
Sign up to save your podcasts
Or


የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ማደግን ተከትሎ፣ የኦንላይን ማጭበርበር በዲጂታል አለሙ ውስጥ ትልቅ ችግር እየሆነ መጥቷል። በዚህኛው #ለአራዳፖድካስት ክፍል ላይ ኦንላይን ማጭበርበሮች እንዴት እንደሚመጡ፣ ምን አይነት ችግር ሊፈጥሩብን እንደሚችሉ እና ራሳችንን ለመጠበቅ መተግበር የምንችላቸውን ቴክኒኮች ተወያይተናል።
Following the increasing number of social media users, online scams have become one of the biggest challenges in the digital world. In this episode of #LeAradaPodcast, we delve into how scams come, how they affect us, and techniques we can apply to protect ourselves.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
በዚህ ከፍተኛ የሥራ ፉክክር በበዛበት ወቅት የኦንላይን ሥራ እየተለመደ መጥቷል፤ ከተማርነው ትምህርት በተጨማሪ ኦንላይን ላይ ልንሰራቸው የምንችላቸው እና ክፍያ የምናገኝባቸው በርካታ የተለያዩ ሥራዎች አሉ። ስዩም ባለው የትርፍ ሰዓት ኦንላይን ላይ የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ጥሩ ገቢ ያገኛል። በዚህ #ለአራዳፖድካስት ክፍል ልምዱን አካፍሎናል።
In this time of high unemployment and fierce competition for the few opportunities, there is a shift towards the internet and digital world for jobs, and making a living is one way of taking advantage of technology. There are a lot of jobs online we can do outside of what we studied and get paid for. As a part-time job, Seyum makes a decent monthly income by freelancing online. In this episode of the #LeAradaPodcast, he shares his experience.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
በዚህኛው #ለአራዳፖድካስት ክፍል የስነ ልቦና ባለሞያ ከሆነው አባይዳር ወርቄ ጋር ሶሻል ሚዲያ እና የአዕምሮ ጤና ስላላቸው ግንኙነት፤ የአዕምሮ ጤናችን ላይ ሊያመጣ ስለሚችለው ተፅዕኖ እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የአዕምሮ ጤናን ጠብቀን መቆየት ስለምንችልባቸው መንገዶች አውርተናል።
In this Episode of #LeAaradaPodcast, we invited Abaydar Workie, to talk about the relationship between social media and mental health, the impact it can have on our mental health and also ways to maintain our mental health while using social media.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
ሰላማዊት ተዘራ በድጋሚ መጥታለች፤ በዚህኛው #ለአራዳፖድካስት ክፍል ኦንላይን ላይ እንዴት በምቾት መጠቀም እንደምንችል እና ያለንን መረጃ እንዴት መጠበቅ እንዳለብን እንዲሁም የተለያዩ የግል ተሞክሮዎችን በማንሳት በቀላሉ ልንተገብራቸው የምንችላቸውን ጠቃሚ ነጥቦች ዙሪያ በስፋት ተወያይተናል።
Selamawit Tezera is back. In this episode of #LeAradaPodcast, we talked about the risks of being compromised online and how that might affect us. We discussed how we can protect our online information, how we should behave while surfing the digital world, and reflected on some real-life experiences to provide tips we can apply to stay safe and better secure our information.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
በኢንተርኔት አለም ላይ አንድ ጠቃሚ እና አስደናቂ ነገር፤ በኦንላይን ላይ እንዴት መጠቀም እንዳለብን ካወቅን በዲጂታል አለም ውስጥ ገቢ መፍጠር ወይም ገቢን ማሳደግ እንችላለን። ዮርዳኖስ ሰለሞን በአንድ ወቅት ባጋጠመው ህመም ምክንያት ቀኑን ሙሉ በአልጋ ላይ ነበር የሚያሳልፈው። ያን ጊዜ ነበር በኦንላይን ላይ ገንዘብ ማግኘት የሚቻልባቸውን አማራጮች መሞከር የጀመረው። ይህ ሙከራ እና ትጋት አሁን ላይ በዲጂታል ግብይት የተሻለ ገቢ እንዲያገኝ አስችሎታል። በዚህ #ለአራዳፖድካስት ክፍል የራሱን ተሞክሮዎች በመጥቀስ በኦንላይን ላይ እንዴት ገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል አካፍሎናል።
One useful and fascinating thing about the internet is that if we know how to navigate our way, we can make money or generate income in the digital world. Yordanos Solomon was once paralyzed and spent his days in bed. It was then that he started to explore the internet and digital world and see if he could turn the time he had into money. His devotion and dedication eventually enabled him to become a digital marketing expert. In this episode of #LeAradaPodcast, he talked about how it is very easy to make money online, referring to local and real examples.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
ስልካችን ከዕለተዕለት ህይወታችን ጋር በጣም የተጣበቀ በመሆኑ ብዙ መረጃዎችን በስልካችን ላይ እናስቀምጣለን፤ አንዳንዶቹም በጣም ምስጢራዊ መረጃዎች ናቸው። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን በስልኮቻችን በኦንላይን ላይ መረጃን እንዴት መጠበቅ እንደምንችል በቂ እውቀት የለንም። በዚህ #ለአራዳፖድካስት ክፍል የሞባይል የስጋት ኢንተለጀንስ እና ደህንነት ኤክስፐርት ከሆነው ሲራክ ኃይሉ ጋር ሞባይል ስልኮች እንዴት እንደሚሰሩ፣ መረጃን ለመጠበቅ ስለሚጠቅሙ አማራጮች እና መንገዶች እንደዚሁም ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ለመቀነስ ልናዳብር ስለሚገባን ልማዶች ተወያይተናል።
As our phone is very much attached to our day-to-day lives, we put a lot of information on the device, some of which is much more sensitive. But most of us don’t have adequate knowledge about how we can protect information online on our phones. In this episode of #LeAradaPodcast, we talked with Sirak Hailu, a mobile threat intelligence and security expert, about how mobile devices work, available options and features to protect information, and habits we should develop to minimize threats that could happen.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
