝ ሙላት ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው በደጃፋቸው አስፓልት ዳር በተወጠረ ሸራ ውስጥ አራስ ልጃቸውን ይዘው ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተናቸዋል...more3minPlay
August 07, 2025የሰሜን ወሎ ሕዝብ ዝናብ እንዲጥል ፈጣሪዉን ሲማፀን ዝናብና ነፋስ ሰዉ ጎዳ ንብረት አጠፋምአደጋው በተከሰተበት ወቅት በቤቶቹ ውስጥ የነበሩ 28 ሰዎች ነፋስ በሚጥለው ቆርቆሮ እና ሚስማር ተመተው ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን የገለፁት ተፈናቃዮች አሁን ቀሪ ያልወደቁ መጠለያ ቤቶችን በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ በመሆናቸው በቀጣይ ሊወድቁ ይችላሉ ሲሉ ስጋታቸውን ይናገራሉ...more4minPlay
August 06, 2025ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት 80ኛ ዓመት በኋላ ያንሰራራው ቀኝ ጽንፈኝነት ዘረኝነትና ፀረ-ሴማዊነትበጎርጎሮሳዊው1933 ዓም በተካሄደው የጀርመን ምርጫ 17 ሚሊዮን 277 ሺህ 180 ጀርመናውያን ለሂትለርና ለጀርመን ብሔራዊ ሶሻሊስት የሠራተኞች ፓርቲ ድምጻቸውን በመስጠት ስልጣን እንዲይዝ መንገዱን ጠርገውለታል።ልዑል ዶክተር አስፋ ወሰን እንደተናገሩት ሂትለር ስልጣን የያዘው በዴሞክራሲ ምርጫ ነው። ለዚህ ያበቃውም የህዝቡ የኮምኒዝም ፍራቻ ነበር።...more12minPlay
August 06, 2025የሕገ-ወጥ ስደት አስከፊ ገጽታ - ከሞት መለስ ያሉ የስቃይ ምዕራፎችመቸገርን ለመጋፈጥ የበረሃ ሲሳይ፣ መሆን፣ የማያልቅ የተስፋ ጉዞ ውስጥ መዳከር፣ ርህራሄ ጨርሶ በራቃቸው ሰዎች መበዝበዝ፣ ቁራሽ ዳቦ ሕልም በሚሆንበት ስፍራ ውስጥ ራስን ማግኘት ሲከፋም ከጀልባ ላይ ተገፍትሮ መጣል የስደት እውነታ ሆነው ሳለ ሕገ ወጥ ስደት ዛሬም እንደትናንቱ፣ ነገም እንደዛሬው የማይቀንስ፣ የማይጠፋውስ ለምንድን ነው?...more5minPlay
August 06, 2025ወጣቶች መሞት እንዳለ እያወቁ ለምን በአደገኛ የጉዞ መስመር ይሰደዳሉ?የዋጃ ከተማ ነዋሪ ወጣትም በባህር ወደ ሳውዲ አረቢያ ቢያመራም ተመልሶ መጥቷል፡፡አሁንም ለመሄድ ያስባል። በማዕበል ምክንያት፣ በረሃና ውሃ ጥም የሞቱ ጓደኞቹን ያስታውሳል፡፡ ዋጃ ላይ በጣም አልቋል እኔም እራሴ ስደተኛ ነኝ፤ መከራ አለ፤ ተስፋ ቆርጠህ ነው የምትሄደው ከዚህ ስትወጣ ሞትን ትመርጣለህ፤ ጓደኛ ሲነጠልህ ታየዋለህ፤ በርሃብ ይላል።»...more4minPlay
August 06, 2025የብሔራዊ ባንክ ገዥ በትይዩ የውጪ ምንዛሪ ገበያ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ እንደሚወረስ አስጠነቀቁየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከአሜሪካ እና ከዱባይ የሚዘወሩትን ጨምሮ በውጪ ምንዛሪ ትይዩ ገበያ ላይ ዘመቻ ጀምሯል። ባንኩ ከፍተኛ ልዩነት የሚታይባቸው ይፋዊ እና ትይዩ ተመኖች ተዋህደው ወጥ የውጪ ምንዛሪ ገበያ እንዲፈጠር ይፈልጋል። ነጋዴዎችን ጨምሮ ኢ-መደበኛውን ገበያ ለሚጠቀሙ ገንዘባቸው ሊወረስ እንደሚችል የብሔራዊ ባንክ ገዥ አስጠንቅቀዋል።...more11minPlay
August 06, 2025ከስማርት ስልክ ሱስ ለመውጣት የሚረዱ ሳይንሳዊ ዘዴዎችስማርት ስልከዎ በእጅዎ ከሌለ እራስዎን ሲቸገሩ ያገኙታል? ወይም ከሰዎች ጋር መገናኘትን ወደ ጎን በመተው ብቸኝነትን ይመርጣሉ? እነዚህ ባህሪያት የእርስዎ የስልክ አጠቃቀም ጤናማ እንዳልሆነ የሚያሳዩ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ናቸው።ባለሙያዎች እንደሚሉት የስልክ ሱስ እንቅልፍ መተኛት ሲገባን እንኳን ስልኮቻችን ያለማቋረጥ እንድንመለከት ይገፋፉናል።...more11minPlay
August 06, 2025ኢትዮጵያዊያንን ለአደገኛ የፍልሰት ጉዞ የሚዳርጓቸው ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው ?ወጣቶች ስለስደት ያላቸው አመለካከት አስደንጋጭ እንደሆነ ከሚያገኛቸው ወጣቶች ለመገንዘብ መቻሉን ለዶቼ ቬለ የተናገረው በረከት “በሕገ ወጥ ፍልሰት ምክንያት የደረሰብኝን የሰባት ዓመት የእሥርና የመከራ ጊዜ መነሻ በማድረግ ለብዙዎች መረጃ ለመስጠት ሞክሪያለሁ ፡፡ በቻልኩት መጠን ግንዛቤ ለመፍጠር ሰርቼያለሁ ፡፡ ነገር ግን ወጣቱ አይሰማህም ብሏል።...more4minPlay
August 06, 2025ግጭት በአሮሚያ እና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎችበነንሰቦ ወረዳ ገመቹ ቀበሌ ነገዎ ዋቃ እና ገዳ ሰንበቶ የሚባሉ በኮኮሳ ወረዳ አራርሶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዳንጎ በሚባል ስፍራ መገደላቸውን የተናገሩት የየአከባቢው ነዋሪ የግጭቱ መንስኤ መሬት የማስፋፋትና መቀማት ፍላጎት ነው ይላሉ፡፡ “ህዝቡ በሰላም ሲኖር ነበር፤ሲዳማ ክልል ከሆነ በኋላ በመሬት ማስፋፋት ፍላጎት ተደጋጋሚ ግጭት እየደረሰ ነው ብለዋል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,908 episodes available.