
Sign up to save your podcasts
Or


"መጽናት!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህት የመጀመሪያው ክፍል።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዕብ. 10፡36፣ 1 ሳሙ. 2፡1-11፣ መዝ. 119፡71፣ ዕብ. 12፡3
"በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ!" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 2ኛው ክፍል።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ይሁዳ 1፡20-21
"በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ!" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ክፍል 1።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ይሁዳ 1፡20-21
"በርሱ መወደድ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት 2ኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማቴ. 17፡1-9፣ ኢሳ. 59፡1-21፣ መክ. 5፡1
ጌታን ስንሰማ ምን ይሆናል?
"በርሱ መውደድ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ትምህርት ክፍል 1።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ኤፌ. 5፡1 ፣ ዳን. 9፡23፣ 10፡11፣ 19
ዳንኤል እጅግ የተወደደ እንዲሆን ያደረገው ምንድን ነው?
"ሰቆቃና የንስሐ አስቸኳይነት" በሚል በሉቃስ 13፡1-5 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
"አገልጋይና አገልግሎቱ" በሚል ርዕስ በኮንቱላ ሜትሮቻፕል በፓስተር ታምራት ኃይሌ የተሰጠ የአገልጋዮች ትምህርት ክፍል 2።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 2 ዜና 29፡11
አገልጋይ ምን መሆን ይገባዋል?
1) የዳነና መዳኑን በህይወት ለውጥ ፍሬ ያሳየ መሆን አለበት / ገላ. 5፡22፣ ዮሐ. 13፡13-14፣ ማቴ. 11፡28-31
2) በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ መሆን አለበት /ኢሳ. 61፣ ኢዩ. 2፡28፣ ዘካ. 5፡11፣ ኤፌ. 5፡18
3) የደቀ መዝሙርነት ጉዞ የጀመረ መሆን አለበት
4) የአገልግሎት ጥሪውን የሚያውቅ መሆን አለበት
5) በምሪትና በተጠያቂነት ያምናል
6) አገልጋይ ሁልጊዜ ያድጋል - ያልደረሰበትን ለመድረስ ይተጋል!
7) መሳሳት እንደምችል ያውቃል - ለመታረምም ፈቃደኛ ነው
8) አገልጋይ ባለራዕይ ነው - ሩቅ ያያል!
9) አገልጋይ ተባብሮ በመሥራት ያምናል
10) አገልጋይ ተተኪ ያፈራል - ለዚሁም ይተጋል!
11) አገልጋይ ኃላፊነትን መውሰድ የሚችልና ወደ ሌላ ሰው የማይገፋ ነው
12) አገልጋይ እርምጃ ለመውሰድ የማይፈራ ነው - ሪስክ ወሳጅ ነው
13) አገልጋይ ዋጋ ለመክፈል የማይሣሳ ነው
14) አገልጋይ የሚያደርገውን ለጌታ ክብርና ለሰዎች ጥቅም የሚያደርግ ነው
15) አገልጋይ ብድራቱን ከሰው ሳይሆን ከጌታ የሚጠብቅ ነው / ቆላ. 3፡24
"አገልጋይና አገልግሎቱ" በሚል ርዕስ በኮንቱላ ሜትሮቻፕል በፓስተር ታምራት ኃይሌ የተሰጠ የአገልጋዮች ትምህርት ክፍል 1።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 2 ዜና 29፡11
ስለፀጋ ሥጦታዎች የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡
1 ቆሮ. 12፡8-10፣ ሮሜ 12፡6-8፣ ኤፌ. 4፡11
ስለሌሎች የጸጋ ሥጦታዎች የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 1 ቆሮ. 14፡26፣ ሐዋ. 2፡17፣ ዘካ. 12፡10፣ 1 ጢሞ. 2፡3፣ ማቴ. 19
አገልጋይና የጸጋ ሥጦታዎች
1) የዳነ ሰው ሁሉ አንድና ከዚያ በላይ የጸጋ ሥጦታ አለው
2) በፀጋ ሥጦታ አለማገልገል ተጠያቂነትን ያስከትላል
3) ለአገልግሎት መሰማራት ያለብን በፀጋ ስጦታችን መሠረት መሆን አለበት።
4) የአገልግሎት ፀጋችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ማደግ አለበት
5) በትህትናና በትጋት ባገለገልን መጠን ፀጋችን በቁጥር ይጨምራል
"መልካም እረኛ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ መዝ. 23፣ ዮሐ. 10፡1-18
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ህዝ.34፡23-24፣ ዕብ. 13፡20-21፣ 1 ጴጥ. 5፡4-7፣ ማቴ. 9፡36-38፣ ሉቃ. 12፡32
From the publisher's feed
Ranked by our users in the last 21 days