Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.
October 06, 2024እንወያይ፤ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ዛሬ በኢትዮጵያ እንዴት ይገመገማል?ኢትዮጵያ ውስጥ ከስድስት ዓመታት በፊት የመናገር ነጻነት ከፍተኛ መሻሻል የታየበት ዓመት ለመሆን በቅቶ ነበር። ይሁንና ሀገራዊ ፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መረጃ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞ፤ ትንታኔ የሚሰጡ የፖለቲካ ተንታኞች፤ ብሎም የኪነጥበብ ባለሞያዎች ጫና ላይ እየደረሰ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በየጊዜዉ መግለጫ ያወጣሉ።...more41minPlay
September 29, 2024የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?ገና ለገና የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ ነው በሚል በተለይ በመሰረታዊ የፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ ተከታታይነት ያለው ጭማሪ እየታየ መሆኑን ሸማቾች ይናገራሉ ። ይህ ደግሞ የሰራተኛውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ይደግፋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የደሞዝ ጭማሪ ተስፋ እንዳያመነምን ያሰጋል ።...more42minPlay
September 22, 2024ውይይት፤እያሽቆለቆለ ለመጣው የተማሪዎች ውጤት እና የትምህርት ጥራት መፍትሄ ይኖረው ይሆን?በኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። በስርዓተ ትምህርቱ ፣በትምህርት ጥራት እና አሰጣጥ ላይም ጥያቄ እንዲነሳ እያደረገ ነው። ታዲያ የችግሩ መንስኤ ምንድነው? ተማሪዎች መምህራን ወይስ ስርዓተ ትምህርቱ?መፍትሄውስ?...more36minPlay
September 08, 2024የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል?በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ለተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት? በውይይቱ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ ተሳትፈዋል።...more43minPlay
September 08, 2024የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል?በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ለተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት እና መንግሥት ምን ሊያደርጉ ይገባል?...more43minPlay
September 01, 2024ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች ያስከተሉት ጉዳት እና የመከላከል ሥራዎች በኢትዮጵያበኢትዮጵያ ከሰሞኑ የተከሰቱ ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች ለበርካቶች ሞት እና መፈናቀል ሰበብ ሆነዋል ። በጎፋ የመሬት መንሸራተት ከሁለት መቶ አምሳ በላይ ሰዎች መቀጠፋቸው ያጫረው የሐዘን ጠባሳ ገና አልጠገገም ። ሦስት ምሑራን እና ባለሞያዎች የተሳተፉበትን ሙሉውን ውይይት በድምፅ ማዕቀፉ መከታተል ይቻላል ።...more39minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.