ከኤኮኖሚው ዓለም

ከኤኮኖሚው ዓለም

Download on the App Store

ከኤኮኖሚው ዓለም episodes

  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀውስ ለባንኮች የማንቂያ ደወል ይሆን?
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገጠመው ዕክል ለተወሰኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጭር ፌሽታ ቢፈጥርም በባለሙያዎች ዘንድ ጥያቄ አጭሯል። የባንኩ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ያስገደደው ክስተት አንድ ተማሪ 180 የገንዘብ ዝውውር እንዲያደርግ መፍቀዱን አቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል። ተግባራዊ የተደረገው ማሻሻያ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ከነባሩ ሥርዓት ጋር መጣጣም ስለመቻሉ መፈተሽ እንደነበረበት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሶፍትዌር ምኅንድስና ባለሙያ የኢትዮጵያ ባንኮች የሳይበር ጥቃት መቋቋም ለመቻላቸው እርግጠኛ አይደሉም።
    11 min
  • የመንግሥት ተቋማት የሀገር ውስጥ ምርቶች እንዲገዙ የሚደረግ ግፊት ለኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ምን ይፈይዳል?
    የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የመንግሥት ተቋማት ከውጭ ከሚገቡ ሸቀጦች ይልቅ ለሀገር ውስጥ ምርት ቅድሚያ እንዲሰጡ ግፊት እያደረጉ ነው። የማምረቻ ኢንዱስትሪ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ፋይናንስ እና የውጭ ምንዛሪ እጦትን የመሳሰሉ ችግሮች ይፈታተኑታል። ባለፈው ዓመት 450 የሚሆኑ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሥራ አቁመዋል። የሀገር ውስጥ ምርት ከኢትዮጵያ ፍጆታ ያለው ድርሻ 38 በመቶ ነው። የባለሥልጣናቱ ግፊት ምን ይፈይዳል?
    11 min
  • ተደራራቢ ቀውሶች በበረታባት ኢትዮጵያ ለሰብአዊ ርዳታ ከ3.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል
    በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዐሥር ወራት ርዳታ ለማቅረብ 3.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ መንግሥት እና አጋሮቹ ለለጋሾች ያዘጋጁት ዕቅድ አሳይቷል። ዕቅዱ ግጭት፣ የከባቢ አየር ለውጥ ዳፋ እና ወረርሽኞች በተደራረቡባት ኢትዮጵያ ርዳታ በአፋጣኝ እና በዘላቂነት ካልቀረበ ሰብአዊ ቀውስ ሊቀሰቀስ እንደሚችል የሚያስጠነቅቅ ነው።
    11 min
  • የአፍሪካ ልማት ባንክ ሪፖርት በተያዘው ዓመት የአፍሪካ ኤኮኖሚ በ3.2 በመቶ እንደሚያድግ ይተነብያል
    የአፍሪካ ልማት ባንክ የአኅጉሪቱ ምጣኔ ሐብት በ3.2% እንደሚያድግ የተነበየበትን ሪፖርት በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ መሠረት የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በ6.7 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል። ይኸ ትንበያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከሚጠብቀው 7.9 በመቶ ዝቅ ያለ ነው። የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት አኪንዉሚ አዲሺና “አፍሪካ የሚወነጨፍ ዕድገት ያስፈልጋታል” የሚል አቋም አላቸው። የአፍሪካ ኤኮኖሚ በዋጋ ግሽበት፣ የመንግሥታት የበጀት ጉድለት እና በዕዳ ክፍያ መጨመር የታጀበ ነው።
    12 min
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱ በዋጋ ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ምን ይፈልጋል?
    በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከተካተቱ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ በወለድ ተመን ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ ነው። የፖሊሲ ለውጡ ብሔራዊ ባንክ “ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ” ሆኖ እንዲቋቋም የሚያስገድድ ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት መንግሥት የበጀት ጉድለት ሲገጥመው የሚበደረውን የገንዘብ መጠን በኃይል መገደብንም ይሻል
    10 min
  • ኢትዮጵያ ለካፒታል ገበያ አገልግሎት አቅራቢዎች ፈቃድ መስጠት ልትጀምር ነው
    ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ሥራ ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ለሚያቀርቡ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠት የምታደርገውን ዝግጅት እያጠናቀቀች ነው። የኢትዮጵያ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ ሥራ ለመጀመር የኢንቨስትመንት ባንኮችን ጨምሮ አስራ አምስት ዓይነት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ይፈልጋል። እንደ ዋትስአፕ እና ቴሌግራም በመሳሰሉ መንገዶች የአክሲዮን ድርሻዎች በማሻሻጥ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አዲስ ፈቃድ መውሰድ አለባቸው።
    10 min
  • የአውሮፓ ኅብረት የደን ጭፍጨፋ መከላከያ ሕግ የኢትዮጵያ ቡና ገበሬዎች እና ላኪዎችን አስግቷል
    የአውሮፓ ኅብረት ደን ተጨፍጭፎ የሚመረቱ ሸቀጦች ወደ ገበያው እንዳይገቡ ለመከልከል ያወጣው ሕግ የኢትዮጵያ ቡና አምራች ገበሬዎች ማኅበራት እና ላኪዎችን አስግቷል። ባለፈው ሰኔ የጸደቀው ሕግ ከኢትዮጵያ ቡና የሚገዙ የአውሮፓ ኩባንያዎችን ገና ካሁኑ እያሸሸ ነው። ከምታመርተው ቡና 30 በመቶውን ወደ አውሮፓ የምትልከው ኢትዮጵያ በሕጉ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ካላሟላች ትልቅ ገበያ ልታጣ ትችላለች።
    11 min
  • የጀርመን ገበሬዎች የአንድ ሣምንት ተቃውሞ ለምን ተቀሰቀሰ?
    የጀርመን መንግሥት ለግብርና ሥራዎች ይሰጥ የነበረውን ድጎማ በመቃወም የሀገሪቱ ገበሬዎች ለአንድ ሣምንት የሚዘልቅ ተቃውሞ ጀምረዋል። ተቃውሞው ባለፈው ሰኞ ሲጀመር በርሊንን ጨምሮ በብዙ ከተሞች መንገዶች እና አውራ ጎዳናዎች በትራክተሮች ተዘግተው ነበር። የጀርመን ገበሬዎች ለግብርና ሥራ ናፍጣ ሲሸምቱ ለሚከፍሉት ታክስ ከመንግሥት ማካካሻ ይሰጣቸዋል።
    10 min
  • በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ሥምምነት የተቀየመችው ሶማሊያ ፊቷን ወደ ግብጽ አዙራለች
    ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ በተፈራረመችው “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” የተቆጣችው ሶማሊያ ፊቷን ወደ ግብጽና ቃጣር አዙራለች። ሶማሌላንድ ኢትዮጵያ እውቅና የምትሰጥ የመጀመሪያ ሀገር በመሆኗ አመስግና ሥምምነቱን “የሚያስተጓጉሉ ወይም የሚቃወሙ” ወገኖችን አስጠንቅቃለች። ተንታኞች የለየለት ጦርነትም ባይሆን የእጅ አዙር ግጭትን ይሰጋሉ
    10 min

About ከኤኮኖሚው ዓለም

From the publisher's feed

በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።