Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
June 03, 2025ብዙዎችን ለስቃይ የዳርገው ምንነቱ ያልታወቀው የሰውነት መዛልበመላው ዓለም 17 ሚሊየን ሰዎች ከዚህ ህመም ጋር በስቃይ ዘመናቸው ለመግፋት ተገደዋል። በህክምናው አጠራር ክሮኒክ ፋቲግ ሲንድሮም ይባላል። እጅግ የተወሳሰበ የጤና ችግር ሲሆን የሚያስከትለው የሰውነት መዛል ለስድስት ወራት ያህል ሊዘልቅ ይችላል።...more10minPlay
June 03, 2025«የህወሓት አመራሮች ትግራይን ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ» ሳልሳይ ወያነ ትግራይየህወሓት አመራሮች ካለፈ ጦርነት ያላገገመች ትግራይ ዳግም ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ ሲል ተቃዋሚው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ገለፀ። በሌላ በኩል በክልሉ ተደቅኖ ያለ ፖለቲካዊ እና የፀጥታ አደጋ የሚያስቀር እውነተኛ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲደረግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።...more4minPlay
June 03, 2025የጀርመኑ ቻንስለር ፍሪድሪሽ ሜርስ የአሜሪካ ጉብኝትና አንድምታዉየጀርመኑ ቻንስለር ፍሪድሪሽ ሜርስ ለጉብኝት ወደ አሜሪካ ሊጓዙ ነዉ። ይህ ጉብኝት በአሜሪካ እና በአዉሮጳ አጋሮችዋ መካከል በንግድ ቀረጥ ጭማሪ ዉዝግብ ባለበት እና በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ባለዉ ግጭት ምክንያት አዉሮጳና ዩናይትድ ስቴትስ ዉጥረት ዉስጥ በገቡበት ወቅት ነው። ከጀርመኑ ቻንስለር ከፍሪድሪሽ ሜርስ የአሜሪካ ጉብኝት ምን ይጠበቃል?...more4minPlay
June 03, 2025በአገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ኦነግ ያወጣው መግለጫፓርቲው በመግለጫዉ በአገሪቱ ለሚስተዋሉ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች መድሃኒት ይሆናል ባለዉ በምክክር አስፈላጊነት እንደሚያም እና፤ ሂደቱ ግን አካታች እና አሳታፊ ሊሆን እንደሚገባ ጠይቋል፡፡ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፈሰር መስፍን አርዓያ በምክክር ሂደቱ ያልተሳተፉ የፖለቲካ ድርጅቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።...more0minPlay
June 03, 2025ወደ ትግራይ እንዲጓዙ ፈቃድ አገኙ የተባሉት ሸቀጥ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ጉዳይለሳምንት ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ ተከልክለው የነበሩ ሸቀጥ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተደረሰ ከተባለ መግባባት በኃላ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ተፈቅዷል። ይሁንና በየግዜው የሚጣሉ ክልከላዎች በሕብረተሰቡ ላይ ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ጫናዎች እየፈጠሩ መሆኑ አስተያየት ሰጪዎች ይገልፃሉ።...more4minPlay
June 02, 2025በምዕራብ ጎንደር ዞን አብዛኛዎቹ ከተሞች ኤሌክትሪክ ተቋርጧልበአገልግሎቱ የምዕራብ ጎንደር ዞን የስርጭት፣ ኔትወርክና መሠረተ ልማት ቡድን አስተባባሪ አቶ ላቅ አያልነህ ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት በነበረው ከበድ ዝናብ ምክንያት ወደ ሱዳን የሚሄደው መስመር ጭምር ተጎድቷል፤ በምዕራብ ጎንደር የሚገኙ በርካታ ከተሞች ኃይል ተቋርጦባቸዋል፣ የጥገና ሥራዎች በባለሙያዎች እየተሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡...more4minPlay
June 02, 2025አናሌና ቤርቦክ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆኑየቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሾሙ። ቤርቦክ በዚህ ቦታ ላይ ለመወዳደር የቀረቡ ብቸኛዋ እጩ መሆናቸው ታዉቋል።...more0minPlay
June 02, 2025በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለአገራዊ ምክክር ጉባኤ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችየባለድርሻ አካላቱን የምክክር አጀንዳ ከተረከቡ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፈሰር መስፍን አርዓያ የቀረቡትን አጀንዳዎች በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበው በአገራዊ ምክክሩ የአጀንዳ አሰባሰብ ሂደት ትግራይ ክልልና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ላይ ማተኮር አበይት ቀሪ ስራዎች ናቸው ብለዋል፡፡...more4minPlay
June 02, 2025በሚልዮን የሚቆጠሩ ሙስሊም ምዕመናን ቅድስት ከተማ መካ እየገቡ ነዉሚልዮን የሚቆጠሩ ሙስሊም ምዕመናን ከዓመታዊው የሐጅ መንፈሳዊ ጉዞ በፊት ወደ ቅድስት ከተማ መካ እየገቡ ነዉ። የመካ ከተማ ባለ ባለሥልጣናት የሐጅ መንፈሳዊ ተጓዦችን ከሳውዲ አረብያ በረሃማ ሙቀት ለመጠበቅ እና ሕገወጥ ጎብኝዎችን በመከላከል ለመንፈሳዊ ተጓዦቹ ደኅንነቱ የተጠበቀ ጊዜ እንዳመቻቹ ገልፀዋል።...more0minPlay
June 02, 2025«ፈቃጅ እና አስቻይ ሁኔታዎች ባሉበት ክልል ሁሉ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይደረጋል »የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ"የፀጥታ ችግር የለም? ልንክድ አንችልም። አለ። ነገር ግን ይህንን ነገር ጊዜው በደረሰ ቁጥር ምርጫ ቦርድም አስቻይ ሁኔታ በሌለበት ሁኔታ ምርጫ አደርጋለሁ ብሎ የሚፎክርበት እና የሚገባበት ምንም ምክንያት የለም"። "የፀጥታ መኖር ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ወሳኝ ነው።» የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.