Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
June 02, 2025ማሕደረ ዜና፤ ሊቢያ፣ ኃያላን ያወደሟት፣ታጣቂዎች የሚተራመሱ፣ ዘራፊዎች የሚሻሙባት ሐገርበ2011 የፖለቲካ እዉቅና ያገኙት ሙስጠፋ አብዱል ጀሊል፣ መሐመድ ጅብሪል፣ አብዱረሒም ኤል-ካይብና መሰሎቻቸዉ ያቺን የነፃነት ተፋላሚዎች፣ የአፍሪቃ ሐብታም፣ ቅንጡ ሕዝብ ሐገርን ለፓሪስ፣ለንደን ዋሽግተኖች ጦር ያስረክባሉ ብለዉ ዑመር፣ ኢድሪስ፣ ሙዓመርም ሆኑ ተከታዮቻቸዉ በርግጥ ሊያስቡ አይችሉም።ግን ሆነ።...more14minPlay
June 02, 2025የግንቦት 25 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባበፊላዴልፊያው የ800 እና 1,500 ሜትር የሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በማሸነፍ የግራንድ ስላም ተሸላሚ ሁናለች ። የአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያሸነፈው ፓሪ ሳን ጃርሞ ደጋፊዎች ፓሪስ ውስጥ ባስነሱት ነውጥ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች ታሰሩ ። ኦስማን ዴምቤል የሻምፒዮንስ ሊግ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ተሰይሟል ።...more10minPlay
June 02, 2025ውጥረት ውስጥ የገባው የህወሓት እና የፌዴራል መንግስቱ ግንኙነትበኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሃት) መካከል የተፈጠረው እሰጥ አገባ እየተባባሰ የሄደ መስሏል። ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን አስከፊውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በፕሪቶሪያ በተደረሰ የሰላም ስምምነት መግታት የቻሉት ሁለቱ ኃይላት ስምምነቱን አጽንተው ዘላቂ ማድረግ ግን ተስኗቸዋል።...more4minPlay
May 31, 2025ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ መሥራች ጉባኤውን በቅርቡ መቐሌ ላይ እንደሚያደርግ አስታወቀየትግራይ ሕዝብ "የተለየ መንገድ" ስለሚያስፈልገው እና አሁን በክልሉ ያለው ችግር "በነበረበት መንገድ የሚፈታ" ባለመሆኑ መቋቋሙን በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ ገለፀ። ፓርቲው ከክልል እስከ ቀበሌ አባላት በመመልመል እስከ አንድ ወር ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ በመቐለ መሥራች ጉባኤ የማካሔድ ዕቅድ አለው።...more3minPlay
May 31, 2025የጊምቢ ወረዳ ተፈናቃዮች ባለፉት ሁለት ወራት ድጋፍ እንዳላገኙ ገለፁበምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች ባለፉት ሁለት ወራት ሰብአዊ ድጋፍ እንዳላገኙ አስታውቋል፡፡ በየወሩ የ15 ኪ.ሎ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች በነፍሰ ወከፍ ይቀርብ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎቹ ከመጋቢት ወር ወዲህ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳልመጣላቸው ተናግረዋል፡፡ ዞኑ በበኩሉ በዚህ ሳምንት እርዳታ መላኩን ገልጿል።...more4minPlay
May 31, 2025ትኩረት በአፍሪቃ፤የማላዊ ነርሶች እስራኤል ሂደው እንዲሰሩ የተደረሰው ስምምነት እና የኮንጎ የቀድሞ መሪ አማፅያንን መቀላቀላቸውየማላዊ ነርሶች ወደ እስራኤል ሂደው እንዲሰሩ የሀገሪቱ መንግስት ከእስራኤል ጋር ስምምነት ፈርሟል፤ ስምነቱ በሀገሪቱ ድጋፍ እና ተቃውሞ ገጥሞታል። በሌላ በኩል በዲሞክራቲክ ኮንጎ የቀድሞው ፕሬዚዳንት የጆሴፍ ካቢላ አማፅያንን መቀላቀላቸው የሀገሪቱን ሰላም አደጋ ላይ ይጥላል በሚል ስጋት አሳድሯል።...more12minPlay
May 31, 2025ፖላንድ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨምሮ በስድስት ሀገራት በሕገ-ወጥ ስደት ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ጀመረችፖላንድ ሕገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል ኢትዮጵያ እና ኤርትራን ጨምሮ በስድስት ሀገራት ዘመቻ መጀመሯን አስታወቀች። የፖላንድ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ራዶስላው ሲኮርስኪ በኤክስ ባጋሩት ቪዲዮ በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ያቋረጠ ሰው ጥገኝነት እንደማይሰጠው ያስጠነቅቃል። በዘመቻው ሶማሊያ እና ግብጽ ጭምር መካተታቸውን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።...more0minPlay
May 31, 2025የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ የተጣለውን የጦር መሣሪያ ግዢ ማዕቀብ ለዓመት አራዘመከ15 የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት መካከል ትላንት ዓርብ በነበረው ድምጽ አሰጣጥ ዘጠኙ የውሳኔ ሐሳቡን ደግፈዋል። የውሳኔ ሐሳቡ ያገኘው የድጋፍ ድምጽ ለመጽደቅ ከሚያስፈልገው ዝቅተኛው ነው። ስድስት ሀገራት ማለትም ሩሲያ፣ ቻይና፣ አልጄሪያ፣ ሴራ ሊዮን፣ ሶማሊያ እና ፓኪስታን ድምጸ ተዓቅቦ አድርገዋል።...more0minPlay
May 30, 2025በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን እስራኤል የገቡበት ዘመቻ ሰሎሞን ሲታወስ15 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ወይም ቤተ እስራኤላዊያን በ36 ሰዓታት ውስጥ ከአዲስ አበባ እስራኤል የገቡበት ዘመቻ ሰሎሞን 34 ዓመት ሞልቶታል።ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በቀጥታ ቴላቪቭ በ35 የአውሮፕላን በረራዎች ወደ እስራኤል የገቡት ቤተ እስራኤላዊያን ዛሬ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ በጎ ድልድይ መሆናቸውም ተገልጿል።...more4minPlay
May 30, 2025በአፋር ክልል ወደ ትግራይ የሚሄዱ የጭነት መኪናዎች ኬላዎች ላይ ተዘግተዋል።ሸቀጣሸቀጥ ጭነው ወደ ትግራይ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች፥ ወደ ትግራይ እንዳይገቡ በአፋር እና አማራ ክልል በሚገኙ የፍተሻ ጣብያዎች መከልከላቸው ተገለፀ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በዚህ ክልከላ ጉዳይ ከፌደራል መንግስቱ ማብራሪያ ጠይቋል።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.