Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 486 episodes available.
February 22, 2026እንወያይ: የአፍሪቃ ሕብረት ግጭቶችን ለማስቆም ለምን ተሳነው?ከተመሠረተ 63 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪቃ አህጉራዊ ተቋም የአፍሪቃ ሕብረት በአባል ሃገራት ውስጥ ለሚካሄዱ ግጭቶችን ማስቆም ባለመቻሉ እየተተቸ ነው። ተቋሙ ራዕይ በነበራቸው የቀድሞ መሪዎች የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተብሎ ሲቋቋም አፍሪቃ እንደ አንድ ተባብራ ሰላም አንድነቷን ለመጠበቅ እንደነበር ይታሰባል። አፍሪቃ ውስጥ እጅግ በርካታ ግጭት ጦርነቶች በሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሱ መሆኑ ይታያል። ሚሊዮኖችም ለስደትና ለመፈናቀል በመዳረጋቸው በአብዛኛው ሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች ሆነዋል።...more45minPlay
February 15, 2026እንወያይ፤የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደየት ያመራ ይሆን?መፍትሄውስ ምን ይሁን?በ2010 ዓ/ም እንደገና የጀመረው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ አድናቆት የተቸረው እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርን የሰላም ኖቬል እስከማሸለም የደረሰ ነበር።ይሁንና የሀገራቱ ሰላማዊ ግንኙነት የዘለቀው ለጥቂት ዓመታት ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ አለመግባቱ እየተካረረ መጥቷል።...more48minPlay
February 08, 2026የትግራይ ግጭት እና ዘላቂው መፍትሔየፌደራል ኃይሎች ከአወዛጋቢዎቹ ከአላማጣ እና ኮረም እንዲሁም ከሌሎች አጎራባች ከተሞች መውጣታቸው ከተሰማ በኋላ ነዋሪዎች ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ከከተሞቹ መሸሽ መጀመራቸው ሌላው ስጋቱ እንዲጨምር ያደረገ ክስተት ነበር። በትግራይ የድሮን ጥቃቶች በሁለት አካባቢዎች ተፈጸሙ የመባሉ ዜና በሀገር ውስጥም በውጭም ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።...more42minPlay
February 01, 2026ውይይት፤ የትራምፕ ሽምግልና ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?እንዴትስ ጥቅሟን ታስከብር?የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአባይ ውሃ ባለድርሻነት ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኝ በሚል፤iኢትዮጵያ እና ግብፅጽን ዳግም ወደ ድርድር ለማምጣት ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ደጋግመው ገልፀዋል.።ያም ሆኖ ትራምፕ በተለያዩ ጊዜዎች የሚሰጧቸው ወደ ግብፅ ያዘነበሉ አስተያየቶች የገለልተኝነት እና የፍትሃዊነት ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም።...more45minPlay
January 25, 2026ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ?የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?...more41minPlay
January 25, 2026ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ?የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት የከዓመት ዓመት ዕድገት በህዳር ወር ከነበረበት 10.9 በመቶ በታኅሳስ ወደ 9.7 በመቶ ዝቅ ብሏል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?...more41minPlay
January 18, 2026ዉይይት፣ የትራምፕ አስተዳደር ርምጃ፣ የዓለም ሕግና ሥርዓት እንዴትነትየትራምፕ መስተዳድር የቬኑሱዌላን መሪ ማገት ብቻ ሳይሆን የነዳጅ ሐብቷንም ተቆጣጥሯል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማዱሮን ከማሳገታቸዉ በፊት የየመን ሁቲዎችን፣ የሶማሊያ፣ የኢራቅ፣ የሶሪያና የናጄሪያ ሸማቂዎችን አጠፋለሁ በሚል ሐገራቱን በተደጋጋሚ ደብድበዋል።እስራኤልን አግዘዉ ኢራንን ደብድበዋልም።...more46minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 486 episodes available.