Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.
June 07, 2025ሩሲያ በዩክሬን ኻርካይቭ ከተማ ላይ በፈጸመችው ከባድ ድብደባ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ተገደሉበምሥራቃዊ ዩክሬን በምትገኘው ኻርካይቭ ከተማ ላይ ሩሲያ በድሮኖች እና ሚሳይሎች በፈጸመችው ከፍተኛ ጥቃት ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ 21 መቁሰላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። የከተማዋ ከንቲባ ኢሖር ቴሬክሖቭ በኻርካይቭ የለሊቱ ድብደባ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ “እጅግ ከባዱ” መሆኑን ገልጸዋል።...more0minPlay
June 07, 2025በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “በፖለቲካዊ እና የብሔር ልዩነት የተቀሰቀሰ ግጭት” ተባብሷል ተባለበኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “በፖለቲካዊ እና የብሔር ልዩነት ምክንያት የተቀሰቀሰ የትጥቅ ግጭት እየተባባሰ” መሔዱን በአውሮፓ ኮሚሽን ሥር የሚገኘው የሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ ርዳታ ክፍል አስታወቀ። በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ሳቢያ ከ11,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጿል።...more0minPlay
June 07, 2025በጀርመን የሀገሪቱን ድንበሮች አቋርጠው የሚመጡ ስደተኞችን የመቀበል ውሳኔ እያወዛገበ ነው።በጀርመን የአገሪቱ ድንበሮች አቋርጠው በሚገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በተመለከተ፤በጥምር መንግስቱ ውስጥ ውጥረት ነግሷል። ውጥረቱ የነገሰው የበርሊን አስተዳደር ፍርድ ቤት በፖላንድ ድንበር ላይ በተደረገው ፍተሻ የተያዙ የሶስት ሶማሊያውያን የጥገኝነት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ሕገ-ወጥ ነው ብሎ ያለፈው ሰኞ ብይን መስጠቱን ተከትሎ ነው።...more0minPlay
June 06, 2025የኢድ አል አድኻ (አረፋ) በዓል አከባበር ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ እሴትየታሪክ ተመራማሪው ዶ/ር ኢብራሂም ሙሉሸዋ አረፋ በዓለም ሙስሊሞች ዘንድ በተመሳሳይ መልኩ ቢከበርም በየአገሩ ሁሉም በአከባቢው ባህል በአብሮነት ያከብረዋል” በማለት በኢትዮጵያ ለአብነትም በስልጤና ጉራጌ አከባቢ የበዓሉ አከባበር የመተጫጫና የቤተሰብ መሰባሰቢያ ተደርጎ ስለሚወሰድ የሚፈጥረው ማህበራዊ ቁርኝትና ኢኮኖሚያዊ ትስስሩ አይናቅም ይላሉ፡፡...more3minPlay
June 06, 2025በሠራተኞች ላይ ሥጋት ፈጥሮ የነበረው የአደጋ ሥጋት ሕግ ማሻሻያ ተደረገበትበረቂቁ "የመንግሥት እና የግል ድርጅት ተቀጣሪ ሰራተኞች ከሚከፈላቸው የተጣራ ደመወዝ ላይ የሚታሰብ" የሚለው ሥጋት ፈጥሮ የነበረው የገቢ ምንጭ እንዲነሳ ተደርጓል። የም/ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ፣ይህ የተደረገው«የተጣራ ደሞዝ ላይ የሚቆረጥ መዋጮ ሠራተኞች ላይ ተደራራቢ የወጪ ጫና እንዳያሳድር ነው» ብለዋ"።...more4minPlay
June 06, 2025የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢው ምን አሉ?ሰብሳቢው አቶ ሰለሞን አየለ ወቅታዊ ሀገራዊ የጸጥታ እና የደህንነት ሁኔታ ከሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ ትግል አንጻር እንዴት እንደሚታይ ፤ በቀጣዩ ዓመት ሊካሄድ ቀጠሮ ስለተያዘለት የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ምርጫ እና አስቻይ ሁኔታዎች በስፋት ዳስሰዋል።...more15minPlay
June 06, 2025የጀርመን መራኄ መንግሥት የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት ፋይዳከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ያካሄዱት ውይይት ገንቢ እንደነበር የተናገሩት ሜርስ አስተዳደራቸውንም ለውይይት ዝግ ያልሆነ የሚያዳምጥና የሌሎችን አመለካከት ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ሲሉ አወድሰዋል።እንደ ዩክሬኑና የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት አታካራ ውስጥ ሳይገቡ ከትራምፕ ጋር መነጋገራቸው ለሜርስ እፎይታን ያስገኘም መስሏል።...more6minPlay
June 06, 20251446ኛው የኢድ አል አደሀ በዓልሕዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን 1446ኛው የኢድ አል አድሀ በዓል ሲያከበር የተፈናቀሉና ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን በመደገፍ ጭምር እንዲሆን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠየቀ ። በዓሉ ነገ በመላው የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ይከበራል ።...more4minPlay
June 05, 2025ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር «የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባችም» - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስከኤርትራ በኩል «የማይመቹ እና የሚጎረብጡ» ነገሮች ቢሩም ኢትዮጵያ የሁለቱን ሀገራት «የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላለመጉዳት» ጉዳዩን በትዕግስት እያለፈችው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ ተናገሩ ። «ኢትዮጵያ ከጌረቤቶቿ ተነጥላለች» በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም ያንን መቀበል እንደሚቸግር ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል ።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,912 episodes available.