Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.
June 29, 2026የቀነ ገደቡ መጠናቀቅ እና የፍልሰተኞች ሥጋት በደቡብ አፍሪካ“ ማርች ኤንድ ማርች “ የተባለው ቡድን ካቀደው የተቃውሞ ሰልፉ አስቀድሞ ከወዲሁ በአንዳንድ የአገሪቱ ግዛቶች ውጥረት የነገሠበት ድባብ ተስተውሏል። በፍልሰተኞች ላይም እሥር እና ወከባ እየተፈመ ይገኛል ፡፡ በተለይ ኢስተርን ኬፕ በተባለ አካባቢ ትናንት እሁድ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በጅምላ መታሠራቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል ፡፡...more0minPlay
June 29, 2026በትግራይ የወጣቶች አፈሳ ቀጥሏል መባሉና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያየአውሮፓ ህብረት በክልሉ ያለውን ውጥረትና የወጣቶች የግዳጅ አፈሳን ተቃውሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ህጋዊ እውቅና የሌላቸው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለስልጣናት ግን አስገዳጅ የተባለውን ወታደራዊ አፈሳ የተሳሳተ ፍረጃ በማለት እያጣጣሉት ነው...more0minPlay
June 28, 2026የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ውጤትና ፋይዳው እንዲሁም ተግዳሮቶቹና ተስፋውምርጫው ከመካሄዱ አስቀድሞም በስፋት እንደተጠበቀው ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ሲያሸንፍ ከቀደሙት ምርጫዎች በተለየ በአሁኑ ምርጫ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪ የምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘታቸው ትኩረት ስቧል።...more41minPlay
June 28, 2026በአውሮጳ ከፍተኛ ሙቀት ከ1300 በላይ ሰዎች ለህልፈት ዳረገበአውሮጳ በተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 1,300 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።...more0minPlay
June 27, 2026ትኩረት በአፍሪካ፤ በኢል ኦቢድ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ሊደርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጠ፤ የዛምቢያ 2026 ምርጫየተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ቃል አቀባይ በሰኔ ወር መጀመሪያ 2026 «የኤልፋሸርን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ኤል ኦቢድ ውስጥ እንዲደገም መፍቀድ የለብንም» ሲሉ አስጠንቅቀው ነበረ ።...more17minPlay
June 27, 2026ከፍተኛ ሙቀት የበረታባት ድሬደዋ ከተማ የውኃ እጥረት እየተፈታተናት እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገለጹየድሬደዋ ከተማ ከፍተኛ ሙቀት በምታስተናግድበት በዚህ ደረቃማ ወቅት የገጠማት ኃይለኛ የውኃ እጥረት ሕብረተሰቡን ለችግር ዳርጎታል። ሆቴሎች ለሁለት ቀን ብቻ ለሚበቃ አንድ ቦቴ ውኃ 5,500 ብር እየከፈሉ ነው። የከተማው ውኃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ መሐመድ ሙሴ በመብራት መቆራረጥ የተከሰተ የፓምፖች መቃጠል ችግሩን እንዳባባሰ ገልጸዋል።...more4minPlay
June 26, 2026ህወሓት የሁዩማን ራይትስ ዋችን ጥያቄ ዉድቅ አደረገዉየሕወሓት ቃል አቀባይ አቶ ሚካኤል አስገዶም ግን፤ “መግለጫው የተጋነነነና መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ” ብለዋል፡፡ “እንደ ትግራይ የህልውና አደጋ ተጋርጦብን ያለን ብሔር ነን” ያሉት አቶ ሚካኤል የሚደረገውን የቶርነት ዝግጅት “እንደብሔር ሊመጣብን የተዘጋጀውን አደጋ ለመቀልበስ የሚደረግ” ሲሉ ማብራሪያቸውን ሰትጥዋል፡፡...more4minPlay
June 26, 2026የጋምቤላ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ አስታወቀየጋምቤላ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ምክር ቤት ካሉት 205 የምክር ቤት ወንበሮች መካከል 176 የሚደርሱትን ማሸነፉ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል፡፡ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ የሆኑት አቶ አሽኔ አስቲን በክልሉ ውስጥ ከምንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አመልክተዋል፡፡...more0minPlay
June 26, 2026መረጃ የዘመኑ ወርቅ ነው ያሉ የዘርፉ ተንታኝ፣ በአፍሪካም ግንዛቤው መኖሩን ገለጹየመረጃ ሉአላዊነት፣ አንዲት ሃገር በግዛቷ ውስጥና በዜጎቿ አማካኝነት የሚመነጨውን መረጃ፣ የመሰብሰብ የማስተዳደርና የመቆጣጠር ሙሉ ስልጣን ሲኖራት ማለት ነው። በአፍሪካ ግን የዜጎችን የግል የመረጃ ልውውጥ ጨምሮ፣ አብዛኛው የመረጃ ቋት ያለው በሌሎች ያደጉ ሃገራት ነው።...more0minPlay
June 26, 2026የደቡብ አፍሪካ የፀረ ስደተኛ ቡድኖች ተቃውሞ ያስከተለው ሥጋትየደቡብ አፍሪካ መንግሥት ህገ ወጥ ሥደተኞችን የመቆጣጠር ሃላፊነት የመንግሥት ተቋማት ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የቡድኑ አባላት በፍልሰተኞች ላይ የሚያደርሱትን ወከባ እንዲያቆሙም መንግሥት እያሳሰበ ይገኛል፡፡ “ ማርች ኤንድ ማርች “ እና ኦፕሬሽን ዱዱላ የተባሉ ቡድኖች እናካሂዳለን ለሚሉት የተቃውሞ እንቅስቃሴም ሃላፊነት እንደማይወስድ አስታውቋል...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,870 episodes available.