ትዳር ማለት መውሰድ እንዲሁም ደግሞ መወሰድ ማለት ነው:: ከፈጥረት መጀመሪያ አዳም ሄዋንን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብሎ እንደወሰዳት እነዲሁ ዛሬም አንዳችንን ለአንዳችን የሚሰጥ ትዳርን የሚሠራ እርሱ እግዚአብሔር ነው::
ሰለዚህ የተወሰደ አይመለስም:: ምክንያቱም ሁለቱ ተጣብቀዋልና:: አንድ ስጋ ሆነዋልና::
ትዳርን የሚጠብቀው ሁለቱም በመንፈሳዊ ህይወታቸው በሁለት እግራቸው የቆሙና በብርሃን ውስጥ መሆናቸው ነው::
*** - በግል ህይወቴ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት በፅድቅና በአውነት አለሁ ወይ ?
- አልሆነችልኝም ወይም አልሆነልኝም ሳይሆን እኔ ሆኜለታለሁ ወይ ? ወይም ሆኜላታለሁ ወይ ?
ብሎ መጠየቅ ከሁለቱ የትዳር አጋሮች ይጠበቃል: