Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እ... more
August 24, 2025እንወያይ፤ ለኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ዋና ዋና ፈተናዎች እና መፍትሔዎችውይይቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ይረዳል በሚል በመስጠት ላይ ስለሚገኘው የክረምት ልዩ ስልጣና ምንነት እና ስለገጠሙት ፈተናዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አዲሱ የትምህርት ዘመን ሊጀምር የአንድ ወር እድሜ ያህል እንደመቅረቱ ከትምህርት ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሯል።...more45minPlay
July 13, 2025የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ ይደረጋል የተባለ ማሻሻያ ለምን ሥጋት ፈጠረ?የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ ሊደረጉ የታቀዱ ማሻሻያዎችን የመረመሩ ባለሙያዎች እና አጥኚዎች ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ ሳለ ዘርፉን ቀፍድደው የያዙ ገደቦች እና አሠራሮች ተመልሰው ተግባራዊ ሊሆኑ ነው የሚል ብርቱ ሥጋት አላቸው። ሦስት እንግዶች የተሳተፉበት ውይይት ማሻሻያዎቹን እና ተጽዕኖዎቻቸውን ይፈትሻል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተመራማሪ ሐይማኖት አሸናፊ፣ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የሰብአዊ መብቶች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ተማሪ እና ተመራማሪ ሕሊና ብርሀኑ በውይይቱ ተሳትፈዋል።...more46minPlay
July 06, 2025ዉይይት፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናር፣እጥረትና እስከፊ ጫናዉለድጎማዉ መነሳት ምክንያቱ ምንም ሆነ ምን የነጃ ዋጋ አለቅጥ ተንቻርሯል።-ለእጥረቱ ተጠያቂዉ ማንም ሆነ ማን እጥረቱ አለ።የዋጋዉ ንረትና እጥረቱ ወትሮም በየአካባቢዉ በሚደረጉ ግጭቶች ከቤት ንብረቱ የተፈናቀለ፣ መሥራት ያልቻለዉ ወይም ሰላማዊ ዝዉዉሩ የተገደደበበት ሕዝብ፣ በብር የመግዛት አቅም መዳከምና በዓለም ላይ በሚታየዉ ግሽበት ምክንያት ኑሮ የተወደደበት ሕዝብ ለከፋ ችግር መጋለጡን በየአጋጣሚዉ እየተናገረ ነዉ።በዛሬዉ ዉይይታችን የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናርና እጥረቱ ያስከተለና የሚያስከትለዉን ችግር ባጫጭሩ አንስተን መፍትሔዉን ለመጠቆም እንሞክራለን...more47minPlay