Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.
July 14, 2026ረቡዕ ስለሚጀረው የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ኮሚሽኑ ምን አለ?የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚመራው የአገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አራት ሺህ ጉባኤተኞች አዲስ አበባ መክተማቸው ተመላክቷል፡፡ ስለ ጉባኤው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፈሰር መስፍን ዓርዓያን ዶይቼ ቬለ ዛሬ አነጋግሯል ።...more0minPlay
July 14, 2026ፈረንሣይ፥ ስፔን፥ አርጀንቲናና እንግሊዝ በግማሽ ፍጻሜ፣ አጋጣሚ ወይንስ?ለግማሽ ፍጻሜው ካለፉት አራት አገራት መካከል ዛሬ ማታ የሚጫወቱት ፈረንሣይ እና ጠንካራ ተፎካካሪ ኾና ብቅ ያለችው ስፔን ናቸው ።ፈረንሣይ ከስፔን፤ እንግሊዝ ከአርጀንቲና ለግማሽ ፍጻሜ መገናኘታቸው ብዙዎች የአጋጣሚ አይደለም የፊፋ ረጅም እጅ አለበት ይላሉ፦ ቃለ መጠይቁን በማገናኛው ማድመጥ ይቻላል ።...more0minPlay
July 14, 2026ረቡዕ ስለሚጀመረው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሰዎች ምን ይላሉ?የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለአራት ዓመታት አጀንዳ ሲያሰባስብ ቆይቶ ነገ ሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ዋናውን ጉባኤውን ይጀምራል ። በዚህ ጉባኤ ከትግራይ ክልል በስተቀር ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ 4 ሺህ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ ገብተዋል ተብሏል። የነዋሪዎች አስተያየት ።...more0minPlay
July 14, 2026በአማራ ክልል የተፈናቃዮች የድረሱልን ጥሪበአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ውስጥ ከስድስት ዓመታት በላይ የቆዩ ከ60 ሺህ በላይ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ የረድኤት ድርጅቶች ፕሮጀክቶቻቸውን ዘግተው በመውጣታቸው የመንግሥት ርዳታም የተቆራረጠ በመሆኑ ምክንያት ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና ሥጋት መጋለጣቸውን ገልጸዋል ።...more0minPlay
July 14, 2026የጊምቢ- ኖሌካባ እና ሜቱ መንገድ ግንባታ መጓተትከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት በምዕራብ ወለጋ ዞን ከጊምቢ አንስቶ እስከ ኢሉ አባቦር ዞን ሜቱ ከተማን ያገናኛል የተባለለት የመንገድ ግንባታ ሳይጠናቀቅ ለምን ቀረ? የመንገዱ የመጀርያ ምዕራፍ ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ የ70 ኪሜር ርቀቱን በአራት ዓመታት ለማጠናቀቅ ታቅዶ እንደበር ይነገራል ።...more0minPlay
July 14, 2026የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አገራዊ ውይይት በጅግጅጋየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ ጅግጅጋ ከተማ ሀገራዊ ውይይት እያካሄደ ነው። "ሰብአዊ መብት እና የሰላም ግንባታ" የሚል መሪ ሀሳብ ባለው የጅግጅጋ ውይይት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰብዓዊ መብቶች አማካሪ ምክር ቤት መቋቋሙ ተገልጿል ።...more0minPlay
July 14, 2026ዛሬ (ማክሰኞ) ምሽት ዳላስ ላይ ፤ ፈረንሳይ እና ምባፔ ወይስ ስፔይን እና ያማል ?የአሜሪካው የዳላስ ስታዲየም የወቅቱን የአውሮጳ እና የዓለም እግር ኳስ ከዋክብትን ባቀፉ ሃገራት መካከል የሚደረገውን ፍልሚያ ያስተናግዳል። መላው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው የ2026ቱ ፊፋ የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በስፔን እና በፈረንሳይ መካከል ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ ይደረጋል።...more0minPlay
July 13, 2026የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ማን ወደ ድርድር ይመልሳቸዋል?የአዲስ አበባና የመቐለ ባለሥልጣናት ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ቢሰጡም በመካከላቸው ያለው እሰጥ አገባ ከፍተኛ ዕልቂትና ብርቱ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዳያገረሽ የሚያሠጋ ነው። በጥቅምት 2013 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ወደ ድርድር ለመግፋት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አስፈልጓል።...more12minPlay
July 13, 2026የሐምሌ 6 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባየዓለም ዋንጫ፦ ከአሜሪካ እስከ ሶማሊያ፤ ከግብጽ እስከ አርጀንቲና፤ ከሞሮኮ እስከ ፈረንሣይ፥ መላ ዓለምን ሲያስደምም፣ ሲያስቦርቅና እንባ ሲያራጭ ቆይቶ ወደ ፍጻሜው እየተጠጋ ነው ። የኢትዮጵያ አዳጊ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በመጨረሻዎቹ ሰዓቶች ለዓለም ዋንጫ የነበረው ዕድል ለምን መከነ? ቃለ-መጠይቁንና ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ማገናኛው ያድምጡ።...more0minPlay
July 13, 2026የግዳጅ ዉትድርናን በመሸሽ ክልሉን እየለቀቁ ያሉት የትግራይ ወጣቶችበትግራይ ክልል በሚገኙ እንደ ራያ አላማጣ፣ ኮረም እና ኦፍላ ባሉ አካባቢዎች የተጀመረውን የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት አፈሳ በመሸሽ በርካታ ወጣቶች በእግራቸውና በተለያዩ አደገኛ መንገዶች ወደ አማራ ክልል ቆቦ ከተማ እየገቡ መሆኑን ገለጹ። ወጣቶቹ አፈሳዉን በመሸሽ እስከ 80 ኪሜ በእግር ተጉዘዉ ቆቦ ከተማ የገቡት፤ አንዳንዶት ተይዘዉ ታስረዋል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.