Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 486 episodes available.
April 12, 2026ውይይት፤የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ 8 የስልጣን አመታት ሲቃኙመጋቢት 24 ቀን 2018 ዶክተር ዓብይ አህመድ በሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ወደ መንበረ ስልጣን መጥተዋል። የእሳቸው ወደ ስልጣን መምጣት የኢህአዴግን አመራር ይወቅሱ በነበሩ በብዙዎች ዘንድ የለውጥ ተስፋ አሳድሯል።ያም ሆኖ፣ መንግስታቸው እንዳጀማመሩ አለመቀጠሉ፤ የነበረው የለውጥ ተስፋ መደብዘዙ ይነገራል።...more55minPlay
April 05, 2026እንወያይ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ዳፋ ለአፍሪቃ ቀንድጉዳቱ በሁሉም ሐገራት ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ደሐ የአፍሪቃ ሐገራት ላይ ያሳደረዉ ከፍተኛ ጫና የየሐገራቱን ሕዝብ ኑሮ እያመሰቃቀለዉ ነዉ።የዚያኑ ያክል አንዳድ ተንታኞች እንደሚሉት ጦርነቱና ሥጋቱ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ይጫራል ተብሎ የሚፈራዉን ሌላ ዙር ጦርነት ባያስቀረዉ እንኳን ለጊዜዉም ቢሆን አዳፍኖታል።በየሰበብ አስባቡ ይሰማ የነበረዉ የአዲስ አበባና የአስመራ የዉጊያ ዛቻና ፉከራ ቀንሷል።...more48minPlay
March 29, 2026በኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ እና ዐበይት ጉዳዮችበ30 ዓመታት ሴቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላቸው መቀመጫ ከ2% ወደ 40% አድጓል። ምን ፈየደ? በግንቦት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ጉዳዮች ምን ያክል ትኩረት አገኙ? በግጭት ድባብ ውስጥ በሚካሔድ ምርጫ ለእንስቶች ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ እጸገነት ተስፋዬ፣ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ሒሮዋቅ ግርማ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህርና የሶሻል አንትሮፖሎጂ ተመራማሪ ዶክተር ትርሲት ሳህለድንግል እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ጥናት ተመራማሪ ፍቅር ጌታቸው በውይይቱ ተሳትፈዋል።...more47minPlay
March 22, 2026ውይይት፤ ኢትዮጵያ ብርቱ ፈተና የደቀነውን የነዳጅ እጥረት እንዴት ትወጣ?የኢራን ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት ላይ የፈጠረው መስተጓጎል ለመቋቋም ሕዝቡ እና ተቋማት በከፍተኛ ጥንቃቄ ነዳጅ እንዲጠቀሙ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት አስጠንቅቋል። የነዳጅ ግብይትም መንግስት ባስቀመጠው ታሪፍ መሰረት እንዲከናወን አሳስቧል። ያም ሆኖ ችግሩ ከዓቅም በላይ መሆኑን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው።...more47minPlay
March 15, 2026እንወያይ፤ የጦርነቱ ዳፋ ወደኛ እንዳይደፋከኢኮኖሚ አንጻር የሖርሙዝ ሠርጥ በዓለም ገበያ ከሚሸጠው የአፈር ማዳበሪያ እስከ 30 በመቶ ወይም 16 ሚሊዮን ቶን የሚጓጓዝበት እንደሆነ ይታወቃል። የአለማችን 20 % የነዳጅ ግብይትም በዚሁ መስመር ይተላለፋል።...more45minPlay
March 01, 2026የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት ያባባሰው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔበብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ የተደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት አባብሶታል። በሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች “ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ” የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀው የካቲት 16 ቀን 2018 ነው። ዶይቼ ቬለ የሕግ ባለሙያዎቹን አቶ አምደገብርኤል አድማሱ እና አቶ አወት ልጃለም፤ ከሳልሳይ ወያነ ትግራይ አቶ ኪሮስ ኃይለሥላሴ፣ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አቶ ዳምጠው ተሰማን በመጋበዝ በጉዳዩ ላይ ውይይት አካሒዷል።...more47minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 486 episodes available.