Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።... more
FAQs about ከኤኮኖሚው ዓለም:How many episodes does ከኤኮኖሚው ዓለም have?The podcast currently has 100 episodes available.
May 21, 2025የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በሥራ ላይ ከሚገኙ ባንኮች አንዱን መግዛት ይፈልጋልየኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ “ቅርንጫፍ ለመክፈት ወይም አዲስ ለማቋቋም” ሳይሆን በሥራ ላይ ከሚገኙት አንዱን መግዛት ይፈልጋል። በታኅሳስ 2018 ገደማ የውጪ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። መጪዎቹ ወራት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ በርከት ያሉ ለውጦች የሚያይበት ይመስላል።...more11minPlay
May 14, 2025አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ቀነሱአሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ለ90 ቀናት በከፍተኛ መጠን ቀንሰዋል። ሁለቱ የንግድ ከባድ ሚዛን ተፋላሚዎች ታሪፍ የቀነሱት ከጥቂት ቀናት ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው በተስማሙት መሠረት ነው። በሥምምነቱ መሠረት የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወደ አሜሪካ ገበያ በሚገቡ የቻይና ሸቀጦች ላይ የጣለውን ታሪፍ ከ145 በመቶ ወደ 30 በመቶ ይቀንሳል። ቻይና በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ የጣለችው ታሪፍ በአንጻሩ ከ125 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ይላል። ዶናልድ ትራምፕ በታሪፍ የጀመሩት የንግድ ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያቀዛቅዝ አስግቶ ነበር።...more10minPlay
May 07, 2025የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ክልሎች የሚሰበስቡት ግብር በሚያዝያ ወር “ከትሪሊዮን ብር ይሻገራል”የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እስከ ሚያዝያ 2017 ድረስ ባሉት ዘጠኝ ወራት ፌድራል መንግሥት እና ክልሎች ከታክስ የሰበሰቡት ገቢ ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ ፌድራል መንግሥት 720 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል። የታክስ ገቢ ከ2016 ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር በ279 ቢሊዮን ብር ቢልቅም ወይዘሮ ዓይናለም በቂ ነው የሚል ዕምነት የላቸውም። በ2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት 1.5 ትሪሊዮን ብር በግብር መልክ የመሰብሰብ ዕቅድ አለው። ከዚህ ውስጥ የፌድራል መንግሥት 900 ቢሊዮን ብር፤ የክልል መንግሥታት በአንጻሩ 600 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ይጠበቅባቸዋል።...more10minPlay
April 30, 2025የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚመሩ ሹማምንት በዋሽንግተን ምን አሉ?የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የጸደይ ጉባኤ በዋሽንግተን ሲካሔድ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት መንግሥታቸው ተግባራዊ ስለሚያደርገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ውጤቶቹ ማብራሪያ ሲሰጡ ሰንብተዋል። ኢትዮጵያ የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ እየጠበቀች ለመሠረተ-ልማት ግንባታ አማራጭ የገንዘብ ምንጭ እያፈላለገች ነው።...more11minPlay
April 23, 2025የትራምፕ ታሪፍ የዓለምን ኢኮኖሚ ዕድገት እንዳቀዛቀዘ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ አሳየዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለዓለም ዋና ዋና ኢኮኖሚዎች በጥር የሰጠውን የዕድገት ትንበያ የዶናልድ ትራምፕ ታሪፍ ባስከተለው ውጥረት ምክንያት ከልሷል። ተቋሙ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በ6.6% ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይፋ አድርጓል። ትንበያው የኢትዮጵያ መንግሥት በ2017 ከሚጠብቀው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በ1.8 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።...more11minPlay
March 26, 2025የኢትዮጵያ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለዕዳ ሽግሽግ ድርድር እንዲዘጋጁ ገንዘብ ሚኒስቴር አሳሰበገንዘብ ሚኒስቴር “ዋና ዋና” ላላቸው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከአበዳሪ መንግሥታት ጋር ለሚደረግ የመግባቢያ ሥምምነት ድርድር እንዲዘጋጁ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። የገንዘብ ሚኒቴር ተቋማቱ እንዲዘጋጁ ያሳሰበው ኢትዮጵያ አበዳሪዎቿን ከሚወክለው ኮሚቴ ጋር የ8.4 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ዕዳ ለማሸጋሸግ “በመርኅ ደረጃ” ሥምምነት ላይ ከደረሰች በኋላ ነው። ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር የተደረሰው ሥምምነት በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ከ2023 እስከ 2028 ባሉት ዓመታት ለኢትዮጵያ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የዕዳ ክፍያ እፎይታ ይሰጣል።...more11minPlay
March 19, 2025ለኢትዮጵያ ከዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ምን አለ?የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሀገራት በቡድን ከኢትዮጵያ ልዑካን ጋር የተደራደሩበት አምስተኛ ስብሰባ ዛሬ በጄኔቫ ተካሒዷል። ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የጀመረችውን ሒደት ለማጠናቀቅ ወደ ጄኔቫ የተመለሰችው “በተቋሙ ላይ ከፍተኛ ጥያቄ” በሚነሳበት ወቅት ነው። ባለፉት ዓመታት የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሀገራት ብሔራዊ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ እና ተገዳዳሪዎቻቸውን ለመቅጣት የድርጅቱን ሕግጋት እየጣሱ መሔዳቸውን ባለሙያዎች ታዝበዋል።...more11minPlay
March 12, 2025የአፍሪካ መንግሥታት የናጠጡ ባለጠጎችን የሐብት ግብር ማስከፈል አለባቸው?በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ብርቱ የኢኮኖሚ ፈተናዎች እየገጠሟቸው ነው። መንግሥታት የተሻለ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ፣ ትምህርት ቤቶች፣ መንገዶች እና ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ለመገንባት የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ ለማግኘት ሲቸገሩ የአፍሪካ ሀገራት በየጊዜው እየጨመረ በሚሔድ የዕዳ ጫና እየቃተቱ ነው። ላለፉት በርካታ ዓመታት የአፍሪካ መንግሥታት በአማካይ ለጤና አገልግሎት ከመደቡት የበለጠ ለዕዳ ክፍያ ወጪ አድርገዋል። በአኅጉሪቱ የናጠጡ ባለጠጎች ቁጥር ሲጨምር የሐብት ግብር ማስከፈል እንዲጀመር የሚደረጉ ጥሪዎችም ከፍ ብለው መሰማት ጀምረዋል።...more10minPlay
March 05, 2025የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ፊቱን ወደ ገበያ ተመን አዞረለዓመታት ለመንግሥት “ርካሽ” ብድር ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሠረታዊ የወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ተግባራዊ ሲያደርግ ፊቱን ወደ ገበያ ተመን አዙሯል። ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም ከውጪ ምንዛሪ ግኝት ጋር በተያያዘ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ደንበኞቹ የሚያቀርባቸውን ጥቅማ ጥቅሞች በመተው ለወጪ ንግድ በሚሰጠው ብድር የሚያስከፍለውን ወለድ አሳድጓል። በማሻሻያው የግብርና ብድር ወለድ በመጠኑ ሲቀንስ የኮንዶሚኒየም የመኖሪያ ቤቶች በነበረበት ቀጥሏል። ንግድ ባንክ ከአርብ ጀምሮ ለቤት መግዣ በ14 በመቶ ለተሽከርካሪ በ15 በመቶ ወለድ ያበድራል።...more11minPlay
FAQs about ከኤኮኖሚው ዓለም:How many episodes does ከኤኮኖሚው ዓለም have?The podcast currently has 100 episodes available.