Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።... more
FAQs about ከኤኮኖሚው ዓለም:How many episodes does ከኤኮኖሚው ዓለም have?The podcast currently has 109 episodes available.
December 10, 2025በኢትዮጵያ ምርጫ ሲቃረብ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እያደላ ነውየኢትዮጵያ ሰባተኛ ምርጫ በመካሔድ ላይ የሚገኙ ግጭቶች፣ የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ እና የተቃዋሚዎች መዳከም አጥሎበታል። ገዥው ብልጽግና ፓርቲ እንደ ስኬት የሚቆጥራቸውን ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አጉልቶ ለማቅረብ ሲጥር ይታያል። የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት እና የድሕነት መጨመርን የመሳሰሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ክርክር ሊደረግባቸው የሚገባ ጉዳዮች ናቸው።...more11minPlay
November 26, 2025የኢትዮጵያ እና የጀርመን ቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሔደየኢትዮጵያ እና የጀርመን ኩባንያዎችን ከመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከልማት ድርጅቶች የሚያገናኘው የቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሒዷል። መርሐ-ግብሩ በታዳሽ ኃይል፣ በግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ እና በዲጂታላይዜሽን ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎች የተጋበዙበት ነው።...more10minPlay
November 19, 2025የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አምስት ተጨማሪ ኩባንያዎች እያቋቋመ ነውየኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የመማሪያ መጻሕፍት አታሚ ድርጅት እና የወጣቶች የኢንቨስትመንት ባንክ ጨምሮ በዚህ ዓመት አምስት ኩባንያዎች እንደሚያቋቁም አሳውቋል። ከሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነቶች የተፈራረመው ተቋም ከ2011 ጀምሮ የስኳር ፋብሪካዎች ለመሸጥ ሲደረግ የነበረው ጥረት አቋርጧል።...more14minPlay
November 12, 2025በሰኔ ይጠናቀቃል የተባለው የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ወጪ ስንት ነው?በ2.5 ቢሊዮን ብር የመነሻ ዋጋ ተጀመረው የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በጀት 20.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን የፌድራል ሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሰነድ አሳይቷል። ለግንባታው በ2018 በጀት ውስጥ ከ4.9 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቧል። መንግሥት 13 ዓመታት የተጓተተው ግንባታ በስምንት ወራት እንደሚጠናቀቅ ገልጿል።...more11minPlay
November 05, 2025የኢትዮጵያ ክልሎች እና ከተሞች የማዘጋጃ ቤት ቦንድ ቢያወጡ ማን ያበድራቸዋል?የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሰነድ የክልል መንግሥታት እና የከተማ መስተዳድሮች ቦንድ በማውጣት ከገበያው የሚበደሩበት ሥርዓት የመዘርጋት ፍላጎት እንዳለው ፍንጭ ሰጥቷል። የማዘጋጃ ቤት ወይም የከተማ አስተዳደር ቦንዶች ለመሠረተ-ልማት ግንባታ የሚያስፈልግ ገንዘብ ለመበደር የሚያገለግሉ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ክልል በቁልፍ የልማት ዘርፎች ረገድ ያለባቸውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ ቦንድ በማውጣት ከገበያው የመበደር ፍላጎት እንዳላቸው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በቅርቡ ይፋ ያደረገው አንድ ጥናት አሳይቷል።...more11minPlay
October 29, 2025የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዳሉት “ከ23 ቢሊዮን ዶላር አይበልጥም”?ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ከ23 ቢሊዮን ዶላር እንደማይበልጥ ተናግረዋል። የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የዕዳ ዘላቂነት ትንተና በአንጻሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተበደሩትን ጨምሮ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ 31.7 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ያሳያል።...more12minPlay
October 22, 2025የዶላር ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ሣምንት ብቻ ከአምስት ብር በላይ ጨመረባለፈው አንድ ሣምንት ንግድ ባንክ ዶላር የሚገዛበት እና የሚሸጥበት ተመን አምስት ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ከፍ ብሏል። የብሔራዊ ባንክ አመልካች ዕለታዊ የምንዛሪ ተመን በአንጻሩ 150 ብር ከ90 ሳንቲም ደርሷል። ብር በውጭ ምንዛሪ ገበያው መዳከሙን ሲቀጥል ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ለመውሰድ በድጋሚ ዝቷል።...more11minPlay
October 15, 2025የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስር የውጪ ምንዛሪ ጨረታዎች ምን አሳኩ?የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ከተደረገ ወዲህ ባካሔዳቸው ጨረታዎች ከ690 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለባንኮች አከፋፍሏል። ጨረታዎቹ በትይዩ ገበያ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የውጪ ምንዛሪ ገበያውን ማረጋጋት ቢችሉም ዋንኛ ዓላማቸውን ያሳኩ አይመስልም። በመደበኛ እና ትይዩ ገበያዎች የምንዛሪ ተመን ሲጨምር ልዩነታቸው አልጠበበም።...more11minPlay
October 08, 2025የኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ፕሮጀክት እንደ ቀደሙት ሙከራዎች ያሰጋል?የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሌ ክልል ያስጀመረውን የነዳጅ ልማት ፕሮጀክት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር አንድ አንጃ ተቃውሟል። ኦብነግ ፕሮጀክቱ “ምክክር” እንዳልተደረገበት እና ሕዝቡ “ፈቃዱን እንዳልሰጠ” ተችቷል። ከዚህ ቀደም በነዳጅ ፍለጋ ወቅት ከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያስታውሱ ተመራማሪዎች አዲሱ ፕሮጀክት “ጥንቃቄ” እንደሚሻ ይመክራሉ።...more11minPlay
FAQs about ከኤኮኖሚው ዓለም:How many episodes does ከኤኮኖሚው ዓለም have?The podcast currently has 109 episodes available.