የመጀመሪያው የወንጌል መልዕክት ለእግዚአብሔር መኖር ነው:: እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ እግዚአብሔርን ሊያመልክና ለእርሱ ሊኖርም እነደሆነ ሁሉ ሰው በክርስቶስ በማመን ከአለም ሲወጣ በፀጋው ለጌታ እንዲኖር ነው::
*** እግዚአብሔር በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ከሰው ጋር ይኖራል:: ሰው ደግሞ በፀገው ወደ እግዚአበሔር የሚቀርብ ሆነ::: ይህም ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ተከናውኗል:: እግዚአብሔር በምህረቱ በክርስቶስ ወደ እኛ መጥቷል:: ፅድቅና በጎነት የሌለን እኛ ደግሞ በክርስቶስ በፀጋው ወደ እግዚአብሔር ቀርበናል::
*** አማኝ ሁሉ ይህ የወንጌል ዕውቀት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ደግሞ ሁልጊዜ የሚያነቃቃና ስላልዳኑት የምስክርነት ትጋት የሚሰጠን የዚህ የወንጌል መንፈስ ሊኖረን ይገባል::