Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.
July 13, 2026በትግራይ ክልል ይፈጸማሉ ስላላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የኢሰመጉ ጥሪየኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ይገኛል ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ጠየቀ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ 18 ዓመት ያልሞላቸው ሕፃናትን፣ ወጣቶችን እና የአካባቢው ነዋሪዎችን በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ማስገባት መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት መርሆዎችን የሚጥስ ነው ብሏል።...more0minPlay
July 13, 2026የአዲስ አበባ ጎጃም መንገድ ደህንነት እና ፀጥታ አሳሳቢነትጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህምድ ከአዲስ አበባ ጎጃም መስመር “ሰዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው መሥራት የማይችሉበት ደረጃ” ላይ የደረሱበትን ከባድ የጸጥታ ስጋት ኮነኑ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብረ ማርቆስ ከተማ ተገኝተው አዲስ አውሮፕላን ማረፊያን ሲመርቁ፤ ባደረጉት ንግግር “አካባቢዉ ላይ ያለዉን የፀጥታ ስጋት ጥዩፍና የማይገባ ብለዉታል።...more0minPlay
July 12, 2026ሃገራዊ ምክክር የመጨረሻው ምዕራፍ ከተስፋ ባሻገርኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ለማድረግ ጥቂት ቀናት ቀርተዋታል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በምክክሩ ላይ ይሳተፋሉ የተባሉ ከአራት ሺ በላይ ተወያዮች አዲስ አበባ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ውጪ የምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ከሶስት ዓመታት በላይ እንደወሰደበት ታይቷል።...more0minPlay
July 11, 2026ደቡብ አፍሪቃ፤ ስደተኛ ጠል ጥቃቶችን ሸሽተዉ የወጡ አፍሪቃዉያንበደቡብ አፍሪቃ የተከሰተዉን የመጤ ጥላቻ ጥቃት ተከትሎ ብዙዎች ህይወታቸውን እንደገና ለመገንባት እየታገሉ ቢሆንም፤ በአፍሪቃ ውስጥ ፍልሰትን የሚያባብሱ ጥልቅ የአስተዳደር እና የኢኮኖሚ ችግሮች መኖራቸዉን የሚጠቁም ነዉ። በደቡብ አፍሪቃ ውጭ ዜጋ እስከሆንክ ድረስ እዚያ እንድትኖር አይፈልጉም።...more0minPlay
July 11, 2026አፍሪቃን ለድርቅ እና ለጎርፍ የሚያጋልጠዉ የኤል ኒኞየኤል ኒኞ የአየር ንብረት ክስተት በዚህ ዓመት መጨረሻ በአፍሪቃ ክፍሎች ድርቅ፣ ጎርፍ እና መፈናቀል ሊያስከትል እንደሚችል እየተገለፀ ነዉ። መንግስታት ለዚህ ዝግጁ ይሆኑ? ተጋላጭ ሃገራት ፤ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ዩጋንዳ እና ዚምባብዌ መሆናቸዉ ተነግሯል።...more0minPlay
July 11, 2026አዲስ አበባ ያሉ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪዎች ከመኝታ ክፍል አገልግሎት 5 በመቶ ግብር ተጣለባቸውአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ከ"የመኝታ ክፍል አገልግሎት"ላይ የ5 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ደንብ ወጥቷል። ደንቡ ሰኔ ላይ በአዲስ ነጋሪት ጋዜጣ የታተመ ሲሆን፤ የከተማዋን ገቢ አሰባሰብ ለማሻሻል እና ሕጋዊነትን ለማስፈን መሆኑ ተገልጿል።ደንቡ በግጭትና ጦርነት ምክንያት ፈተና ለተጋረጠበት ለዚህ ዘርፍ ስጋት ፈጥሯል።...more0minPlay
July 11, 2026የመሪዎች የስልጣን ገደብ ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር መጠናከር ያለው ፋይዳኢትዮጵያ እያካሄደች በምትገኘው የአገራዊ ምክከር ውስጥ የህግመንግስት ማሻሻያ ሃሳብ ሚቀርብ ከሆነ አንዱ በማሻሻያው እንዲካተት ሃሳብ ከሚቀርብባቸው ጉዳዮች መካከል የመሪዎችን የስልጣን ዘመን መወሰን አንዱ መሆኑን አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡ለመሆኑ የመሪዎችን የስልጣን ዘመን መወሰን ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር መጠናከር ምን ፋይዳ ይኖረው ይሆን?...more4minPlay
July 11, 2026አሜሪካ ፤ኢራን የሆርሙዝ ጥቃቶችን ለማስቆም በይፋ ቃል እንድትገባ መፈለጓን ባለስልጣናት ገለፁዋሽንግተን ቴህራን በሆርሙዝ ስትራቴጂካዊ የባህርት ወሽመጥ ላይ በሚጓዙ መርከቦች ላይ የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች ለማስቆም በይፋ ቃል እንድትገባ መፈለጓን ዘገባዎች አመልክተዋል። በሌላ በኩል ዶናልድ ትራምፕ ኢራን እሳቸውን ለመግደል ከሞከረች ሀገሪቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚያወድሟት ዝተዋል።1000 ሚሳይሎች ወደ ኢራን አነጣጥረው ተቀምጠዋል። ሲሉም ዝተዋል።...more0minPlay
July 10, 2026ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቀሳ የህወሓት ምላሽሕወሓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኤርትራና ሱዳን ጋር በመስራት ያቀረቡበትን ክስ አጣጣለ ። ፓርቲው ምላሹን የሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማጠቃለያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ሕወሓት፣ ኤርትራ እና ሱዳንን የኢትዮጵያን መንግስት ለመዋጋት ተጣምረዋል በማለት በጠንካራው መተቸታቸውን ተከትሎ ነው፡፡...more0minPlay
July 10, 2026በአፍሪቃ የሚካሄዱ ምርጫዎች ዳያስፖራውን ማሳተፍ እንደለባቸው ተገለፀየዳያስፖራ አባላት የብሔራዊ ምርጫ ተሳትፎ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ያለበት ደረጃ ተመሳሳይ አለመኾኑን የገለፀው የአፍሪካ ኀብረት፣ አባል ሃገራት ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቧል። በርካታ ሃገራት በተለያዩ የውጭ ሃገራት የሚገኙ ዜጎቻቸው በምርጫ እንዲሳተፉ የሚያስችሉ የሕግ ማሻሻያዎች ማድረጋቸውን ገልፀዋል።...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.