Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
June 25, 2025የብር ምንዛሪ ተመን እየላሸቀ ሲሔድ የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ድጎማ አስቀረ-ከዚያስ?የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዳጅ ግብይት ያደርግ የነበረውን “ጥቅል ድጎማ” ከግንቦት ወር ጀምሮ አቁሟል። እርምጃው ኢትዮጵያውያን ቤንዚን እና ናፍጣን የመሳሰሉ የነዳጅ ውጤቶች ሲገዙ የዓለም ገበያ ዋጋን እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው። የድጎማ መቅረት ለመንግሥት ወጪ ፋታ የሚሰጥ ቢሆንም በገበያው ወደ ሸማቾች የሚተላለፍ ጫና ሊያስከትል ይችላል።11 minPlay
June 18, 2025የኢትዮጵያ መንግሥት የዋጋ ግሽበትን የተመለከቱ አሐዞች የገበያውን እውነታ ምን ያክል ያሳያሉ?የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት በግንቦት ወር የዋጋ ግሽበት 14.4% ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል። ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር እንቁላል፣ አትክልት፣ ሥጋ እና ስኳርን መሰል ግብዓቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። የዋጋ ግሽበት 34.5% ከደረሰበት ከ2014 ወዲህ በከፍተኛ መጠን ቢቀንስም የኑሮ ውድነት አሁንም ሸማቾችን በኃይል እየተፈታተነ ይገኛል።13 minPlay
June 11, 2025ከኢትዮጵያ የ2018 አጠቃላይ በጀት 24 በመቶ ገደማ ለዕዳ ክፍያ ተመደበከ2018 የኢትዮጵያ 1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት 463 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ ተመድቧል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት “የተሟላ” የሚሉት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ያተኮረው በጀት ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች ገንዘብ አልመደበም። በቀጣዩ ዓመት 1.2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ከሀገር ውስጥ ለመሰብሰብ አዳዲስ የታክስ ፖሊሲዎች ሥራ ላይ እንደሚያውል መንግሥት አስታውቋል።11 minPlay
June 04, 2025የዶናልድ ትራምፕ ታክስ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚላከውን ሐዋላ ወደ ኢ-መደበኛው ገበያ ሊገፋ ይችላልበአሜሪካ የሚኖሩ የውጪ ሀገር ሰዎች ሐዋላ ሲልኩ 3.5 በመቶ ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ የሕግ ረቂቅ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ የሴኔቱን ይኹንታ እየጠበቀ ነው። ሕጉ ተግባራዊ ከሆነ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአሜሪካ ሐዋላ በሚቀበሉ በርካታ ሃገራት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።14 minPlay
May 28, 2025የኢትዮጵያ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለውጥ ለገበሬዎች ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?ከ60,000 በላይ የልማት ሠራተኞች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት መሠረታዊ ለውጥ የሚያደርግበት ምዕራፍ ላይ ነው። አገልግሎቱ እስከ ቀበሌ የተዘረጋ መዋቅር ቢኖረውም ውጤታማ አይደለም። መንግሥት ተቆጣጥሮት የቆየውን አገልግሎት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር የግሉን ዘርፍ ጨምሮ ለሌሎች ተዋንያን አሳልፎ ለመስጠት ቆርጧል።13 minPlay
May 21, 2025የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በሥራ ላይ ከሚገኙ ባንኮች አንዱን መግዛት ይፈልጋልየኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ “ቅርንጫፍ ለመክፈት ወይም አዲስ ለማቋቋም” ሳይሆን በሥራ ላይ ከሚገኙት አንዱን መግዛት ይፈልጋል። በታኅሳስ 2018 ገደማ የውጪ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። መጪዎቹ ወራት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ በርከት ያሉ ለውጦች የሚያይበት ይመስላል።11 minPlay
May 14, 2025አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ቀነሱአሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ለ90 ቀናት በከፍተኛ መጠን ቀንሰዋል። ሁለቱ የንግድ ከባድ ሚዛን ተፋላሚዎች ታሪፍ የቀነሱት ከጥቂት ቀናት ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው በተስማሙት መሠረት ነው። በሥምምነቱ መሠረት የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወደ አሜሪካ ገበያ በሚገቡ የቻይና ሸቀጦች ላይ የጣለውን ታሪፍ ከ145 በመቶ ወደ 30 በመቶ ይቀንሳል። ቻይና በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ የጣለችው ታሪፍ በአንጻሩ ከ125 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ይላል። ዶናልድ ትራምፕ በታሪፍ የጀመሩት የንግድ ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያቀዛቅዝ አስግቶ ነበር።10 minPlay
May 07, 2025የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ክልሎች የሚሰበስቡት ግብር በሚያዝያ ወር “ከትሪሊዮን ብር ይሻገራል”የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እስከ ሚያዝያ 2017 ድረስ ባሉት ዘጠኝ ወራት ፌድራል መንግሥት እና ክልሎች ከታክስ የሰበሰቡት ገቢ ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ ፌድራል መንግሥት 720 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል። የታክስ ገቢ ከ2016 ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር በ279 ቢሊዮን ብር ቢልቅም ወይዘሮ ዓይናለም በቂ ነው የሚል ዕምነት የላቸውም። በ2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት 1.5 ትሪሊዮን ብር በግብር መልክ የመሰብሰብ ዕቅድ አለው። ከዚህ ውስጥ የፌድራል መንግሥት 900 ቢሊዮን ብር፤ የክልል መንግሥታት በአንጻሩ 600 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ይጠበቅባቸዋል።10 minPlay
April 30, 2025የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚመሩ ሹማምንት በዋሽንግተን ምን አሉ?የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የጸደይ ጉባኤ በዋሽንግተን ሲካሔድ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት መንግሥታቸው ተግባራዊ ስለሚያደርገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ውጤቶቹ ማብራሪያ ሲሰጡ ሰንብተዋል። ኢትዮጵያ የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ እየጠበቀች ለመሠረተ-ልማት ግንባታ አማራጭ የገንዘብ ምንጭ እያፈላለገች ነው።11 minPlay
April 23, 2025የትራምፕ ታሪፍ የዓለምን ኢኮኖሚ ዕድገት እንዳቀዛቀዘ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ አሳየዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለዓለም ዋና ዋና ኢኮኖሚዎች በጥር የሰጠውን የዕድገት ትንበያ የዶናልድ ትራምፕ ታሪፍ ባስከተለው ውጥረት ምክንያት ከልሷል። ተቋሙ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በ6.6% ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይፋ አድርጓል። ትንበያው የኢትዮጵያ መንግሥት በ2017 ከሚጠብቀው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በ1.8 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።11 minPlay