ከኤኮኖሚው ዓለም

ከኤኮኖሚው ዓለም

Download on the App Store

ከኤኮኖሚው ዓለም episodes

  • የኢትዮጵያ መንግሥት ታክስ ሳይጨምር ከዘርፉ የሚሰበስበውን ገቢ 4 በመቶ ማሳደግ ይችላል?
    ኢትዮጵያ ከታክስ የምትሰበስበው ገቢ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (GDP) 4 በመቶ ለመጨመር መንግሥት ታቅዷል። ለ2017 በጸደቀው በጀት መንግሥት ከታክስ 502 ቢሊዮን ብር ሊሰበስብ ተዘጋጅቶ ነበር። በጀቱ ሲሻሻል በዕቅዱ መሠረት ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በአንድ በመቶ ጨምሮ ወደ 850 ቢሊዮን ብር ገደማ ከፍ ብሎ እንደሚከለስ ይጠበቃል።
    11 min
  • የኢትዮጵያ መንግሥት የኤሌክትሪክ ታሪፍን ቢያንስ በየሦስት ወሩ በ10 በመቶ ሊጨምር ነው
    የኢትዮጵያ መንግሥት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ በየሦስት ወሩ ቢያንስ በ10% ለመጨመር ተዘጋጅቷል። ጭማሪው መንግሥት ከዓለም ባንክ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ እና ብድር ባገኘበት ሥምምነት የተካተተ ነው። በሥራ ላይ ያለው ተመን ዕዳ ክፍያን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ወጪ የሚሸፍነው 18% ብቻ ነው
    11 min
  • ዶላር ፍለጋ፦ የኢትዮጵያ ባንኮች እና የጥቁር ገበያው ፉክክር እስከ የት ይጓዛል?
    ኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት መከተል ከጀመረች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ባንክ ባካሔደው ጨረታ አንድ ዶላር በ107 ብር ከ90 ሣንቲም ተሸጧል። ተመኑ ትላንት በባንኮች ከነበረው አማካኝ ምንዛሪ በ4 ብር ገደማ ከፍ ያለ ነው። ባንኮች በምንዛሪ ተመን ሲሽቀዳደሙ በተለምዶ ጥቁር እየተባለ የሚጠራው የትይዩ ገበያ ተዋንያን አድፍጠው ይታዘባሉ። በአዲሱ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት የዋጋ ግሽበት በጥር ከ30 እስከ 35 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሰነድ ያሳያል።
    11 min
  • ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያጸደቀው የኢትዮጵያ የተራዘመ የብድር አቅርቦት የፖሊሲ አላባዎች የሚሳኩ ናቸው?
    ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ያጸደቀው የተራዘመ የብድር አቅርቦት የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ያሉበትን ሥር የሰደዱ ችግሮች ለመቅረፍ የተወጠኑ አምስት የፖሊሲ አላባዎች አሉት። የገቢ እና የወጪ ንግድ ሚዛን ጉድለትን ለማረቅ እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገኝበታል። የተራዘመ የብድር አቅርቦት የተሰኘውን መርሐ-ግብር ለማስፈጸም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል። ዓለም ባንክ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ ሰጥቷል።
    14 min
  • ካማላ ሐሪስ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ ምን አይነት ኤኮኖሚያዊ እንድምታ ይኖረዋል?
    ጆ ባይደን ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ሲያገልሉ ዴሞክራቶች የመነቃቃት አዝማሚያ አሳይተዋል። በንግድ ሥራ የተሰማሩ ኩባንያዎች በአንጻሩ ካማላ ሐሪስ የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ በኤኮኖሚው ረገድ ምን ለውጥ እንደሚኖር እርግጠኞች አይደሉም። በርካታ ኩባንያዎች ግብር ለመቀነስ ቃል የገቡት ዶናልድ ትራምፕ እንዲመረጡ ይደግፋሉ።
    13 min
  • የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የመገበያያ ገንዘብ ልውውጥ ሥምምነት እንዴት ያለ ነው?
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ 817 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የመገበያያ ገንዘብ ልውውጥ ሥምምነት ተፈራርመዋል። ባንኮቹ ሥምምነቱ “በሁለቱ ሀገራት መካከል የፋይናንስ እና የንግድ ትብብርን ይደግፋል” ብለዋል። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ኻሊድ ሞሐመድ ባላማ ናቸው። ባንኮቹ በድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች ብር እና ድርሐም የበለጠ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እንዲሁም የክፍያ እና የመልዕክት መለዋወጫ ሥርዓቶችን ለማስተሳሰር የመግባቢያ ሥምምነቶች ተፈራርመዋል።
    11 min
  • የኢትዮጵያ ሠራተኞች አማካኝ ገቢ ለመሠረታዊ ፍላጎቶች ከሚያስፈልገው የመኖሪያ ደመወዝ በ2000 ብር ያነሰ ነው
    በኢትዮጵያ አማካኝ ወርሀዊ ደመወዝ 3000 ብር እንደሆነ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (ILO) ይፋ አድርጓል። ይኸ ለመሠረታዊ ፍላጎቶች ከሚያስፈልገው መኖሪያ ደመወዝ (Living Wage) እጅግ ያነሰ ነው። ኢትዮጵያ እንደ ጎረቤቶቿ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ካልደነገጉ የመጨረሻዎቹ የአፍሪካ ሀገራት አንዷ ናት።
    11 min
  • የብሔራዊ ባንክን ካፒታል ከ500 ሚሊዮን ወደ 10 ቢሊዮን ብር የሚያሳድግ የአዋጅ ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተከፈለ ካፒታል ከ500 ሚሊዮን ብር ወደ 10 ቢሊዮን ብር የሚያሳድግ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። በረቂቅ አዋጁ “የዋጋ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የገንዘብ ፖሊሲን ቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ” የብሔራዊ ባንክ ዋና ዓላማ ነው። መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደው የብድር መጠን፣ የአከፋፈል ሁኔታ እና ወለድ የሚወስኑ ድንጋጌዎች ተካተውበታል።
    11 min
  • ለብድር አሰጣጥ ጠበቅ ያሉ መመሪያዎች ያወጣው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እስከ ዛሬ የት ነበር?
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመንግሥት ባንኮች እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እንደ “ተዛማጅ ወገኖች” እንደሚቆጠሩ ወስኗል። የባንኩ መመሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተቋማቱ የሚሰጠውን የብድር መጠን እንዲገድብ የሚያስገድድ ነው። እስከ ጎርጎሮሳዊው 2022/23 ብቻ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች 777.8 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለባቸው።
    10 min
  • የኢትዮጵያ የበጀት ጉድለት በ2017 ከአጠቃላይ ሀገራዊ የምርት መጠን 2.1% ድርሻ ይኖረዋል
    በ2017 የኢትዮጵያ የበጀት ጉድለት ከአጠቃላይ ሀገራዊ የምርት መጠን 2.1% ድርሻ እንደሚኖረው አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። መንግሥት ለሚቀጥለው ዓመት ያዘጋጀው 971 ቢሊዮን ብር በጀት 358.5 ቢሊዮን ብር ጉድለት ይገጥመዋል። ከ2017 በጀት 139.3 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ የታቀደ ነው። መንግሥት ኤኮኖሚው በ8.4% ያድጋል ብሎ ይጠብቃል። ኢትዮጵያ የምትከተለው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት በ2017 እንደሚቀጥል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጸዋል።
    11 min

About ከኤኮኖሚው ዓለም

From the publisher's feed

በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።