Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.
July 10, 2026የኢሰመኮ የአምስት ዓመት ዕቅድ የመብት ጥሰቶችን ይቀንስ ይሆን?ኢትዮጵያ ውስጥ «ግጭት፣ የፀጥታ ችግርና መፈናቀል፣ ሕገ ወጥ የሲቪል ሰዎች ግድያ እና የአካል ጉዳት፣ የዘፈቀደ እና የተራዘመ እስር» የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሥጋት ሆነው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጠ። በሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ የሚሠራ አንድ ሀገር በቀል ሲቪክ ድርጅት የኢሰመኮን ሥጋት እንደሚጋራ ጠቅሷል ።...more5minPlay
July 10, 2026በአርሲ አሰኮ በግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የድጋፍ ጥያቄበኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ግንቦት 23 እና 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በርዳታ አቅርቦቶች መቋረጥ መቸገራቸውን ገለጹ። ተፈናቃዮቹ በጥቃቱ ወቅት በደረሰባቸው የቤት ቃጠሎና የንብረት ውድመት ወደ መኖሪያቸው ቀየያቸው ለመመለስም ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል ፡፡...more5minPlay
July 10, 2026በእሥር ላይ ስለሚገኙ ፖለቲከኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰጡት ፍንጭየኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በልዩ ልዩ ፖለትካዊ ምክንያቶች በእሥር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከእሥር ሊለቀቁ የሚችሉበት ዕድል ስለመኖሩ ፍንጭ ሰጡ። መንግሥታቸው "የሃይማኖት አባቶችን እና ትልልቅ ሰዎችን" ተጠቅሞ "በተቻለ መጠን በእሥር ላይ ያሉ ሰዎችን ለመፍታት" ፍላጎት እንዳለው ጠቁመዋል ።...more5minPlay
July 10, 2026አንድነት ላይ ያተኮረው የኔቶ ጉባኤበዚህ ሳምንት ለሁለት ቀናት አንካራ ቱርክዬ ላይ የተካሄደው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ጉባኤ የአባላቱ አንድነት አሁንም እንዳለ መሆኑን ለማሳየት ያለመ እንደነበር ነው ተንታኞች የሚናገሩት።...more6minPlay
July 09, 2026ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የመረጃ ሰጪ መተግበሪያዎች የንባብ ባህልን እያዳከሙ ይሆን?ብዙዎቻችን የመረጃ ሰጪ መተግበሪያዎችን ወይንም አፕሊኬሽን ልንጠቀም እንችል ይሆናል ፡፡ በተለይ ወጣቶች እንደቻት ጂፒቲ የመሳሰሉ መተግበሪያዎችን አዘውትረው ይጠቀማሉ። ነገር ግን አጠቃቀም ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነስ ይስተዋላል ፡፡ የመረጃ ሰጪ መተግበሪያዎች የንባብ ባህልን እያዳከሙ ይሆን ?...more13minPlay
July 09, 2026«በትግራይ ባለሥልጣናት የግዴታ ዉትድርና እየተፈፀመ ነዉ» ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችየትግራይ ክልል ባለሥልጣናት የ15 ዓመት አዳጊዎችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን እያፈኑ በግዳጅ ለውትድርና እያስገደዱ እንደሚገኙ ዓለምአቀፉ ሰብአዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት ሒውማን ራይት ዎች ወነጀለ። ድርጅቱ የአፍሪቃ ህብረት፣ የተመድ እና የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ እና ክልላዊ አጋሮች በትግራይ ያሉ ባለስልጣናት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቋል።...more0minPlay
July 09, 2026ግብርና በቤኒሻንጉል ጉሙዝአቶ አወቀ ኃይሉ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ነዋሪ ሲሆን በ2013 ዓ፣ም ተፈናቅለው የነበሩና ወደቀያቸው ከተመለሱት መካከል ናቸው፡፡ በወረዳው የግብርና ስራ ከባለፈው ዓመት በተሻለ መልኩ አርሶ አደሩ ስራውን መቀጠሉን ገልጸው በወረዳው የጸጥታ ስጋት በሚታይባቸው ሁለት ቀበሌዎች ግን በተሟላ መልኩ አርሶ አደሩ ወደ ስራ አለመግባቱን ጠቁመዋል ፡፡...more0minPlay
July 09, 2026የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ምንያህል ማህበራዊ ጠቀሜታ እያስገኘ ይሆን ?የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የሚያዘጋጀው የወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በየዓመቱ በክረምት ወራት የሚካሄድ አገር አቀፍ ክንውን ነው ፡፡ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ 5 "በሚል መሪ ቃል ዘንድሮው ለአምስተኛ ጊዜ የሚካሄደው ይሄው አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሐግብሩን በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል ።...more0minPlay
July 09, 2026''ኸርት አታክ ኢትዮጵያ'' በኢትዮጵያ ከ200 ለሚበልጡ ሰዎች ነጻ የልብ ህክምና ያደርጋል''ኸርት አታክ ኢትዮጵያ''በዘንድሮው አምስተኛ ዙር ነጻ የልብ ህክምና 60 የልብ ህመምተኞችን በማከም ተልእኮውን የጀመረ ሲሆን፣ ከነዚም መኻል አንዳንዶቹ ለዓመታት የህይወት አድን ህክምና ለማግኘት ሲጠብቁ መቆየታቸው ተመልክቷል። የህክምና ቡድኑ፣በዚህኛው አምስተኛ ተልዕኮው በተለይ በልብ ህመም ለሚሰቃዩ ህጻናት ለመጀመሪያ ጊዜ ህክምና ያካሄዳል።...more0minPlay
July 09, 2026ጀርመን ወታደራዊ ኃይሏን ማጠናከር መጀመሯጀርመን የመከላከያ ዘርፏን ለማጠናከርና ለማዘመን መነሳቷን እያሳየች ነው። የሀገሪቱ መራኄ መንግሥት ፍሪደሪሽ ሜርስ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር እንደ አዲስ የመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ግዢ ስምምነት አድርገዋል። በርሊን ከትራምፕ አስቀድመው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ከነበሩት ከጆ ባይደን ጋር ያደረገችው ስምምነት በትራምፕ ተሰርዞ ነበር።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.