Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.
July 04, 2026ጠቅላይ ሚንስትሩ በአርባምንጭ የኮንፈረንስ ሪዞርት ምረቃ ላይ ምን አሉ?በአርባ ምንጭ ሪዞርት የመረቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “አላስፈላጊ ሽኩቻ ከልማት እንዳያስቀረን” ሲሉ ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቱሪዝም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ኹነኛ ምሰሶ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸው በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የቱሪዝም ባለሙያ ግን የጸጥታ ችግሮችን በማስወገድ ሰላም ማስፈን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።...more0minPlay
July 04, 2026የውጪ ዜጎች የሚሳቀቁባት ደቡብ አፍሪቃደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የውጭ ዜጎች በሰቀቀን መኖር ከጀመሩ ሰነበቱ። ኢትዮጵያውያን ንብረቶቻቸው ለዘረፋና ጥቃት መጋለጣቸውን ይናገራሉ።...more0minPlay
July 04, 2026የኬንያው ጄን ዚ ንቅናቄ ሁለተኛ ዓመትሰኔ 18 ማለትም በጎርጎሪዮሳዊው የዘመን ቀመር ሰኔ 25 ለበርካታ የኬንያ ወጣቶች ተራ ቀን መሆኑ ከቀረ ሁለት ዓመት ተቆጠረ። የዛሬ ሁለት ዓመት ጀነሬሽን ዜድ የተሰኘው ንቅናቄ የኬንያን የፖለቲካ ገጽታ ቀይሯል።...more0minPlay
July 04, 2026በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ የኢሰመኮ መግለጫበትግራይ ክልል “በግዳጅ ከሚታፈሱ ሰዎች መካከል በአብዛኛው እድሜያችዉ ከ18 ዓመት በታች መሆናቸዉን” እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ። “ሕፃናትንና ሌሎች ለመብቶች ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን በግዳጅ ለወታደራዊ ምልመላ ወይም ለጦርነት ማሰማራት” ሕገ መንግሥቱንና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን እንደሚጥስ ተችቷል።...more0minPlay
July 04, 2026የሆሮ ጉዱሩ አሙሩ ወረዳ ጥቃት ተጎጂዎች ስጋትበኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በአገምሳ ከተማ እና ዙሪያው ባሉ ቀበሌዎች ላይ ሰኔ 23 የተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት በነዋሪው ላይ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል። ልጃቸው የተገደለባቸው አባት ጥቃት በተፈጸመበት ቀን የቤት እንስሳትን ጨምሮ የንብረት ዘረፋ መፈጸሙን ተናግረዋል።...more0minPlay
July 04, 2026ኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ የስድስት ቀናት ህዝባዊ የሽኝት ሥነ ስርዓት በይፋ ጀመረችኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ቀናት የሚዘልቅ ህዝባዊ የሀዘን ሥነ ሥርዓት በይፋ መጀመሯን የሀገሪቱ የመንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።ካሜኒ በጎርጎሪያኑ የካቲት 28 ቀን 2026 ዓ ም ቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ በተደረገ የጋራ የአየር ጥቃት ነበር የተገደሉት።...more0minPlay
July 03, 2026እቅዱን አሳክቷል የተባለው የኢትዮጵያ የቡና ገቢአገሪቱ በበጀት ዓመቱ ወደ ውጪ ገቢያ ለመላክ ያቀደችው የቡና መጠን ሳይሳካ የታለመው ገቢ እንዴት ግቡን ሊመታ ቻለ ተብለው የተጠየቁት የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማኅበር ዋና ሥ/አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ “የቡና የዓለም አቀፍ ዋጋው ምንም እንኳ በመሀል እየወረደ የነበረ ቢሆንም በአንጻራዊነት ጥሩ ስለነበር የታቀደውን ገቢ ማግኘት ተችሏል” ብለዋል፡፡...more5minPlay
July 03, 2026በድሬደዋ የህፃናት ተማሪዎች ምገባ በተደራጃ መንገድ ማከናወን ያስችላል የተባለ ፕሮጀክት ተጀመረአቶ ሱልጣን "ከአስተዳደሩ አጠቃላይ ገቢ ሶስት በመቶው ለዚህ ዓላማ እንዲውል" መወሰኑን ጠቁመዋል። ሁሉም ህብረተሰብ በዚህ ረገድ የድርሻውን የሚያበርክትበት የአሰራር አቅጣጫ መቀየሱን አስረድተዋል። በመስተዳድሩ ለተማሪዎች ምገባ የተሰናዳው የማብሰያ ምዕከል እና ግብዓት የሚያመርተው የእርሻ ስራ መጀመሩንም አብራርተዋል ።...more4minPlay
July 03, 2026በአሜሪካ የትግራይ ማኅበረሰብ አባላት፣ስለክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ የሰጡት አስተያየትከሲያትል ያነጋገርነው እና የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት የሚከታተለው ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ በውይይት መፍትሔ ይገኝለታል የሚል እምነት የለውም። ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ፣ፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ አለበት ባይ ነው ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ።...more4minPlay
July 03, 2026የኢራን ልዕላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አስከሬን ሽኝትበአያቶላህ አሊ ኻሚኒ አስከሬን ሽኝት ሥነ-ስርዓት ላይ ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎች እንዲሁም ከ100 በላይ ሀገራት ተወካዮች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከመካከላቸው የሩስያ እና የቻይና ተወካዮች እንደሚገኙ ተመልክቷል ። የኢራቅ የአርሜንያ እና የፖኪስታን ፖለቲከኞች በሽኝት ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ቴህራን ገብተዋል።...more6minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,863 episodes available.