Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እ... more
January 12, 2025እንወያይ፦ የአራት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ዕግድ ስለ ኢትዮጵያ የሲቪክ ምኅዳር ምን ይናገራል?የብሔራዊ ምክክር ሒደት የጀመረችው፤ ለሽግግር ፍትሕ የምትዘጋጀው እና በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ የምታካሒደው የኢትዮጵያ መንግሥት አራት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶችን አግዷል። በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኩል የተላለፈው ዕግድ ሕጋዊ ነው? ዕግዱ ስለ ሲቪክ ምኅዳሩ ይዞታ ምን ይናገራል? በውይይቱ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፣ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የሰብአዊ መብቶች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበራ ኃይለማርያም ተሳትፈዋል።...more47minPlay
December 01, 2024ውይይት፤ የአማራ ክልል ምስቅልቅል እና የክልሉ ነዋሪ ሰቆቃ እንዴት ያብቃ?በአማራ ክልል በመካለከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደው ግጭት የክልሉን ነዋሪ ለዘርፈ ብዙ ችግር ዳርጓል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰላማዊ ሰዎችም በግጭቱ የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን የመብት ተሟጋቾች የሚያወጧቸው መረጃዎች ያሳያሉ።ያም ሆኖ ይህንን ሰቆቃ ለማስቆም በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የንግግር ፍንጭ አልታየም።...more42minPlay
November 20, 2024የእንወያይ ፕሮግራም ማስተዋወቂያበሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።...more1minPlay
November 15, 2024Diskussion-Addis Abeba Corridor Development necessary or urgent? 15.11.2024 - MP3-Stereoየአዲስ አበባ ችግሮች መፍትሔ እንደሚሹ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትም ይሁኑ ዋና ከተማዋን በጥልቀት ያጠኑ ባለሙያዎች ይስማማሉ። በከፍተኛ ወጪ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በዚህ ወቅት አስፈላጊ ነው ወይስ አንገብጋቢ? ፒያሳ እና ካዛንቺስን ለመሳሰሉ ነባር ሠፈሮች ነዋሪዎችስ ምን ይዞ መጣ? የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ፣ በበርሚንግሐም ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ የዓለም አቀፍ ልማት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር ኤዛና ሐዲስ እና በፊንላንድ ራምቦል በተባለ ተቋም የከተማ መሠረተ-ልማት የንድፍ (Design) ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ዱጋሳ ተሳትፈዋል።...more43minPlay