መቆም ማለት በጌታ ተስፋ ቃል ላይ እንዲሁም በእኛ ሁኔታ በተገለጠልንና በተናገረን ላይ ተመስርተን በእምነት የተዋሀደን ያ የቆምንበት ነው:: ቆምን ማለት ቃሉ በእምነት ተዋህዶን የሆንበተ ማንነት ነው:: ደስ የምንሰኝበት የሚሰማንና የምንነካባቸው ሁሉ የቆምንባቸው አይደሉም:: መንፈሳዊ ነገር ሰሜት ላይ ብቻ የሚቀር ሳይሆን ከዚህ ያለፈ ወደ መሇን የሚደርስ ነው::
*** እግዚአብሔር የሚፈልገው ውጫቸውን በውስጣቸው በቆመ ማንነታቸው ያሸነፉ የገዙ ሰዎች ማውጣት ነው:: እነዚህ ናቸው ሁሉን ፈፅመው በሰው ልጅ ፊት ለመገለጥ የሚበቁት::