Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 486 episodes available.
July 12, 2026ሃገራዊ ምክክር የመጨረሻው ምዕራፍ ከተስፋ ባሻገርኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ለማድረግ ጥቂት ቀናት ቀርተዋታል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በምክክሩ ላይ ይሳተፋሉ የተባሉ ከአራት ሺ በላይ ተወያዮች አዲስ አበባ ከተማ መግባታቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ውጪ የምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ከሶስት ዓመታት በላይ እንደወሰደበት ታይቷል።...more47minPlay
July 05, 2026እንወያይ፤ የትግራይ ክልል ቀዉስ ወዴት እያመራ ነዉ? መፍትሔዉስ?በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።...more44minPlay
June 28, 2026የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ውጤትና ፋይዳው እንዲሁም ተግዳሮቶቹና ተስፋውምርጫው ከመካሄዱ አስቀድሞም በስፋት እንደተጠበቀው ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ሲያሸንፍ ከቀደሙት ምርጫዎች በተለየ በአሁኑ ምርጫ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪ የምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘታቸው ትኩረት ስቧል።...more41minPlay
June 21, 2026በአርሲ ዞን ጥቃት ግድያው ለምን ተደጋገመ፥ እንዴትስ ይቆማል?ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ይሰነዘራሉ ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ የመገደል የመፈናቀላቸው፣ የቤት ንብረታቸው መዘረፍና መውደም ሰበቡ ምን ይኾን፥ እንዴትስ ይቁም? ሙሉ ውይይቱን በማገኛው በኩል ማድመጥ ይቻላል ።...more44minPlay
June 14, 2026ውይይት፤በምርጫው ከሚያሸንፈው መንግስት በመጭው አምስት የስልጣን ዓመታት ምን ይጠበቃል?በኢትዮጵያ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡበት ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል።ያም ሆኖ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተካሄደው የኑሮ ውድነት፣ ስራ አጥነት እና የኢኮኖሚ ችግር ባየለበት እና በተለያዩ አካባቢዎች ግጭት፣መፈናቀል እና ሞት በሚሰማበት ነው። ለመሆኑ ከመንግስት በመጭዎቹ 5 ዓመታት ምን ይጠበቃል?ቅድሚያ የሚሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይስ የቱነው?...more46minPlay
June 07, 2026ዉይይት፤ ቅድመ ምርጫ፣ ምርጫ እና ድኅረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተካሂዷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ምርጫ ፤ዋዜማው፣ የምርጫው ዕለት እና ድህረ ምርጫ በጋዜጠኞች ዕይታ ምን ይመስላል።?7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ፤ ከዘገቡ የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞች መካከል አራቱን አነጋግረናል።...more43minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 486 episodes available.