Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።... more
FAQs about ከኤኮኖሚው ዓለም:How many episodes does ከኤኮኖሚው ዓለም have?The podcast currently has 100 episodes available.
July 30, 2025የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ሥርዓት ለውጥ በዓመቱ ምን አሳካ?የኢትዮጵያ መንግሥት የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ካደረገ ወዲህ የሸቀጦች የወጪ ንግድ እና ሐዋላን ጨምሮ ሀገሪቱ 32 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። በለውጡ ብር ዶላርን ከመሳሰሉ የመገበያያ ገንዘቦች ያለው የምንዛሪ ተመን እየተዳከመ ሲሔድ እንደ ነዳጅ ያሉ ሸቀጦች ዋጋ እየጨመረ የሸማቾችን አቅም እየተፈታተነ ይገኛል።...more12minPlay
July 16, 2025ኢትዮጵያ ተስፋ የጣለችበት የካፒታል ገበያ ፍሬ መቼ ይታያል?የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በደረሰበት ምዕራፍ መንግሥት እና የዘርፉ ተዋንያን ከፍ ያለ ተስፋ ሰንቀዋል። ገበያው የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነዶች፣ የወጋገን እና የገዳ ባንኮችን አክሲዮኖች መዝግቦ ለሁለተኛ ገበያ አቅርቧል። ባለሙያዎች “ፈጣን ግብይት” እስኪፈጠር መታገስ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። ነገር ግን “ቀስ በቀስ እያደገ ካልመጣ ሊሞት ይችላል” የሚል ሥጋትም አለ።...more13minPlay
July 09, 2025ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፊቷን ከያዮ እና ድሬዳዋ ወደ ጎዴ አዞረችሜቴክ በያዮ የጀመረው የማዳበሪያ ፋብሪካ ኢትዮጵያን በቢሊዮን ብሮች አክስሮ ገበሬ አስለቅሶ ቆሟል። በሞሮኮ ኩባንያ በድሬዳዋ ሊገነባ የታቀደው ከወረቀት አልዘለለም። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በሶማሌ ክልል በምትገኘው ጎዴ ከተፈጥሮ ጋዝ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተስፋውን በናይጄሪያዊው ባለጠጋ አሊኮ ዳንጎቴ ላይ አሳርፏል።...more10minPlay
July 02, 2025የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የማስተማሪያ ሆስፒታሎች በጀት መፈተሽ እንዳለበት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናገሩየኢትዮጵያ መንግሥት ለ2018 ለትምህርት 114.7 ቢሊዮን ብር መድቧል። በትምህርት ሚኒስቴር ሥር ለሚገኙ 47 ዩኒቨርሲቲዎች ለመደበኛ እና ካፒታል ወጪ በጠቅላላ የተመደበው 106 ቢሊዮን ብር ገደማ ነው። ግንባታቸው ያልተጠናቀቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የማስተማሪያ ሆስፒታሎች የበጀት ጉዳይ ግን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መነጋገሪያ ሆኗል።...more10minPlay
June 25, 2025የብር ምንዛሪ ተመን እየላሸቀ ሲሔድ የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ድጎማ አስቀረ-ከዚያስ?የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዳጅ ግብይት ያደርግ የነበረውን “ጥቅል ድጎማ” ከግንቦት ወር ጀምሮ አቁሟል። እርምጃው ኢትዮጵያውያን ቤንዚን እና ናፍጣን የመሳሰሉ የነዳጅ ውጤቶች ሲገዙ የዓለም ገበያ ዋጋን እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው። የድጎማ መቅረት ለመንግሥት ወጪ ፋታ የሚሰጥ ቢሆንም በገበያው ወደ ሸማቾች የሚተላለፍ ጫና ሊያስከትል ይችላል።...more11minPlay
June 18, 2025የኢትዮጵያ መንግሥት የዋጋ ግሽበትን የተመለከቱ አሐዞች የገበያውን እውነታ ምን ያክል ያሳያሉ?የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት በግንቦት ወር የዋጋ ግሽበት 14.4% ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል። ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር እንቁላል፣ አትክልት፣ ሥጋ እና ስኳርን መሰል ግብዓቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። የዋጋ ግሽበት 34.5% ከደረሰበት ከ2014 ወዲህ በከፍተኛ መጠን ቢቀንስም የኑሮ ውድነት አሁንም ሸማቾችን በኃይል እየተፈታተነ ይገኛል።...more13minPlay
June 11, 2025ከኢትዮጵያ የ2018 አጠቃላይ በጀት 24 በመቶ ገደማ ለዕዳ ክፍያ ተመደበከ2018 የኢትዮጵያ 1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት 463 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ ተመድቧል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት “የተሟላ” የሚሉት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ያተኮረው በጀት ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች ገንዘብ አልመደበም። በቀጣዩ ዓመት 1.2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ከሀገር ውስጥ ለመሰብሰብ አዳዲስ የታክስ ፖሊሲዎች ሥራ ላይ እንደሚያውል መንግሥት አስታውቋል።...more11minPlay
June 04, 2025የዶናልድ ትራምፕ ታክስ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚላከውን ሐዋላ ወደ ኢ-መደበኛው ገበያ ሊገፋ ይችላልበአሜሪካ የሚኖሩ የውጪ ሀገር ሰዎች ሐዋላ ሲልኩ 3.5 በመቶ ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ የሕግ ረቂቅ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ የሴኔቱን ይኹንታ እየጠበቀ ነው። ሕጉ ተግባራዊ ከሆነ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአሜሪካ ሐዋላ በሚቀበሉ በርካታ ሃገራት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።...more14minPlay
May 28, 2025የኢትዮጵያ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለውጥ ለገበሬዎች ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?ከ60,000 በላይ የልማት ሠራተኞች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት መሠረታዊ ለውጥ የሚያደርግበት ምዕራፍ ላይ ነው። አገልግሎቱ እስከ ቀበሌ የተዘረጋ መዋቅር ቢኖረውም ውጤታማ አይደለም። መንግሥት ተቆጣጥሮት የቆየውን አገልግሎት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር የግሉን ዘርፍ ጨምሮ ለሌሎች ተዋንያን አሳልፎ ለመስጠት ቆርጧል።...more13minPlay
FAQs about ከኤኮኖሚው ዓለም:How many episodes does ከኤኮኖሚው ዓለም have?The podcast currently has 100 episodes available.