በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ለተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት? በውይይቱ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ ተሳትፈዋል።