Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.
July 17, 2026የወጣቶች የፈጠራ ስራ እና ተቀባይነታቸውበነቀምቴ ከተማ በፈጠራ ስራው ትልቅ ተቀባይነት ያገኘው ወጣት ሚካኤል መስፍን በ2007 ዓ.ም በሳይንስና ቴክኖሎጂ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል፡፡ በወቅቱ ሁለት ሰዎችን መሸከም የሚችል ሳይክል ከወዳደቁ ብረታ ብረቶች ሰርቶ ለሽልማት በቅቷል።በመቀጠል የብሎኬት ስራን የሚያዘመን ማሽኖችን በመስራት በከተማው ትልቅ ተቀባይነት አግኝተዋል፡...more10minPlay
July 17, 2026በአሜሪካ ምርጫ ቻይና ጣልቃ ገብታለች ያሉት ትራምፕየዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ቻይና በአሜሪካ ምርጫዎች ላይ ጣልቃ ገብታለች በሚል የቀረበውን ክስ በተመለከተ አዲስ ምርመራ እንዲደረግ አዘዙ። ትራምፕ ይህን ያሉት ትንንት ምሽት ለአሜሪካ ህዝብ ባደረጉት ንግግር ነዉ። የትራምፕ የስልጣናቸዉ አጋማሽ የምክር ቤት የሟሟያ ምርጫ ሊካሄድ የቀረዉ ሁለት ወራት ግድም ነዉ።...more5minPlay
July 17, 2026በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሰሜን ኢትዮጵያ ጉብኝቶችበኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ሀገራቸው በትግራይ ክልል ለሰላም፣ ለመረጋጋት እና ለሰብአዊ ማገገም ያላትን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ መቀሌ መጓዛቸው ሲነገር፣ ጎንደር ላይ ደግሞ ስለ ሰላም ተስፋዎች እና ለኢትዮጵያ እና አሜሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ስለሚኖሩ ዕድሎች ስለመምከራቸው ተገልጿል።...more0minPlay
July 17, 2026በትግራይ የሰላምና ለውጥ ም/ቤት በአዲስ አበባ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ምበትግራይ ክልል እየተፈጸመ ነው የተባለውን “የወጣቶች አፈሳ” የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ሊካሄድ ነዉ። አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በትግራይ ክልል “አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን” በሚል መርህ ለፌዴራል መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ ለማቅረብ የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡...more0minPlay
July 17, 2026በጊምቢ ወደ ቀያቸው የተመለሱ ዜጎች ቅሬታበምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ከዚህ በፊት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ገምሱ ወደ ግብርና ስራ መግባታቸውን የገለጹ። ሲሆን መኖሪያ ቤታቸው የወደመደመባቸው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ደግሞ ለስምንት ወራት ያህል ሰብአዊ ድጋፍ እንዳላገኙ ተናግረዋል። ቤታቸው የወደመባቸው ሰዎች አሁንም መጠለያ ዉስጥ ናቸዉ ሰብአዊ ድጋፍ የላቸዉም፡፡...more0minPlay
July 17, 2026በአማራ ክልል በሴቶች ላይ የሚደርሰው ወሲባዊ አካላዊና ጥቃት ተባብሷል ተባለበአማራ ክልል በሴቶች ላይ የሚደርሰው ወሲባዊ አካላዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቃት አስከፊ መሆኑ ተገለጸ። በተያዘው የበጀት ዓመት ብቻ ከ17 ሺህ በላይ ሴቶች የተለያዩ ጥቃቶች ሰለባ መሆናቸውን የክልሉ የሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታዉቋል። ለጥቃቱ መባባስም በታጣቂ ኃይሎች መካከል ያለዉ ግጭት ነዉ ተብሎል።...more0minPlay
July 16, 2026በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው መጀመር፣ አካሄድ እና ውጤቱ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየትየምክክር ጉባኤው ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅምና መፍትሔ ያመነጫል የሚል አቋም ካሳዩ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አብን፣ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲና ኢዜማ ይገኙበታል። የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኦፌኮ ከምክክሩ ሀገራዊ መፍትሔ ይገኛል የሚል እምነት እንደሌለው ደጋግሞ አስታውቀል። ኢሕአፓ "አግላይ ምክክር ሳይሆን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት ይቅደም" ሲል ተችቷል።...more5minPlay
July 16, 2026ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበችበት 61ኛዉ ዓለም አቀፉ ቬኒስ ቢናሌበጣሊያን ቬኒስያ ከተማ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደዉና አንጋፋና ግዙፉ ዓለምአቀፍ የሥነ-ጥበብና የባህል መድረክ ለ61ኛ ጊዜ እየተካሄደ ነዉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 አፍሪቃ ሃገራት ተካፋይ ናቸዉ። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በቀረበችበት በዚህ መድረክ፤ ሠዓሊ ተገኔ ኩንቢ ሥራዎቹን አቅርቧል። መድረኩ « Shapes of Silence» በሚል ስያሜን ይዟል።...more0minPlay
July 16, 2026የእንግሊዝና የአርጀንቲና የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ እና የፍጻሜው ግጥሚያበትናንቱ ጨዋታ የእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ የማንሳት ህልም ህልም ሆኖ ቀርቷል። በጨዋታው እንግሊዝ የመጀመሪያውን ግብ ብታስቆጥር ወደ ኋላ ላይ ጠንካራ እንቅስቃሴ ያሳየው የአርጀንቲና ቡድን ከመሸ አከታትሎ ባገባቸው ሁለት ግቦች የበላይነቱን ተቀዳጅቷል።...more0minPlay
July 16, 2026የኢትዮጵያ የወደብና የቀይ ባህር ወሰን ጥያቄየዲፕሎማሲ ባለሙያው እንዳሉት ከውስጥ ጠንካራ መሆን በውጭም ዲፕሎማሲን ያጠናክራል፡፡ “ዲፕሎማሲ ሰጥቶ መቀበል ነው” ብለዋል። የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ተንታኝ አብዱራሃማን ሰይድ የኢትዮጵያ መንግስታት በቀይ ባህር ባለቤትነት ላይ የሚያቀርቡትን ጠንከር ያለ ጥያቄ «በኢትዮጵያ እና ጎረቤቶቿ መካከል ጦርነት የሚፈጥር» ብለውታል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,862 episodes available.