Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።... more
FAQs about ከኤኮኖሚው ዓለም:How many episodes does ከኤኮኖሚው ዓለም have?The podcast currently has 100 episodes available.
February 19, 2025የኢትዮጵያ ቦንድ ባለቤቶች የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትን ሪፖርት ለምን ተቃወሙ?ኢትዮጵያ የገጠማት የዕዳ ጫና የመክፈያ ጊዜ በማራዘም የሚፈታ የአጭር ጊዜ የገንዘብ እጥረት ወይስ የተለቃችውን ብድር ለመቀነስ የሚያስገድድ የመክፈል ችግር? ጉዳዩ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማስፋፋት እና ስኳር ፋብሪካዎች ለመገንባት ሲነሳ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያበደሩ የግል ኢንቨስተሮችን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሪፖርት እያወዛገበ ነው።...more10minPlay
February 12, 2025ኢትዮጵያ የመረጠችው የሊብራል ኢኮኖሚ ሥርዓት ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል ከባቢ አለ?ኢትዮጵያ በታሪኳ ከየትኛውም ጊዜ በላይ አሁን የበለጠ ወደ ሊብራል የኢኮኖሚ ሥርዓት ማዘንበሏን ባለሙያዎች ይስማማሉ። ሊብራል የኤኮኖሚ ሥርዓት ግለሰቦች ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት በነጻ እንዲገበያዩ የሚፈቅድ ነው። ሊብራል ኤኮኖሚ በኢትዮጵያ ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል የፖለቲካ ሥርዓት እና ጠንካራ የግል ዘርፍ አለ?...more11minPlay
February 05, 2025የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪፍን እንደ መሣሪያ የመጠቀም ሥልት የዓለም የንግድ ሥርዓትን አስግቷልየአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገራቸዉን የንግድ ጉድለት ለማሟላት እና ፖለቲካዊ ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም ታሪፍን እንደ መሣሪያ እየተጠቀሙ ነው። አሜሪካ ከሜክሲኮ እና ከካናዳ በምትሸምታቸው ሸቀጦች ላይ 25 በመቶ ታሪፍ እንዲጣል ትራምፕ ያስተላለፉት ውሳኔ ለ30 ቀናት እንዲቆም ተደርጓል። በቻይና ላይ የተጣለው ታሪፍ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን የፕሬዝደንት ሺ ዢፒንግ መንግሥት በአጸፋው በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ተመሣሣይ እርምጃ ወስዷል። ቻይና ጉዳዩን ወደ የዓለም የንግድ ድርጅት እንደምትወስድ ዝታለች። የዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ የታሪፍ ውጥረት የፈጠሩ ሀገራት አደብ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።...more10minPlay
January 29, 2025የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ?ባለፉት አምስት አመታት አሜሪካ ለኢትዮጵያ 7.6 ቢሊዮን ዶላር ሰጥታለች። ባለፈው ዓመት ብቻ ግጭት፣ ድርቅ እና የምግብ ዋስትና እጦት ለገጠማቸው ኢትዮጵያውያን የሕይወት አድን ርዳታ ለማቅረብ አሜሪካ 676 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች። ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የምትሰጠው ርዳታ ለ90 ቀናት እንዲቆም ያሳለፉት ውሳኔ ካሁኑ ተጽዕኖ አሳድሯል። ትራምፕ በጎርጎሮሳዊው 2020 በታላቁ የኅዳሴ ግድብ መዘዝ የሚነታረኩትን ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ለማደራደር ሞክረው ሲከሽፍባቸው አዲስ አበባን ያስቆጣ አስተያየት ሰጥተው ነበር።...more12minPlay
January 22, 2025ዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ስለ ኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ ምን አሉ?የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ ለዜጎች ፈታኝ ቢሆንም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዓለም ባንክ በጥሩ ሁኔታ እየተካሔደ ነው የሚል እምነት አላቸው። ዓለም ባንክ ያለፈው ዓመት የማክሮ ኤኮኖሚ ማሻሻያ ለሀገሪቱ ምጣኔ ሐብት ዕድገት ጥቅም እንደሚኖረው አስታውቋል። የማሻሻያውን አፈጻጸም የገመገመው አይኤምኤፍ 248 ሚሊዮን ዶላር ለመንግሥት ለቋል።...more11minPlay
January 15, 2025በኢትዮጵያ የንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል?ኢትዮጵያውያን በቤት እና በመሬት ግብር የሚከፍሉበት የንብረት ታክስ በተቃዋሚዎች ኃይለኛ ትችት ቢገጥመውም በአራት ተቃውሞ እና በአስር ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽጸድቋል። ተቃዋሚዎች አዲሱ ታክስ በሸማቾች ላይ ጫና እንደሚፈጠር አስጠንቅቀዋል። መንግሥት “ፍትኃዊ የሀብት ክፍፍል የሚያሰፍን” ያለው የንብረት ታክስ በክልሎች ይሰበሰባል። ለመሆኑ በንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል? የማይከፍሉትስ እነ ማን ናቸው?...more11minPlay
January 08, 2025ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ማመንጫዎች እና መሠረተ-ልማቶች ግንባታ 14 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታልኢትዮጵያ ከናፍጣ ከሚመነጭ ብርሀን ከተዋወቀች ከ127 ዓመታት ገደማ በኋላም በሺሕዎች የሚቆጠሩ ቀበሌዎች አሁንም ጭለማ ውስጥ ናቸው። ኃይል የማስፋፋት ኃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኪሳራ ተጭኖታል። ሀገሪቱ እየጨመረ የሚሔደውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ የኃይል ማመንጫዎች፣ ማስተላለፊያ እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለመገንባት 14 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ያስፈልጋታል።...more11minPlay
December 25, 2024የኢትዮጵያ የዕዳ ዘላቂነት ትንተና በዓለም ባንክ ባለሙያዎች ጥያቄ ተነሳበትዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና ዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (IDA) ያጸደቁት የኢትዮጵያ የዕዳ ዘላቂነት ትንተና በዓለም ባንክ ባለሙያዎች ጥያቄ ተነስቶበታል። እስከ 2023 የኢትዮጵያ የውጪ ዕዳ 33.2 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የ3 ቢሊዮን ዩሮ የዕዳ አከፋፈል ማሻሻያ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።...more10minPlay
FAQs about ከኤኮኖሚው ዓለም:How many episodes does ከኤኮኖሚው ዓለም have?The podcast currently has 100 episodes available.