Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.
July 14, 2024እንወያይ፤ ሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቶች ተግዳሮቶች በኢትዮጵያበኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን በተለያዩ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በሌላ በኩል ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ እና ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚወተውቱ በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በስራቸው ሳቢያ ከመንግስት ጫና እና እንግልት እየጠነከረባቸው መምጣቱን እየገለፁ ነው።...more41minPlay
June 23, 2024እንወያይ፤ በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለ ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያበኢትዮጵያ ዉስጥ ግጭትና ጦርነት ሴቶች ይበልጥ ግፍ ደርሶባቸዋል፤ እየደረሰባቸዉም ነዉ። ጾታዊ ጥቃትና ማዋከቦችን ለመግታት ከመንግሥትም ሆነ ከሴቶች ማህበራት በቂ ድጋፍ አልታየም ይባላል። እንደሚታወቀዉ ሴት እናት፤ እህት፤ ሚስት፤ ልጅ ናት። ለኢትዮጵያዉያን ደግሞ አገርም ናት። ግን ሴቶች ላይ እየደረሰ ያለዉ ሰቆቃ ለምን ትኩረት አልተሰጠዉም?...more42minPlay
June 16, 2024የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳውማሻሻያውን የደገፉ እርምጃው በኢትዮጵያ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲገቡ የሚያበረታታ ሲሉ የማሻሻያው ተቃዋሚዎች ደግሞ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ በነበረው በትግራዩ ጦርነት የተፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ ሳያገኙ ተድበስብሰበው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሲሉ ይቃወማሉ።...more37minPlay
June 02, 2024ውይይት፦ የመንግሥት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከኢትዮጵያ ፍላጎት ምን ያህል የተጣጣመ ነው?የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድራቸው ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ባለፉት ሦስት አስር ዓመታት ገደማ ከሁለት ወደ አርባ ሰባት አድጓል። ባለሙያዎች በተማሪዎች ቁጥር እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ረገድ ዕድገት ቢኖርም ውጤቱ ለመንግሥትም ሆነ ለዜጎች አመርቂ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ። በዚህ ውይይት በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የኅትመት ዳይሬክተር ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ እና በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ ተሳትፈዋል።...more41minPlay
June 02, 2024የመንግሥት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከኢትዮጵያ ፍላጎት ምን ያህል የተጣጣመ ነው?አየር መንገድ፣ መከላከያ ሠራዊት እና ፌድራል ፖሊስ ያቋቋሟቸውን ሳይጨምር ኢትዮጵያ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አሏት። የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ሲጨምር ሀገሪቱ ምን አተረፈች? የትምህርት ተቋማቱ ከገዢው ፓርቲ ምን ያክል ነጻ ናቸው? በዚህ ውይይት አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ እና ዶክተር ሰይፈ ታደለ ተሳትፈዋል።...more41minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.