"ከባድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቴክኖሎጂን ከመሞከር ወጥተን ወደ ሥርዓታዊ ኢኮኖሚ መሸጋገራችንን ያሳያሉ። በአገራችን ከ60% እስከ 70% የሚሆነውን የምርትና አገልግሎት እንቅስቃሴ የሚይዙት እነዚህ በመሆናቸው፣ ሽግግሩን ስኬታማ ለማድረግ የትራንስፖርት፣ የኢነርጂ እና የኢንዱስትሪ ፖሊሲዎቻችንን ማጣጣም አለብን።" ሲሉ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኤክስፐርት በረከት ተስፋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተች ነው። በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶአችን ሁለት ሀገራዊ ፋይዳቸው የላቁ ጉዳዮችን ይዘንላችሁ ቀርበናል፦
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አብዮት፦ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ያደረጋትን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ንቅናቄ በተለይም ወደ ከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች (Heavy EVs) የምታደርገውን ሽግግር ከዘርፉ ኤክስፐርት አቶ በረከት ተስፋዬ ጋር እንቃኛለን።
የብሪክስ (BRICS) አባልነት እና ጥቅሞቹ፦ የኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆን የሚያስገኛቸው የፋይናንስ ዕድሎች፣ የገበያ ትስስር እና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ የሚረዳው የገንዘብ ልውውጥ ወይም 'ከረንሲ ስዋፕ ስልት በምን መልኩ ይተገበራል? በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ያየው ገነት ሰፊ ትንታኔ ይሰጡናል።