Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.
July 07, 2026የጀርመን ቀኝ ጽንፈኛ ፓርቲ አማራጭ ለጀርመን የመንግሥት ኃላፊነትን የመውሰድ ዝግጅትና ተግዳሮቶቹየሕግ ባለሞያ እና የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ AfD ከሚያስመዘገበው ውጤት በመነሳት ህዝባዊ መሠረት አለው ማለት እንደሚቻል ገልጸው፣ በዛክሰን አንሀልት መስከረም ላይ በሚደረገው ምርጫ ፓርቲው እንደተጠበቀው ካሸነፈ በፌደራል መንግሥትነት ሃላፊነት ለመውሰድ የሚያበቃ የመጀመሪያው ደረጃ ሊሆን ይችላል።...more0minPlay
July 07, 2026«በትግራይ አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላው ተጠናክሮ ቀጥሏል»« ከአንድ ወር በፊት አስገዳጅ ምልመላ እየተካሄደ እንደሆነ በማስረጃ አስደግፈን ሪፖርት ማቅረባችን ይታወሳል። ከዚያ በኃላ ባለው ጊዜም ክትትል ስናደርግ ነበር። የክትታላችን ውጤት እንደሚያመላክተው በትግራይ አስገጅ ወታደራዊ ምልመላው ተጠናክሮ መቀጠሉን ያሳያል።»...more0minPlay
July 07, 2026የተመድ፤ በሱዳን የተፈፀሙ በደሎች በአስቸኳይ እንዲመረመሩ አዘዘየተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ም/ቤት በሱዳን ኤል-ኦቤይድ ከተማ ውስጥ የተፈፀሙ ጥሰቶችና በደሎች ላይ "አፋጣኝ ምርመራ" እንዲደረግ ጠየቀ። ምክር ቤቱ በቀጣይ "ከፍተኛ ጭካኔዎች" ሊከሰቱ ይችላሉ ሲልም አስጠንቅቋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አስጠንቅቋል። ም/ቤቱ ቀዳሚዉ ጉዳይ በሱዳን የዉጭ ጣልቃ ገብነትን መቆጣጠር መሆኑን አጾኖት ሰቷል።...more5minPlay
July 07, 2026የእምቦጭን መስፋፋት በዘላቂነት ለመግታት የተመራማሪዎች ምክረ ሀሳብበኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ላይ የተንሰራፋው የውኃ ላይ ተክል ዛሬም ይዞታውን እያስፋፋ መዝለቁን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ይህን የውኃ ላይ አረም ለማስገድ ላለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት ተደጋጋሚ ኅብረተሰቡን ያሳተፉ ዘመቻዎች ተደርገዋል። ዛሬም ግን እምቦጭ ጣና ላይ ተንደላቆ መባዛቱን ቀጥሏል። ዘላቂ መፍትሄ እንዴት ጠፋ?...more0minPlay
July 06, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃነት 250ኛ ዓመት ዝክርና ዉዝግብበተለይ ሚያዚያ 1775 ሌክሲግተንና እና ኮንኮርድ በተባሉት ከተማና አካባቢዎች «የአሜሪካ አብዮት ጦርነት» የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ዉጊያ አላባራም።በጦርነቱ መሐል «ሁለተኛዉ አሐጉራዊ ጉባኤ» የተባለዉ ሥብሰባ ተሳታፊዎች ኢስትሩም በተባለዉ የፊላደፊያ ግዛት አስተዳደር አዳራሽ ዉስጥ ተሰበሰቡ...more0minPlay
July 06, 2026የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፍጻሜውን ሲያገኝ የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚዎችን እየለየ ነውበሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በተደረጉ የተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን ድል ቀንቷቸዋል፡፡ የፕሪፎንቴይን ክላሲክ -ዩጂን ዳይመንድ ሊግ እና በአሜሪካው የፒችትሪ የጎዳና ሩጫ ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል ። በአሜሪካዋ ዩጂን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ በሴቶች የሁለት ማይል ርቀት ብርቱ ፉክክር የተስተዋለበት ነበር።...more0minPlay
July 06, 2026የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ያልተቀመጠዉ የትግራይ ክልል ቅሬታየትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ባለመስማማት በራሱ አሠራር በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈተና አውጥቶ ተማሪዎችን ሊፈትን መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በትግራይ ክልል ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበው ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ 15 ሺህ 349 ተፈታኝ ተማሪዎች ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ ፈተናቸውን እንዲወስዱ ዕቅድ ተይዞ ነበር።...more0minPlay
July 06, 2026የፀጥታ ሥጋት ያጋጠመው የጋሞ ዞን ዛይሴ አካባቢበደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋሞ ዞን “ በመንግሥት የፀጥታ አባላት ተከፈተ “ በተባለ ተኩስ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት አባል ገልጸዋል ፡፡ የፀጥታ አባላቱ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ተኩስ የከፈቱት በዞኑ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዛይሴ ኤልቦ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡...more4minPlay
July 06, 2026በአፍሪቃ ቀንድ እየጨመረ የመጣው የጦርነት ስጋትአፍሪቃ ቀንድ እና ቀይ ባህር ቀጣና ለውስብስብ እና የግጭት ሁኔታዎች ከምን ጊዜውም በላይ እየተጋለጠ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዋና ኢታማዦር ሹም ጽምዶ ያሉት “በውጪ ኃይል” አስተባባሪነት የተቋቋሙ የታጣቂዎች ጥምረት ኢትዮጵያ ውስጥ መረጋጋት እንዳይኖር እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡...more4minPlay
July 05, 2026እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ?በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.