ከኤኮኖሚው ዓለም

ከኤኮኖሚው ዓለም

Download on the App Store

ከኤኮኖሚው ዓለም episodes

  • ደቡብ ኮሪያ እና አፍሪካ አንዳቸው ከሌላው የሚፈልጉት ምንድነው?
    በመጀመሪያው የኮሪያ አፍሪካ ጉባኤ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የኬንያን ጨምሮ 25 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል። ከደቡብ ኮሪያ የወጪ እና ገቢ ንግድ አፍሪካ ያላት ድርሻ ከ2% ያነሰ ነው። የአፍሪካ መሪዎች ደቡብ ኮሪያ ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ ዕድገት እንድታቋድሳቸው ይፈልጋሉ። ደቡብ ኮሪያ በአንጻሩ በአፍሪካ ማዕድናት ላይ አይኗን ጥላለች።
    9 min
  • የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ብድር 65 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል
    የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 65 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ባለፈው ሣምንት ተናግረዋል። ወደ 1.2 ትሪሊዮን ብር ያሻቀበው የመንግሥት የሀገር ውስጥ ብድር “ጫናው፣ ክምችቱ እየጨመረ፣ እየከፋ” ሊሔድ እንደሚችል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አብርሃም ዓለማየሁ አስጠንቅቀዋል። ሀገሪቱ በጦርነት የወደመውን መልሶ ለመገንባት የጀመረችው ጥረትም በታቀደው ፍጥነት ተግባራዊ አልሆነም።
    10 min
  • አዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ምን ይዞ መጣ?
    የኢትዮጵያ ገበሬዎች እና አርብቶ አደሮች በመሬታቸው የመጠቀም መብታቸውን አስይዘው ከባንክ እንዲበደሩ የሚፈቅድ አዋጅ ባለፈው ሣምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል። በአዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ባለመብቶች መሬታቸውን ማከራየት እና ከባለ ሐብቶች ጋር በጋራ ማልማት ጭምር ተፈቅዶላቸዋል።
    12 min
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የወሰደው እርምጃ ለውጥ እያመጣ ነው?
    የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት እንደሚለው በሚያዝያ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት የሚያድግበት ፍጥነት የመለዘብ አዝማሚያ አሳይቶ 23 በመቶ ገደማ ደርሷል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ የታየውን ለውጥ “ታላቅ ዕምርታ” ብለውታል። የምግብ ነክ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት ግን ባለፈው ሚያዝያ ወር 27 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ዳቦ እና ጥራጥሬን የመሳሰሉ ምግቦች ከ2015 ሚያዝያ አኳያ አሁንም ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል።
    10 min
  • በጋዛ የወደመውን መልሶ ለመገንባት እስከ 50 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል
    እስራኤል በጋዛ ለሰባት ወራት ባካሔደችው ወታደራዊ ዘመቻ የወደመውን መልሶ ለመገንባት እስከ 50 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተመድ አስታውቋል። ጦርነቱ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ወደ ድሕነት ሲገፋ ሥራ አጥነት ከ25% ወደ 46 አሻቅቧል። በጦርነቱ የወደሙ መኖሪያ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እስከ 80 ዓመታት ሊወስድ ይችላል።
    9 min
  • ሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለች
    የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ንብረት የሆነው ዱባይ ወርልድ ኩባንያ የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት አቅደዋል። ለዚህም የወደብ አጠቃቀም እና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ሥምምነት በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል መፈረም አለበት። ሥምምቱ በሚቀጥሉት 60 ቀናት ሊፈረም እንደሚችል የሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር ባለሥልጣን ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
    10 min
  • የኢትዮጵያ ገበያ ለውጭ ባለወረቶች ሲፈቀድ ባለሙያዎች ተስፋ እና ሥጋት ተሰምቷቸዋል
    ለኢትዮጵያውያን ተከልለው የቆዩ የወጪ እና ገቢ ንግድ ሥራዎች ለውጭ ባለወረቶች ተፈቅደዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ መመሪያ የውጭ ባለወረቶች በጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ጭምር እንዲሳተፉ የፈቀደ ነው። መንግሥት ለረዥም ዓመታት ሲከተል በቆየው ፖሊሲ ረገድ ያደርገው ለውጥ ለአንዳንድ ባለሙያዎች ተስፋ ለሌሎች ሥጋት ያጫረ ሆኗል።
    11 min
  • የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የኢንቨስተሮችን የድርሻ ድልድል እያካሔደ ነው
    ከ48 ኢንቨስተሮች 1.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያሰባሰበው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የድርሻ ድልድል እያካሔደ ነው። በዚህ ሣምንት የሚጠናቀቀው ድልድል ባለድርሻዎች ምን ዓይነት መብት እንደሚኖራቸው ይወስናል። የናይጄሪያ ኤክስቼንጅ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የቦርድ አባል እንደሚሆኑ አስታውቋል።የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሥራ ሲጀምር ግብይቱ የሚመራበትን ሕገ-ደንብ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ግብይት የሚካሔድበትን ቴክኖሎጂ ለመዘርጋት አቅራቢዎች የሚመርጥበት ደረጃ ላይ ነው።
    10 min
  • የመጀመሪያውን የሙዓለ-ንዋይ አማካሪነት ፈቃድ የተቀበለው ዴሎይት በኢትዮጵያ ገበያ ተስፋ ሰንቋል
    የመጀመሪያውን የሙዓለ ንዋይ አማካሪነት ፈቃድ የተረከበው ዴሎይት በኢትዮጵያ ገበያ ተስፋ ሰንቋል። ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ 900 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖች ከአስር በላይ የግል ባንኮች እና የመድን ድርጅቶች ድርሻ ገዝተዋል። በምሥረታ ላይ የሚገኘው ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሕንጻ ላይ ገበያ ያቆማል።
    10 min
  • ኢትዮጵያ የዕዳ ክፍያ እፎይታዋን ለማዳን የአይኤምኤፍ ባለሙያዎችን የአዲስ አበባ ጉብኝት ውጤት ትጠባበቃለች
    የኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎችን ሥምምነት የሚጠባበቀው የዕዳ ክፍያ እፎይታ “ዋጋ ቢስ” የመሆን ሥጋት ተጋርጦበታል። ኦፊሴያል አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ የሰጡት እፎይታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት 1.5 ቢሊዮን ዶላር በዓመት የሚያድን ነው። ለአንድ ሣምንት የተደረገው የአይ.ኤም.ኤፍ. ባለሙያዎች የአዲስ አበባ ጉብኝት ከዕዳ ክፍያ እፎይታው በተጨማሪ ኢትዮጵያ ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ማስፈጸሚያ በጠየቀችው 3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ላይ ጭምር ተጽዕኖ ይኖረዋል።
    11 min

About ከኤኮኖሚው ዓለም

From the publisher's feed

በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።