“አፍሪካውያን የራሳቸውን ታሪክ በራሳቸው መንገድ እና አተራረክ ዘዬ ማቅረብ አለባቸው የሚል ትልቅ የፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ አለ። […] ያ ትግል ረጅም ዓመት ሄዷል፣ ግን ያን ያህል ውጤታማ መሆን አልቻለም። ውጤታማ እንዳይሆን ያደረገው ትልቁ ምክንያት የመረጃ ክፍተት ነው። መረጃ ደግሞ ኃይል መሆኑን የምታውቀው ቢያንስ የራስህ ባይሆን እንኳን አንተ የምትቆጣጠረው ሚዲያ ወይም በአንተ መጫወቻ ሜዳ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ነው።” ሲል በስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮ አዘጋጅ እና አቅራቢ የሆነው ዐብይ ሀብታሙ ተናግሯል።