የአዲስ አበባ ችግሮች መፍትሔ እንደሚሹ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትም ይሁኑ ዋና ከተማዋን በጥልቀት ያጠኑ ባለሙያዎች ይስማማሉ። በከፍተኛ ወጪ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በዚህ ወቅት አስፈላጊ ነው ወይስ አንገብጋቢ? ፒያሳ እና ካዛንቺስን ለመሳሰሉ ነባር ሠፈሮች ነዋሪዎችስ ምን ይዞ መጣ? የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ፣ በበርሚንግሐም ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ የዓለም አቀፍ ልማት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር ኤዛና ሐዲስ እና በፊንላንድ ራምቦል በተባለ ተቋም የከተማ መሠረተ-ልማት የንድፍ (Design) ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ዱጋሳ ተሳትፈዋል።