#ለአራዳፖድካስት በዚህ ክፍል አሪፍ አሪፍ በሆኑ ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጠራዋ የምትታወቀውን ሰላም አታላይን ጋብዘናታል። ሰላም ሳይኮ ቴራፒስት እና የራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ነች። በማህበራዊ ሚዲያ በምታካፍላቸው ይዘቶች እየፈጠረች ሰላለችው ተፅዕኖ ፤ ስላለፈቻቸው ተግዳሮቶች እና ስኬቶች እንዲሁም ያልተነገሩ አስገራሚ ገጠመኞቿንም አውርታናለች።
In this Episode of #LeAaradaPodcast, we hosted one of the coolest social media content creators, psychotherapist, and radio producer, Selam Atalay. She talked about her journey as a social media content creator, the impact she is creating, her challenges, and her success. She has also shared with us some of her untold stories.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
በዚህኛው #የለአራዳፖድካስት ዝግጅታችን ወጣት ቢፀ ተስፋዬን ይዘን ቀርበናል። ቢጸ ወደ ዲጂታል ማርኬቲንግ ሙያ ከመግባቱ በፊት ከተማረው የማህበረሰብ ጤና ሙያ ወደ መዝናኛው ዓለም በመቀላቀል የፊልም ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በነበረን ቆይታ መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ ከመጀመራችን በፊት ስላሉ የተለያዩ ልናደርጋቸው እና ልንከተላቸው የሚገቡ ቅደም ተከተል ጉዳዮች ተወያይተናል።
This time, #LeAradaPodcast featured Bitse Tesfaye, a fascinating young man from DireDawa who studied public health, then jumped into the entertainment industry and became a movie maker before switching to a career in digital marketing. We talked about the basics of digital marketing, the steps and techniques we can follow when considering getting into it, the benefits of integrating digital marketing with traditional marketing to boost revenue and better explore options, and Bitse's journey toward becoming an expert at it from scratch.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
የኦንላይን ላይ ትንኮሳ፣ ጥቃት እና የመሳሰሉት በዲጂታሉ አለም ላይ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች ናቸው። በዚህኛው #ለአራዳፖድካስት ክፍል ሰላማዊት ተዘራን ከ SheEsecure ይዘን ቀርበናል። በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈፀሙ ፆታን መሰረት ያደረጉ ትንኮሳዎች እና ጥቃቶች ምን አይነት ቅርፅ እና ይዘት እንዳላቸው ፤ ስለሚያደርሱት ጉዳት ፤ እነዚህን ትንኮሳዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስናያቸው እንዴት ልንለያቸው እንደምንችል እና በሚያጋጥሙን ጊዜ ምን ማድረግ እንደምንችል ተወያይተናል።
Online harassment, abuse, bullying, etc, are challenges with the internet. In this episode of #LeAaradaPodcast, we featured Selamawit Tezera from SheEsecures. This online channel uses the internet for good causes, works for digital rights, and fights online gender-based violence. We talk about the forms and formats these abuses take, how to identify such abuses, and what to do when coming across them on social media.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
የመረጃ አጣሪ ባለሙያ ርሆቦት አያሌውን አስታወሳችኋት? በዚህ ክፍል ሶሻል ሚዲያ ላይ ወይም ኦንላይን የምናገኘውን መረጃ እንዴት ማረጋገጥ እንደምንችል ልታወራን በድጋሚ መጥታለች። በተጨማሪም የግል ተሞክሮዎቿን እና መረጃ በምታረጋግጥበት ወቅት ያጋጠሟትን አስቸጋሪ ነገሮች አካፍላናለች። ስለተለያዩ ልንተገብራቸው ስለምንችላቸው ቴክኒኮች እና ምክሮች፤ የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎች ስለሚመጡባቸው መንገዶች እና ቅርፆችም አውግተናል።
Remember Fact-checker Rehobot Ayalew from our first episode? She is back again, this time to discuss how we can verify information we found on social media or online. She shared her personal experience and the challenges she faced while fact-checking. We also talked about techniques, steps, and tips we can apply, and the forms and formats where misinformation and disinformation take place.
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.
From the publisher's feed
This is very interesting podcast "Le’Arada podcast" is for all social media users who want to navigate the internet and digital world safely and responsibly. Le’Arada covers…
ለአራዳ ፖድካስት ሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚ ለሆኑ ሁሉ እና የኢንተርኔቱን እና የዲጂታሉን አለም በደህንነት እና በአግባቡ መጠቀም ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ፖድካስት ነው። ለአራዳ ላይ በዲጂታሉ አለም ላይ ወሳኝ እና አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን በመዳሰስ ጠቃሚ መረጃዎችን፣ ምክሮችን እና ሊተገበሩ የሚችሉ ቴክኒኮችን በማቅረብ ሰዎች ውጤታማ፣ ፈጣን እና ምርጥ ሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ነጥቦች ይቀርባሉ። በዲጂታሉ አለም ላይ የዳበረ ልምድ ያላቸው እንግዳዎች ከአቅራቢዎች ነዋል እና ኪሩቤል ጋር ይስቃሉ ይጫወታሉ። #ለአራዳፖድካስት
Hosted on Acast. See acast.com/privacy for more information.