Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
July 02, 2026ሴኔጋል እና ኮንጎ ባለቀ ሰዓት ምን አፍረከረካቸው?ለዓለም ዋንጫ አፍሪቃን ከወከሉ 10 አገራት ስምንቱ ወደ ጥሎ ማለፍ መሻገር ተሳክቶላቸው ነበር ። ትናንት በነበረው ግጥሚያ ግን ሴኔጋል እና የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክየአውሮጳ ኃያላን ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያስጨንቁ ቆይተው በስተመጨረሻ ሁለቱም እጅ ሰጥተዋል ። በዋነኛነት ችግሩ ምን ነበር? ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።...more0minPlay
July 02, 2026በደቡብ ኢትዮጵያ የኮሬ ዞን መምሕራን ተማሪዎችን ላለመፈተን አደሙመምህራኑ የመብት ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለፈተና መቀመጥ እንዳልቻሉ ሁለት የኬሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የተማሪ ወላጆች ዶቼ ቬለ ተናግረዋል።...more0minPlay
July 02, 2026አሜሪካ፤ 43ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌዴሬሽንየኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ፣43ኛው ዓመት ክብረ በዓል ሚኒሶታ ውስጥ ካለፈው እሁድ አንስቶ እየተካሄደ ሲሆን፣ እንግዶቿን በጉጉት ስትጠባበቅ የነበረችው ሚኒሶታም መሰንበቻውን ሞቅ ደመቅ ብላ ትቆያለች። ይህ ዓመታዊ ዝግጅት፤ተጠፋፍተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን ዓመቱን ጠብቀው የሚገናኙበት ሁነኛ ዝግጅት ነው።...more0minPlay
July 01, 2026የዐቢይ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ “መጥፎ” በተባለ ሥምምነት ወደ ንግድ ብድር ሊመለስ ነው?ውድ ወለድ የሚከፈልባቸው የንግድ ብድሮች እንዳቆሙ በተደጋጋሚ ምለው የሚገዘቱት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቃላቸው የሚፈተንበት ሥምምነት ከቦንድ ባለቤቶች ጋር አድርገዋል። ሥምምነቱ ኢትዮጵያ እስከ 9% ወለድ የሚከፈልበት ቦንድ እንድታወጣ የሚያደርግ ነው። ኢትዮጵያ ቦንዱን ካላወጣች ለግል አበዳሪዎቿ እስከ 90 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ትገደዳለች።...more0minPlay
July 01, 2026የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነውየ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ትናንት ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ በይፋ ተጀምሯል። ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላትና የመፈተኛ ክፍሎች ከመግባታቸው በፊት ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር ተደርጎባቸዋል።...more0minPlay
July 01, 2026ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጎላ ሚና አላቸውበጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በማኅበረሰብ መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴ መፍታት እንደሚገባ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች አመለከቱ። ከዚህ በተጨማሪ ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በክልሉ አዋሳኝ ቦታዎች የሚስተዋል በመሆኑ ታጣቂዎች መሣሪያ በቀላሉ እንደሚያገኙ አመልክተዋል።...more0minPlay
July 01, 2026እንደ ቲክቶክ ያሉ ዲጅታል መድረኮች ለስዓትት እዚያው እንድንቆይ ለምን ያደርጋሉ?ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደ የቲክቶክ ያሉ የአጫጭር ቪዲዮ መድረኮች የተነደፉት ሱስ እንዲያስይዙ ሆነው ነው በሚል የሚቀርብባቸውን ክስ ሲያስተባብሉ ቆይተዋል። በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት እንዳረጋጠው ግን የአጫጭር የቪዲዮመድረኮች የተነደፉት ተጠቃሚዎችን የበለጠ ተሳታፊ እንዲሆኑ በሚያደርጉ የሰዎች የሥነ-ልቦና እና የነርቭ ስርዓቶች ላይ ተመስርቶ ነው።...more0minPlay
July 01, 2026አዲሱ የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ ጥናትየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዓመታዊ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን ለመወሰን ያጠናውን ጥናት ይፋ በማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል። በቀረበው የጥናት ሰነድ መሠረት፣ ለሚቀጥለው የ2019 ዓ.ም የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ጣሪያው 11 በመቶ ብቻ እንዲሆን ሐሳብ ቀርቧል።...more0minPlay
July 01, 2026የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያሳለፈው ውሳኔየዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን ለማስቀረት ያደረጉትን ሙከራ ውድቅ አደረገ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች፣ የዚህ ውሳኔ ፋይዳ፣ ከፍተኛ መሆኑን እና ለኢትዮጵያውያንም በብዙ መልኩ አስተውጽኦ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።...more0minPlay
July 01, 2026ምባፔ እና ሃላንድ የየራሳቸውን የታሪክ ገጾችን መግለጥ ቀጥለዋልየ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የ32ቱ ቡድኖች የጥንካሬ መፈተኛ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ማክሰኞ ምሽት በተደረጉ ጫወታዎች የዘመናችን ከዋክብቶች ኪሊያን ምባፔ እና አርሊንግ ሀላንድ ለየሀገሮቻቸው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈቱበት ተአምራዊ ምሽት ሆኖ አልፏል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.