ከኤኮኖሚው ዓለም

ከኤኮኖሚው ዓለም

Download on the App Store

ከኤኮኖሚው ዓለም episodes

  • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዕዳ ክፍያ በኢትዮጵያውያን ትከሻ ላይ ተጫነ?
    ገንዘብ ሚኒስቴር የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን 845.3 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ ከነወለዱ ለመክፈል ተረክቧል። መንግሥት ንግድ ባንክን ለመታደግ በተከተለው አካሔድ ትምህርት እና ጤና የመሳሰሉ አገልግሎቶች ለመሥራት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለዕዳ ክፍያ ሊያውል አሊያም ገቢውን ለማሳደግ ተጨማሪ ግብር ሊያስከፍል እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።
    12 min
  • ኢትዮጵያውያን የአፍሪካ ኮምት ተሳታፊዎች በጀርመን በቀሰሙት ልምድ ሀገራቸውን ለመጥቀም ተስፋ ሰንቀዋል
    አራት ኢትዮጵያውያን አፍሪካ ኮምት በተባለው እና በጎርጎሮሳዊው ከ2023 እስከ 2025 በሚዘልቀው መርሐ-ግብር በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ይኸ መርሐ-ግብር አፍሪካውያን ወጣት ባለሙያዎችን ከሥመ -ጥር የጀርመን ኩባንያዎች የሚያገናኝ ነው። ገነት አታክልት እና ጌቱ ታደለ በሁለት ግዙፍ የጀርመን ኩባንያዎች ውስጥ ለስምንት ወራት እየሰሩ ሲማቁ ቆይተዋል።
    12 min
  • በኢትዮ-ቴሌኮም መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ ልብ መባል ያለባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?
    የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢትዮ-ቴሌኮምን መደበኛ አክሲዮን ሽያጭ ከጀመረ በኋላ የኩባንያውን ያለፈ ዓመት ገቢ እና ትርፍ በማስላት “ያዋጣል” ወይስ “አያዋጣም” የሚሉ ትንታኔዎች በማኅበራዊ ድረ-ገጾች እና በመገናኛ ብዙኃን እየታዩ ነው። መንግሥት ከመደበኛ አክሲዮኖች ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር (255 ሚሊዮን ዶላር) የማግኘት ዕቅድ ያለው ሲሆን ወደፊት የኢትዮ-ቴሌኮም 45 በመቶ ድርሻ ለውጪ ባለወረቶች ይሸጣል ተብሎ ይጠበቃል። ለመሆኑ ልብ መባል ያለባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? ባለሙያዎችስ ምን ይመክራሉ?
    11 min
  • የኢትዮጵያ ባንኮች የውጪ ምንዛሪ መሸጫ እና መግዣ ተመን ልዩነት ወደ 2% ቢያጠቡም የሚያስከፍሉትን ኮሚሽን አላሳወቁም
    የኢትዮጵያ ባንኮች በውጪ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ተመኖቻቸው መካከል ያለውን ልዩነት የብሔራዊ ባንክን የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ ወደ 2 በመቶ ዝቅ አድርገዋል። እርምጃው የባንኮች የዶላር የመሸጫ ተመን ከ6 እስከ 10 ብር እንዲቀንስ አድርጎታል። ይሁንና ባንኮቹ በተቆጣጣሪው በታዘዙት መሠረት ለደንበኞቻቸው ከውጪ ምንዛሪ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች ሲያቀርቡ የሚጠይቁትን ክፍያ እና ኮሚሽን ይፋ አላደረጉም።
    11 min
  • የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራተኞች ከሚጠበቀው የደመወዝ ጭማሪ ለምን ተስፋ አጡ?
    መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች የኢትዮጵያ መንግሥት በ91.4 ቢሊዮን ብር ባቀደው የደመወዝ ጭማሪ ደስተኞች አልሆኑም። የመንግሥት “ለኑሮ ውድነት መደጎሚያ የደመወዝ ማሻሻያ” የመከላከያ ሠራዊት እና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ ለ2.4 ሚሊዮን ሠራተኞች የሚደረግ ነው። ዕቅዱ ከተተገበረ ዝቅተኛ ተከፋይ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በ332% ከፍ ይላል። ገንዘብ ሚኒስቴር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን “ተጠንቶ እና ተደግፎ የቀረበው እና በማክሮ ኤኮኖሚ ኮሚቴ የታየው የደመወዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ” መቅረቡን በማኅበራዊ ድረ ገጾች የተሰራጨው ሰነድ ይጠቁማል።
    14 min
  • የኬንያ እና የጀርመን የስደት እና የሰለጠኑ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ሥምምነት
    የሰለጠኑ ኬንያውያን ሠራተኞች በጀርመን መሥራት እና መኖር የሚችሉበት ሥምምነት ባለፈው ሣምንት በበርሊን ከተማ ተፈርሟል። ሥምምነቱ በጀርመን የመኖር ፈቃድ የሌላቸው ኬንያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያደርግ ነው። ኬንያ ለወጣቶቿ አመርቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን 82 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ዕዳዋን ለመክፈል የከበዳት ሀገር ሆናለች።
    11 min
  • ሐዋላን ወደ መደበኛው ሥርዓት ለመመለስ ያቀደው የኢትዮጵያ የ100 ቢሊዮን ብር ዕቅድ ይሳካል?
    ባንኮች ሐዋላ ለሚላክላቸው ደንበኞች እስከ 17 በመቶ የሚደርስ የአዲስ ዓመት ስጦታ ቃል ገብተዋል። የአንዳንዶቹ ባንኮች ስጦታ ከመደበኛው የዶላር ምንዛሪ ሲደመር በተለምዶ ጥቁር ከሚባለው የጎንዮሽ ገበያ የሚያቀራርባቸው ነው። የኢትዮጵያ 31 ባንኮች ሐዋላ ለሚልኩ የ100 ቢሊዮን ብድር ማዘጋጀታቸውን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ይፋ አድርገዋል
    11 min
  • አበዳሪን ከተበዳሪ ያገናኘው የቻይና አፍሪካ ዘጠነኛ የትብብር ፎረም
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ መሪዎች የሚሳተፉበት ዘጠነኛው የቻይና አፍሪካ ፎረም ዛሬ በቤጂንግ ተጀምሯል። ቻይና ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ዋና አበዳሪ ሆናለች። አንጎላ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ናይጄሪያ ከቻይና በቢሊዮኖች ዶላሮች በመበደር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናቸው።
    13 min
  • አምስት ፋብሪካዎች በ2016 ያመረቱት ስኳር ከኢትዮጵያ ፍላጎት 10% ገደማ ብቻ ነው
    ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫ፣ ከሰም እና ጣና በለስ ፋብሪካዎች በ2016 ያመረቱት 124,097 ቶን ስኳር እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዐስታውቋል። ይኸ የሚሸፍነው 10% የኢትዮጵያን የስኳር ዓመታዊ ፍላጎት ብቻ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ኸርነስት ኤንድ ያንግ በተባለ አማካሪ ኩባንያ ያሠራው የገበያ ጥናት የሀገሪቱ የስኳር ፍላጎት በጎርጎሮሳዊው 2020/2021 መጨረሻ 1.2 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያሳያል። መንግሥት እስከ ጥር ስምንት ስኳር ፋብሪካዎችን በመሸጥ የፈሰሳባቸውን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር መመለስ እና የግል መዋዕለ-ንዋይ ወደ ዘርፉ ለመሳብ አቅዷል።
    12 min

About ከኤኮኖሚው ዓለም

From the publisher's feed

በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።