እሺታና እምቢታ በሰው ህይወት ውስጥ የሚታዩና የማነነታችን አንዱ መገለጫ የሆኑ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው:: እምቢታ የኃጢአት የአመፅና የእልከኝነት ፍሬ ነው:: እሺታ ግን ከእግዚአብሔር የሆነና ሰውን ወደ በጎና መልከም ወደሆነ መንገድ የሚመራበት ነው:: ዳዊት " በእሺታ መንፈስ ደግፈኘ" ብሎ እንደፀለየ::
የእኛን እሺታ የሚፈልጉ ነገሮች በእኛ ሚዛን ሲመዘኑ ፈፅሞ ስፍራ የማንሰጣቸው የተናቁ ሊሆኑ ይችላሉ:: ነገር ግን እሺ ብለን ብንታዘዝ ለፈውሳችንና ለበረከታችን መለቀቅ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉና:: ንዕማን እሺ ብሎ እርሱ በናቀው ውሃ ውሰጥ ገበቶ ፈውሱን እንደተቀበለ::
*** ነገሮች በእኛ ፊት የተናቁና ክብደት የሌላቸው ወይንም ደግሞ አሰፈሪዎችና እንዴት ይሆናል የምንለው ቢሆን እንኳ የእኛን እሺታ እሰከፈለጉ ድረስ በጌታ ፀጋ ልንዘረጋ የተገባ ነው::