የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድራቸው ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ባለፉት ሦስት አስር ዓመታት ገደማ ከሁለት ወደ አርባ ሰባት አድጓል። ባለሙያዎች በተማሪዎች ቁጥር እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ረገድ ዕድገት ቢኖርም ውጤቱ ለመንግሥትም ሆነ ለዜጎች አመርቂ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ። በዚህ ውይይት በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የኅትመት ዳይሬክተር ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ እና በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ ተሳትፈዋል።