Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እ... more
March 16, 2025የኢትዮጵያ ባንኮች ውህደት፦ በግዳጅ ወይስ በገበያው ፍላጎት?የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ሲጸድቅ አንድ ባንክ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ቅርንጫፍ ከፍቶ ለመሥራት የሚያስችለውን ፈቃድ ለማግኘት 66 ቢሊዮን ብር ገደማ አጠቃላይ ሐብት ሊኖረው ይገባል። ረቂቅ መመሪያ ውህደትን የሚገፋፋ እንደሆነ በባለሙያዎች ዘንድ ግንዛቤ አለ። ይህ ውይይት የባንኮች ውህደትን ፋይዳ እና ተግዳሮት ይፈትሻል። በውይይቱ ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት አቶ ባህሩ ያሲን፣ ለረዥም ዓመታት በከፍተኛ የባንክ ባለሙያነት ያገለገሉት የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ለማ እና የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ ተሳትፈዋል።...more47minPlay
February 16, 2025የእርዳታ መታገድ አሉታዊ እና አዎንታዊ ፋይዳአሜሪካ ለውጭ የምትሰጠውን እርዳታ ማቆሟ በተለይ በአፍሪቃ ሃገራት ከፍተኛ ግርታና ድንጋጤ ፈጥሯል። ለሁለተኛ ጊዜ ወደ የሥልጣን መንበር የመጡት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ እርዳታ ለዘጠና ቀናት እንዲቆም ወስነዋል። ትራምፕ እርዳታ አፍሪቃውያንን አሳንፏቸዋል ነው የሚሉት።...more41minPlay
February 07, 2025እንወያይ፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ-ብዙ ቀዉስ፣ ምክንያቱና መፍትሔዉየአማራና የኦሮሚያ ክልሎችን የሚያብጠዉ የመንግሥትና የአማፂያን ግጭቶች፣ በየአካባቢዉ የተንሠራፋዉ ሥርዓተ አልበኝነት፣ እገታ፣ ዘረፋ፣ መፈናቃል፣ የኑሮ ዉድነት ብዙዎች እንደሚሉት ሕዝቡን ለመከራ፣ ሐገሪቱን ደግሞ ለሕልዉና አደጋ ዳርጓቸዋል...more49minPlay