Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.
May 26, 2024የኢትዮጵያ የግጭት አዙሪትና የአሜሪካ የፖሊሲ ንግግርዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግጭት በተመለከተ ከሦስት ዐሥርተ ዓመታት ወዲህ ለየት ያለ የፖሊሲ አቋሙዋን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከአዲስ አበባ ዐሳውቃለች ። ጉዳዩ 33 ዓመት ወደ ኋላ ወደ ለንደኑ ስብሰባም ይወስደናል ። እንዴት? መልሱን ከሳምንታዊው የውይይት መድረክ ያድምጡ ።...more40minPlay
May 19, 2024የጠቅላይ ሚንስትሩ የሰላም ጥሪ ፤ ሰላማዊ ምላሽ እንዴት ያግኝ?ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንታት መንግስታቸው ከታጣቂዎች ጋር ብርቱ ፍልሚያ እያደረገ ወደ ሚገኝባቸው የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አካባቢዎች አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሁለቱም አካባቢዎች በጥቅሉ ጦርነት እንዲቆም ብሎም «በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ መገዳደልም እንዲያበቃ » ጥሪ አስተላልፈዋል።...more41minPlay
May 12, 2024የሁለቱ ወገኖች የስልጣን ሽኩቻ ወዴት ያመራ ይሁን?በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በህወሐት መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዳይደፈርስ ብዙዎቹ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።...more41minPlay
April 28, 2024እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ግጭትን ለመሸከም ጫንቃዉ አላት?ትግራይና አማራ ክልል በሚወዛገቡባቸዉ አካባቢዎች የተቀሰቀሰዉን ዉጥረት እንዴት አያችሁት? ምንስ ተሰማችሁ? ከየትኛዉም ወገን ይሁን ያ ሁሉ ህዝብ ካለቀ እና ንብረት ከወደመ በኋላ በፕሪቶርያዉ ስምምነት ሰላም ይሰፍናል ተብሎ ሲጠነቅ ዳግም ወደ ሌላ ዉጥረት እየተገባ ነዉ? ይህን ዉጥረት ህዝቡና ሃገሪቱ መሸከም ይችላሉ? ምንድን ነዉ መደረግ ያለበት?...more46minPlay
April 21, 2024አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰትወደ ሳዑዲ አረብያ ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ 38 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የተጫኑበት ጀልባ ሰጥሞ ባለፈው ሳምንት ሞተዋል። በዚሁ ሳምንት ነበር ሳዑዲ አረብያ ውስጥ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ጥረት የቀጠለው።በአሁኑ ጊዜ በአደገኛ ጉዞ መላልሰው ወደ መካከለኛው ምሥራቅና ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚሄዱ ጥቂት አይባሉም።...more43minPlay
April 07, 2024ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታትጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን የያዙበት ስድስተኛ ዓመት ደጋፊዎቻቸው በሰልፍ ተቃዋሚዎቻቸው በትችት አስበውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጆን አሕመድ፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሙከርም ሚፍታህ፣ ከጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሰይፈ ታደለ የተሳተፉበት ውይይት ለመሆኑ ዐቢይ ምን አሳክተው ምን አጎደሉ? ሲል ያጠይቃል...more44minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.