Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 355 episodes available.
January 19, 2025እንወያይ፤ የበቀል ፖርኖግራፊ - የበይነ መረብ ሰላባ የሆኑት ወጣት ኢትዮጵያዉያንየወጣት ኢትዮጵያዉያት የእርቃን ፎቶና ቪዲዮዎች በኢንተርኔት የበቀል መሳርያ እየሆኑ መምጣታቸዉ እያነጋገረ ነዉ። ያለፈቃድ የሚለቀቁት እነዚህ ምስሎች የገንዘብ ማግኛ ምንጭ መሆናቸዉ ደግሞ ነገሩን አሳሳቢ አድርጎታል። በኢንተርኔቱ ጨለማ ዓለም ታስረዉ እራሳቸዉን እስከማጥፍት የሚደርሱ ጥቂቶች አይደሉም። መፍትሄዉ ምንድን ነዉ? ሃሳባችሁን አካፍሉን!...more39minPlay
January 12, 2025እንወያይ፦ የአራት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ዕግድ ስለ ኢትዮጵያ የሲቪክ ምኅዳር ምን ይናገራል?የብሔራዊ ምክክር ሒደት የጀመረችው፤ ለሽግግር ፍትሕ የምትዘጋጀው እና በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ የምታካሒደው የኢትዮጵያ መንግሥት አራት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶችን አግዷል። በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኩል የተላለፈው ዕግድ ሕጋዊ ነው? ዕግዱ ስለ ሲቪክ ምኅዳሩ ይዞታ ምን ይናገራል? በውይይቱ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፣ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የሰብአዊ መብቶች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበራ ኃይለማርያም ተሳትፈዋል።...more47minPlay
January 12, 2025እንወያይ፤ የአራት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ዕግድ ስለ ኢትዮጵያ የሲቪክ ምኅዳር ምን ይናገራል?የብሔራዊ ምክክር ሒደት የጀመረችው፤ ለሽግግር ፍትሕ የምትዘጋጀው እና በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ የምታካሒደው የኢትዮጵያ መንግሥት አራት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶችን አግዷል። በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኩል የተላለፈው ዕግድ ሕጋዊ ነው? ዕግዱ ስለ ሲቪክ ምኅዳሩ ይዞታ ምን ይናገራል? ሦስት እንግዶች የተሳተፉበትን ውይይት ያድምጡ!...more47minPlay
January 05, 2025ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የሚደረጉ ድርድሮች እና ስምምነቶች ለምን አይነገሩም ?በተለያዩ ጊዜያት ከኦነግ ጋር የተደረጉ ድርድሮች ፤ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ጋር የተደረገ ድርድር እና ስምምነት ፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ፣ ከህወሓት ጋር እንዲሁም በቅርቡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አንድ ክንፍ ጋር የተደረጉ ድርድሮች እና ስምምነቶች ተጠቃሾች ናቸው ።...more45minPlay
December 29, 2024የ2024 ዓ.ም ዐበይት ክስተቶች አንድምታቸውና መዘዞቻቸው2024 ዓ.ም. በዓለማችን ከባድ ጦርነቶች የቀጠሉበት ዓመት ነው።የፊታችን የካቲት ፣3 ዓመት የሚደፍነው የዩክሬን ሩስያ ጦርነት፣ከዓመት በላይ የዘለቀውና የአካባቢውን ሀገራት ያዳረሰው የእስራኤል ሀማስ ጦርነትና ዓመት ከ8 ወር ያለፈው የተዘነጋው የሱዳን ጦርነት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።የእነዚህ ጦርነቶች ዳፋም ለመላው ዓለም ተርፏል።...more42minPlay
December 22, 2024ባህላዊው ሽምግልና እና የፖለቲካው ተፅዕኖበግለሰብም ሆነ በማኅበረሰብ መካከል ግጭት ፀብን ለማርገብ፣ ብሎም ሰላምን ለማስፈን ሽምግልና ኢትዮጵያ ውስጥ በየማኅበረሰቡ የረዥም ዘመናት ማኅበራዊ እሴት ሆኖ ቆይቷል። በአሁኑ ጊዜ ግን በአመዛኙ ይህ ማኅበራዊ እሴት የቀድሞ ክብሩን እያጣ፣ ወግ ያለው የማረጋጋት ሚናውም እየደበዘዘ መምጣቱን ብዙዎች በማንሳት ይተቻሉ።...more41minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 355 episodes available.