ገንዘብ ሚኒስቴር “ዋና ዋና” ላላቸው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከአበዳሪ መንግሥታት ጋር ለሚደረግ የመግባቢያ ሥምምነት ድርድር እንዲዘጋጁ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። የገንዘብ ሚኒቴር ተቋማቱ እንዲዘጋጁ ያሳሰበው ኢትዮጵያ አበዳሪዎቿን ከሚወክለው ኮሚቴ ጋር የ8.4 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ዕዳ ለማሸጋሸግ “በመርኅ ደረጃ” ሥምምነት ላይ ከደረሰች በኋላ ነው። ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር የተደረሰው ሥምምነት በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ከ2023 እስከ 2028 ባሉት ዓመታት ለኢትዮጵያ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የዕዳ ክፍያ እፎይታ ይሰጣል።